የኢትዮጵያ አንድነት አንዲጠበቅ ፣ ፍትሕ እና ዲሞክራሲ እውን እንዲሆን ዜጎች አፍራሾችን ልንታገል ግድ ይለናል!

ከኢትዮጵያ አገር አድን ግብረኃይል የተሰጠ መግለጫ!!

የኢትዮጵያ  አገር አድን ግብረኃይል አገራችንን  የኦሮሞ ጽንፈኞችና  ሕወሓት አንድነትዋንና  ሰላሟን  ለማናጋት እየወሰዱት ያሉትን ዕኩይ ዓላማ በመቃወም የተመሠረተና አገዛዙ ጽንፈኞችን  ለመዋጋት ዓልሞ በዚሁ ሰበብ ያለአግባብ የሰላማዊ የድርጅት መሪዎቸን በቁጥጥር ሥር  በማዋሉ  በጥቅሉ የኅሊና  እስረኞችም እንዲፈቱ በቅርቡ በዋሽንግተን ዲሲ የኀሙሱን ሰልፍ የጠራው አካል “ አገር አድን ግብረኃይል ”  በሚል ስያሜ የሚታወቀው እንደሆነና ይህ እንቅስቃሴም በአገራችን ሰላም ዕኩልነት ፍትሕና ዲሞክራሲ እስካልሰፈኑ ድረስ  ለነዚህ ዕውን መሆን  የብዙኃኑን ድምፅ በማሰማት እንዲቀጥል በመወሰን እየሰራን እንገኛለን ፤

እንደሚታወቀው የአገራችንም ነባራዊ ሁኔታ ከድጡ ወደ ማጡ እየሆነ በመሄዱና  በተለይም በኦሮሚያ ክልል የሀጫሉን ሞት ተከትሎ በንፁኀን  ወገኖቻችን ላይ በማንነትንና በእምነትን  ላይ ያነጣጠረ የዘር ፍጅት  ተፈጽሙዋል::  ከዚህ ፍጅት  የተረፉትም   እልፎች እስካሁንም መጠጊያና መጠለያ አጥተው በየገዳማቱና መቃብር ቦታዎች  የሰቀቀን ሕይዎት  እየገፉ ይገኛሉ::

እነዚህን ሁኔታዎች ስናጤን   አገራችን ወዴት እየሄደች ነው? ብለን እንድንጠይቅ ያስገድዱናል:: ይህም ለብዙዎቻችን ብዠታን ፈጥሮብናል ፤ ሆኖም  አገራችን ኢትዮዮጵያ በነዚህና መሰል ምስቅልቅል ሁኔታዎች  ብትገኝም  ዝምታን አልመረጥንም! ይልቁንም በእልህና  በቁጭት ለአገራችን ህልውና መቀጠል የምንችለውን ሁሉ ለማድረግ ቆርጠን ተነስተናል::

በኦሮሚያ በተደረገው ማንነትንና እምነትን መሠረት የአደረገውን የአገዛዙ ባለሥልጣናትና የመሪው የብልፅግና  ፓርቲ አባላት እጅ መኖሩ  ነገሩን  የበለጠ ያወሳሰበው እንደሆነ ግልጽ ነው ፤ መንግሥት የዜጎችን ሰብዓዊ መብትና ደኅንነት ማስጠበቅ አለመቻሉ ዕውነት መንግሥት አለ ወይ? እንድንል ግፊት ከማሳደሩም ሌላ  የለውጥ እንቅስቅስቃሴው ግብ ምን እንደሆነ ለመገንዘብ አዳጋች አድርጎብናል::

በአዲስ አበባ ከንቲባ ኃላፊነት ሥልጣን በጠራራ ፀሐይ የመሬት ወረራ  እና የጋራ ቤቶች ቅሚያ መፈፀሙን ለሁሉም ገሃድ እየሆነ መምጣቱና ይህንን ቀድሞውኑ ያጋለጠውን የባልደራሱን መሪ እስክንድር ነጋን የነጃዋር ሚዛን ማስጠበቂያ በሚመስል መልኩ  ለእስር መዳረግ  የለውጥ አራማጁ ኀይል ስለ እውነተኛ ፍትሕ ማስፈን ያለን አመለካከት  በጥርጣሬ ውስጥ እንዲወድቅ ያደረገ ነው::  የእስክንድር ነጋና የዐሥራት ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች እስር ጠቅላይ ሚኒስትር  ዐቢይ “በቅድሚያ አጣርተን እንጂ አስረን አንመረምርም” ያሉትን ቃል ያለመጠበቃቸው ጉልህ ማሳያ ነው ፤  በዚህም አማራጭ  ሐሳቦች ይዘው  አመራሩን ስለሞገቱ  ብቻ ምንም ከወንጀል ጋር ተያያዠነት የሌላቸው ወገኖች አቶ እሰክንድር ነጋን ፣ አቶ ልደቱ አያሌውና ሌሎችም ያለአግባብ ለብዙ ጊዜ የሐሰት ክስ ሲያቀነባብሩ ክስ ሳይመሠረትባቸው በእስር ላይ ይህን ያክል ጊዜ መቆየታቸው አግባብ ነው ብለን ከቶውንም አናስብም።

