February 26, 2021
9 mins read

“አይ AM NASTY?!!” በሐገር ቤት ስላሉ የሰብዓዊ መብቶች ነጋዴዎች እና ስለ ፍስሐ ተክሌ

ከታዛቢ – የካቲት 19 / 2013 ዓ.ም.

ይህን አጭር ጽሁፍ እንድጽፍ ያስገደደኝ (ያበረታታኝ?) ደጀኔ አሰፋ ነው፤ አምነስቲ ኢንተርናሽናል – “አይ AM NASTY?!!” አለው ደጀኔ!? – ዛሬ ያወጣው መግለጫም ለዚህ ጽሁፍ የራሱ አስተዋጽዖ አለው፡፡ ደጀኔ አሰፋ፣ ስለ አምነስቲ ኢንተርናሽናል የምሥራቅ አፍሪካ ቅርንጫፍ (Hub)፣ በተለይም ስለ ፍስሐ ተክሌና ሐበን ፈቃዱ፣ በዘሐበሻ ፌስ ቡክ ገጽ ላይ ዛሬ ያጋለጠው መረጃ በራሱ ዓይን ገላጭ ነው፡፡ የደጀኔ ማስረጃ የሚያሳየው የራያን አውድ ብቻ ቢሆንም፣ ዕውነት እንደሚሆን ግን እኔ ጥርጥር የለኝም፡፡ ምክንያቱም የርሱን ቅሬታና ማስረጃ የሚያረጋግጡ በሌሎች አውዶች ሊቀርቡ የሚችሉ በጣም ብዙ ማስረጃዎች ስላሉ ነው፡፡ ስለ ሐበን ፍቃዱም የገለጸው ትክክል ነው፤ የፍስሐ ተክሌ ተባባሪ ስለመሆኗ ማስረጃ አለ (አንዳንዴ የሚጣሉ ቢመስሉም)፡፡

ዓለም አቀፍ ሸረሪት እና ሰብዓዊ መብቶች ነጋዴዎች

ደጀኔ የገለጸው እነፍስሐ ከወያኔ ጋር የነበራቸውንና ያላቸውን የጥቅም ግንኙነት ብቻ ነው፡፡ መረባቸው ግን ተቋም-ተሻጋሪ፣ ብዙ ሰው ሊገምት ከሚችለው በላይ የሰፋ፣ የተወሳሰበና አስፈሪም ነው፡፡ ሥሩን ባሕር ማዶ ያደረገና ሐገር ቤትም ሰፊ መረብ/ቅርንጫፍ ያለው ዓለም አቀፍ ሸረሪት አለ፡፡ እነ ፍስሐ ተክሌ በውጭ የሚገኙ የሸረሪቱ ድሮች ናቸው፡፡ ከለውጡ በፊትም ዛሬም በሐገር ቤት ተንሰራፍተው የሚገኙ የዚሁ ዓለም አቀፍ ሸረሪት / ኔት ዎርክ አካል የሆኑ የሰብዓዊ መብቶች ነጋዴዎች (Human Rights Entrepreneurs) አሉ፡፡ እነዚህ በሐቀኛ የሰብዓዊ መብቶች ድርጅት እና በሰብዓዊ መብት ልዩ ልዩ ስሞች በሚንቀሳቀሱ “የቦርሳ ውስጥ ድርጅቶች” ውስጥ በአመራርነት ተሸጉጠውና ራቅ ብለውም በአማካሪነት ስም መሽገው ይገኛሉ፤ በሰብዓዊ መብቶች ታጋይነት ስም የግል ጥቅማቸውን ሲያሳድዱ እስካሁን የቆዩ ናቸው፡፡ …

ፍስሐ ተክሌ በብሔሩ ከነዚህ ቢለይም የነዚህ ነጋዴዎች የቅርብ ጓደኛና የጥቅም ተባባሪ ነው፤ (ከሰብዓዊ መብቶች ነጋዴዎቹ የሐገር ውስጥ መረብ አመራሮችና አባላት መካከል የሚበዙት የአማራ ተወላጆች ናቸው)፡፡

የሰብዓዊ መብቶች ፕሮጀክት ፋብሪካዎች (Human Rights Project Factories)

እነዚህ የሰብአዊ መብቶች ነጋዴዎች “የተማሩ” ናቸው፤ “የታወቁ” የሰብዓዊ መብቶች ፕሮጀክቶች ፋብሪካዎችም ናቸው፡፡ መሬት ላይ የማይወርዱ፣ ለሕዝብና ለሐገር የረባ ጥቅምና ለውጥ የማያመጡ ልፍስፍስ ፕሮጀክቶችን ቀርጸው ይቸበችባሉ፡፡ ለነዚህ ፕሮጀክቶቻቸው ማስኬጃ የሚያስፈልጋቸውን ገንዘብ በዶላርና በዩሮ የሚሰጧቸው ዓለም አቀፍ ተቋማት አሉ፡፡ ዋናዋናዎቹም የፋብሪካው መሥራችና መሪዎችም፣ ተቀማጭነታቸው አዲስ አበባ ለሆነ አንዳንድ ኤምባሲዎች “የአማካሪነት” አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡

