የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)ሰልፉን ሰረዘ

ለአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች፤
*****
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በአማራዎች ላይ እየተፈፀመ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ለማውገዝ ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱ ይታወቃል።
በጠራው ሰልፍና ከሰልፉ ጋር ተያይዞ በተፈጠሩ ጉዳዮች ዙሪያ ብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚው ዛሬ ማምሻውን እስከ ምሽቱ 5:00 ድረስ ውይይት ያደረገ ሲሆን አብን ጠርቶት የነበረውን ሰልፍ በመንግስት አምባገነናዊ ተግባር ሰልፉን አስተባብሮ በተቋማዊ ማዕከላዊነት ለመምራት ባለመቻሉ መሰረዙን ይገልፃል።
ስለሆነም የንቅናቄያችን አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች አብን ሰልፉን የሰረዘ መሆኑን አውቃችሁ ሰልፎችን ከማስተባበርና ከመምራት እንድትቆጠቡ እያሳወቅን ቀጣይ የአብን የትግል አካሄዶችን በተመለከተ በቅርቡ የምናሳውቅ ይሆናል።
አንድ አማራ ለሁሉም አማራ፣ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ!
ተጨማሪ ያንብቡ:  ከኦነግ ሸኔ እና ህውሃት ጋብቻ ጀርባ ያለው ሚስጥር ተጋለጠ!

2 Comments

  1. አብኖች ይህን ጉዳይ በስሱ አድርጉት፡ ጉዳዩ እንዲህ ነው፤
    1. የአማራ ብልጽግና በክልሉ ትቀባይነት እያገኘ መምጣት አብንን በጣም አሳሰበው፡ ታስታውሱ እንደሆነ ተመስገን ጥሩነህ ሽመልስ አብዲሳን ካባ ሲያለብሰው የአማራ ህዝብ “እሰይ” ባይልም አልከፋውም፡ በፋኖ ሥም ዘረፋ ቆመ፤ በክልሉ ሰላም ወረደ፡ ምረጫ መጣ ተባለ፡ አብንም የህዝቡ ዝምታ አሳሰበው፡፡
    2። ገዳይ/አስገዳዮችም የአማራን የውጊያ ቀጠና ከክልሉ ውጭ አደረጉት፡ አብን አጋጣሚዋን መጠቅም ፈለገ፡ ሰላማዊ ሰልፍ ጠራ፤ (እስቲ ማን ይሙት “በክልሉ ከተሞች ሁሉ” ተብሎ ሰልፍ ይጠራል?)
    3። ጥሪው በአማራ ህዝብ ሳይቀር “ወቅታዊ አይደለም” እንደተባለ እና ሰው እንደማይወጣ (በተለይ አዲሳባ) ጣሂር መግለጫውን አንብቦ ሳይጨርስ ተገለጸለት፡
    4። ጣሂር በአባይ ሚዲያ “የህጻን ተንታኞች” ታጅቦ መጣና “ሰልፉ ይደረጋል፤ ይደረጋል” ብሎ እንደመፎከር አደረገው፡፡
    5። ድንጉጡ የአማራ ብልጽግና በቲቪ ወጥቶ “ሰልፉ እውቅና የለውም” አለን፤
    6። አብን በፖሊስ ተከበብኩ “ሰልፉን ሰርዣለሁ” አለን፤ እንግዲህ ዋናው ነጥብ እዚህ ላይ ነው፡፡ (ሌላ የሚገርመው የፖሊስ ከበባ መኖሩን አንድ ሚዲያ እንኳ ከቦታው ሊያረጋግጥልን አልቻለም)
    አብን የሚፈልገውን “የወንድ በር” አገኘ፡ አስተውላችሁ ከሆነ ብዙም አልተንጫጩም፤ በውስጣችውም ከመጀመሪያው ለውሳኔው ከፍተኛ ፍጭት የነበረ ይመስለኛል)፤ እግረ መንገድ ግን “አቢይ አምባገነን ነው” የሚለውን መልክት ለማስተላልፍ ሞከሩ፤ እምም።ህዝብ ነቄ ነኝ አለ!
    በነገራችን ላይ አብኖች ወሳኝ በሆነ ውቅት (የሃጫሉን ሞት ተከትሎ በመጣውና ምርጫውን ከማስተላለፍ ጋር ተያይዞ) ለወሰዱት አቋም አድናቆቴ እና አክብሮቴ እንዳለ ነው፡ የፖለቲካ መስመራችውን ባልስማማም አላወግዝም፤ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥም አስፈላጊ ናቸው ብዬ አምናለሁ፤ ይቺ አሁን ሰልፍ የጠሯት ግን በፍጹም ወቅቱ አይፈቅድም፤ ስለዚህ ተከልከልን ብለው ብዙ ባያስጮኋት ጥሩ ነው፡፡

  2. ታዲያ ሲከለከሉ ለምን ለአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ለኦቦ ሽመልስ አብዲስ እና ለኮ/ል አብይ አህመድ ጥያቂያቸውን አያስገቡም፡፡ ምንአልባት ችግሩ ደብዳቢያቸውን ለጥበቃ ክፍል ሃላፊው ለኮንስታብል ተመስገን ጥሩነህ ማቅረባችው ሊሆን ይችላል፡፡ ለማንኛውም ያበሳጫል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share