ተጨማሪ ያንብቡ:  በልደታ ለአንድ ንግድ ቤት በካሬ ሜትር 71,770 ብር የመጫረቻ ዋጋ ቀረበ

አገዛዙ የትላንትናው ቅሪት እንደመሆኑ ፍትህን በተመሳሳይ አዛብተው  በአቶ ልደቱ ላይ እየተፈፀመ ያለው የተዛባ የፍትህ አፈፃፀም ሂደት በዋስትና ላይ እንደገና አዲስ ክስ ምስረታና በባልደራሱ መሪ አቶ እስክንድር ነጋ ላይ እንደ አንድ ብሔራዊ ክህደትና የሽብር ወንጀለኛ በርካታ ውስብስብ የሀሰት ክሶች መመስረታቸው አምባ ገነንትና ፍትህ መዛባት ገፁን ቀይሮ መቀጠሉን ዓለም አቀፍ ማሕበረሰብም ይሁን የኢትዬጵያ ሕዝብ የምር እንዲታዘብ አስችሎታል

ስለሆነም ከዚህ ቀደም በዋሽንግተን ዲሲ በተጠራው የተቃውሞ ሰልፉ ምክንያት የተመሠረተው ግብረኃይላችን የአገራችን ነባራዊ ሁኔታ አሳሳቢ እየሆነ በመምጣቱ አገዛዙ ትክክለኛውን መንግሥታዊ ኃላፊነት አለመወጣት ፣ ያለአግባብ የታሰሩ ሰላማዊ ዜጎች እንዲፈቱ ነገም በሌሎች ሰላማዊ ታጋዬች ተመሳሳይ የበል እርምጃዎች እንዳይወሰድ ማኅበረሰባችንን ይዘን  የተቃውሞ ድምፃችን ለማሰማት ለመቀጠል ፣ የአገሪቱን አንድነትና  ህልውና  የሚፈታተኑትን   ጽንፈኞችንና ሕወሓትን ለመቃወም   እንደዚሁም በጊዚያዊነት በየጊዜው ከሚነሱ ችግሮች ባሻገር በዘላቂነት የአገራችንን ችግር ለመፍታት  ኢትዬጵያ አንድነት ኃይሎች በአገራችን  ፍትሕንና ዲሞክራሲን እውን ለማድረግ ፣ ዘውገኝነትንና ተረኝነትን ታግሎ ለመጣል  አገራችንን  ከዚህ ማጥ ለማውጣት መጪውን ምርጫ ለማሸነፍ ለዚሁም የድሞክራሲ ተቋማት የሁሉም የአንድነት ኀይሎች የወል መገልገያ እስኪሆኑ ድረስ  አንድ ግንባር በመፍጠር እንዲታገሉ ተፅዕኖ ለመፍጠር  በሚደረገው ግብግብ ውስጥ የራሳችን  ሚና ለመጫወት  ቁርጥ ሐሳብ አድርገናል::  ለዚህም  የኢትዮጵያ አንድነት ተጠብቆ መዝለቅ የሚሻ  ሁሉ  ድጋፉን  እንዳይለየን አበክረን እናሳስባለን::  አገራችን ከዚህ ማጥ ውስጥ እንድትወጣ ዘርፈ ብዙ ሥራዎች ስለሚጠብቁን በዚህ ረገድ  ግብረኃይላችን  በውዴታ የወሰደውን ኀላፊነት ለመወጣት ሥራችንን በትጋት  የተያያዝነው መሆኑን ለወገናችን ስናበስር በደስታ ነው::

ሆኖም ይህ ግቡን ይመታ ዘንድ በመግቢያችን እንደገለፅነው በዓለም ዙሪያ በውጪ የሚገኘው ወገናችን የበይ ተመልካች ሳይሆን በማናቸውም ጥሪ ከጎናችን እንዲሆን ስንጠይቅ በተለይ አክቲቪስቶችና የኢትዮጵያ  ጉዳይ ያገባናል የምትሉ ስብስቦችና አገር ወዳድ ወገኖች በግብረኃይሉ ውስጥ ተሳትፎ በማድረግ ውጥናችን አንዲሳካ እንድታደርጉ ጥሪያችንን እናደርሳለን።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ገነት ደርሼ መጣሁ ያለው የጠገዴ ነዋሪ ሕዝቡን ሲያሸብር ዋለ

በሰሜን አሜሪካ ” የአገር አድን ግብረኃይል ” አስተባባሪ አካል!!

 

September 16,2020

 

 

4 Comments

  1. This is the way it should be! Stand together and move forward in order to stop the untold sufferings of the people and save the country from disintegration that will entail unimaginable blood shed !
    Thank you for saying truly ENOUGH is ENOUGH!

  2. How far will you take it? Are you willing to fight the whole establishment including abiy and his party? Or are you targetting just woyane and olf? If woyane and just olf are the targets, it will not bring about any change. Need to be more clear in that aspect. Whole heartdly support enough is enough if all enemies of Ethiopia and Ethiopians are included, that includes abiy and his party and the so called constitution.

  3. To advocate for Lidetu Ayalew means loosening your moral credibility and ground ,We do not forget how many young people died by Ethiopian calendar 97 election.

  4. This is the way it should be! Stand together and move forward in order to stop the untold sufferings of the people and save the country from disintegration that will entail unimaginable blood shed !
    Thank you for saying truly ENOUGH is ENOUGH!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንቷ ምን ነካቸው? |ሕብር ራዲዮ ዜና ትንታኔ

Next Story

መንበረ አክሊሉ – በጎ አድራጊ- አርትስ ወግ

Latest from ዜና

ልዕልት ሂሩት ደስታ ምን አይነት ሰው ነበሩ?

ከአንሙት ስዩም እስካሁን በኖርኩባቸው አመታት የተረዳሁትና የገባኝ አንድ ነገር አለ፡፡ በዝህብ ላይ መጥፎ ስራ የሰሩትን ወንጀለኞች ለፍርድና ለቅጣት የማቅረብና የማስፈረድ ልምድ ያለንን ያህል፤ መልካም ለሰሩት ግለሰቦች ግን ተመጣጣኝ የሆነ የስማቸው

Share