ሐገር ቤት ላሉት የሰብዓዊ መብቶች ነጋዴዎች የገንዘብ ድጋፉን የሚያሳልጡላቸው፣ ፍስሐ ተክሌን የመሰሉ፣ በልዩ ልዩ ዓለም አቀፍ “የነጻነት፣ የዴሞክራሲና የሰብዓዊ መብቶች” ተቋማት ውስጥ የተሰገሰጉ የጥቅም ተካፋዮቻቸው ዛሬም አሉ፡፡ አንዳንዴ በኤክስፐርትና በተንታኝ ስም በዓለም አቀፍ ሜዲያዎችና መድረኮች ላይ አፍቃሪ ወያኔና ጸረ ኢትዮጵያ ዘመቻ ሲያካሂዱ እያየናቸው ነው፡፡ የሰብዓዊ መብቶች ፕሮጀክቶች ፋብሪካ የሆኑት የሰብዓዊ መብቶች ነጋዴዎች በነፍስሐ ተክሌ አማካኝነት እና ራሳቸውም ባላቸው ግንኙነት ከሚያገኙት ዶላርና ዩሮ ውስጥ 80 በመቶው ራሳቸው ኪስ የሚገባ ነው፡፡ አንዳንዴም በፕሮጀክት ድግግሞሽና ተመሣሣይነት ምክንያት የእርዳታ ሰጪውን ቅድሚያ ለማግኘት እርስ በርስ ሲሻኮቱ ታገኛቸዋለህ፡፡ ክፋቱ ወዲያው መልሰው ይገጥማሉ!

ሸረሪቷና ድሯ የሚናቁ አይደሉም!

የነፍስሐ ተክሌንና በውስጥ ያሉትን ነጋዴዎች ሥፍር ቁጥር የሌለው ጉድ ልታጋልጥ ብትሞክር የሚሰማህ የለም/አልነበረምም፡፡ ችግሩ የወያኔ ሽፋን ሰጪነትና የኔት ዎርኩ ጠንካራና ሰፊ መሆን ብቻ አይደለም፤ ነጋዴዎቹ ትርፍራፊ የሚጥሉለት፣ ተስፋ የሚሰጡት፣ አድርባዩ፣ ፈሪውና ነገሩ ያልገባው ሁላ ያዋክብሃል ወይም ቸል ይልሃል! ከነጋዴዎቹ ጋር ብትተቃቀፍ ደግሞ የሚያቀርቡልህ ቁሳዊ ጥቅም የሚያማልል ነው፤ ጥቅሙን በነርሱ ኑሮና አኗኗር ላይ ታየዋለህ፡፡ የሰብዓዊ መብቶች ነጋዴዎቹን እና አምነስቲን ጨምሮ ዓለም አቀፍ መረቡን ለመጋፋት መሞከር አደገኛ ነው፡፡ በነጋዴዎቹ በራሳቸው፣ በሥውር እጆችና በእጀ ረዥሞቹ የሚከፈትብህ ዘመቻና የሚያርፍብህ ጥቃት መዘዙም ብዙ ነው፡፡ የሚሰማቸው የዋህና እነርሱን መሰል መሰሪም ያገኙ ከመሰላቸው የወያኔ ቅጥረኛ እንደሆንክ አድርገው ሁሉ ስምህን ያጠፉታል፡፡ ዛሬ ሌላ ቀን ቢሆንም፣ “እንኳን ዛሬ፣ እንኳን እናንተን፣ ትናንትም ወያኔን ራሱን አልፈራንም!” ብትልም አይበቃም፡፡ ፍስሐ ተክሌንም ሆነ የሐገር ቤቶቹን የሰብዓዊ መብቶች ነጋዴዎች እንደ ግለሰቦች ብቻ መመልከት ስህተት ነው! እነርሱ ተቋም፣ ሰፊና ውስብስብ መረብ እንዲሁም መቀመጫዋን ውጭ ያደረገች የትልቅ ሸረሪት ድሮች ናቸው!! ከነርሱ ጋር የሚደረገውም ትግል ከፍተኛ ብልሐትና ጥንቃቄን ይጠይቃል!

የኢትዮጵያ ዋርካና የሰብዓዊ መብቶች አባት፣ ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም ከማለፋቸው ከወር በፊት፣ እነዚህን የሰብዓዊ መብቶች ነጋዴዎች፣ “ጋዜጠኞች/ ሜዲያ ጠርቼ በአደባባይ ለሕዝብ አጋልጣቸዋለሁ!” ብለው ነበር፡፡ ይህን ማለታቸውን ማረጋገጥ የሚፈልግ፣ በህልፈታቸው ማግሥት በኢሳት ቴሌቪዥን ላይ በዓይን እማኝ መገለጡን ማጣራት ይችላል፡፡ ሞት ቀደማቸው!

አሁን ለሐገርና ለሕዝብ ሕልውና ሲባል፣ ለመነጋገር ጊዜው ግድ የሚልና የደረሰ ይመስላል! ይህ ለሕዝብና ለሚመለከተው ክፍል ፍንጭ እንዲሆን ብቻ ነው! ዝርዝሩማ ገና ምኑ ተነክቶ …

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ከአድፋጭ ሠይጣኖችም ይጠብቅልን!

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop