የውስጥ ጠላቱን ያላሸነፈ የውጭ ጠላቱን መቼም አያሸንፍም – ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

አንድ ጓደኛየ በከፍተኛ ብስጭት “መጀመሪያ መምታት ለግብጽም ሆነ ለሌሎች የውስጥም ሆኑ የውጭ የኢትዮጵያ ጠላቶች በገንዘብ ራሳቸውን ሸጠው እርስ በርስ የሚያበጣብጡንን እንትናን፣ እንትናንና እንትናን ነው!…” እያለ እንደሽሮ በንዴት ሲንተከተክ ከአፉ ቀለብ አድርጌ ይህችን አጭር ማስታወሻ ጻፍኩ፡፡ እርሱ የሰዎቹን ስም እየጠራ ነበር የሚንፈቀፈቀው፡፡ እኔ ግን “ጃፋር፣ ገርቡና ልቀቱ” እያልኩ እንደሱ ስም በመጥራት በስም ማጥፋት ወይም በግድያ ዛቻ መከሰስ ስለማልፈልግ  ስማቸውን በሆድ ይፍጀው ተውኩት፡፡

እርግጥ ነው፡፡ ማንም ወገን የውስጥ ጠላቱን ለይቶ ካላስወገደ ምንም ዓይነት ውጊያ አያሸንፍም፤ በልማትም ሆነ በሥልጣኔ ስንዝርም ብትሆን ሊጓዝ አይችልም፡፡ ማስወገድ ሲባል ለኢትዮጵያዊ ቀድሞ የሚታየው መግደል ሊሆን ይችላል፤ ይህም የሚሆነው የብዙዎቻችን አስተዳደግ ከግድያና ከጠበንጃ ጋር ብዙ ቁርኝት ስላለው ይሆናል፤ በጨዋነት ተነጋግሮ በሃሳብ ልዩነት መሸናነፍ ብርቃችን በመሆኑም ሊሆን ይችላል፡፡ በሰለጠነ ዓለም ግን ግድያ ምርጫ ውስጥ ሊገባ የማይገባው ምናልባትም ከገባ በመጨረሻ የሚመጣ ነው፡፡

ስለሆነም ጓደኛየ የጠቀሳቸውን የመሰሉ የሀገራችን ጠላቶች ዋናው መለየታቸው እንጂ የአወጋገዳቸው ጉዳይ ብዙም ከባድ አይሆንም፡፡ እነሱን መምከር፣ መገሰጽ፣ ማስመከርና በዚህ አልመለስ ካሉ ህግን ተከትሎ በሀገር ክህደት ወንጀል በመክሰስ የሚገባቸውን ቅጣት በትክክለኛ የፍርድ ሂደት ማስበየን ነው፡፡ እፍኝ የማይሞሉ ሰዎች ሆድ እምብርት ባጣ ቁጥር፣ የጥቂት አጋሰሶች ቁሣዊ ፍላጎት ለከት ባጣ ቁጥር ሀገር ልክ እንዳሁኑ በቁሟ እንጦርጦስ መውረድ የለባትም፡፡ እነሱን ሁልጊዜ እያባበሉና እሹሩሩ እያሉ የፈለጉትን እንዲያደርጉ መፍቀድ ደግሞ ከነሱ እንደ አንዱ መሆን አለዚያም በአንድ ወይ በሌላ መንገድ እነሱንና በጠማማ መንገድ ተጉዘው ያገኙትን ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ተፅዕኖ  መፍራት ነው፡፡  ከነሱ እንደ አንዱ ሆነን ወይም ፈርተን ደግሞ እንዲሁ በማስመሰል ብቻ  ይህችን ኢትዮጵያ ከገባችበት ማጥ ማውጣት አንችልም – በጭራሽ፡፡ ድካማችን ሁሉ በዜሮ እየተባዛ ከንቱ እንቀራለን እንጅ ሰላም፣ ዕድገትና ብልጽግና ዕንቁልልጭ ናቸው፡፡ የምንችለው ሀገራችንን ይበልጥ ቅርቃር ውስጥ መክተትና የነፃነቷን ቀን ማራቅ ነው፤ ሁለት ተሸናፊዎች ደግሞ አንድ የሁሉም ሊሆን የሚችልና የሚገባው ድል ሊያስመዝግቡ አይችሉም (መንግሥትና ከሃዲዎች እየተፈራሩ ቢጓዙ ሁሉም ተሸናፊ መሆናቸው ግልጽ ነው፡፡) ጠላትህን እጉያህ ወትፈህ፣ ከዚያም ባለፈ በዘረኝነት አረንቋ ገብተህም ይሁን የድንቁርና ሰለባ ሆነህ  ለጠላትህ የሽፋን ተኩስ እየሰጠህ፣ “አገር፣አገር” ብትል “ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ” ዓይነት ራስን የማታለል ቂልነት ነው፡፡ በቃ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአፍሪካ ቀንድ ጅኦ-ፖለቲካል ሽኩቻና ውልደተ ውክልና ጦርነት!!! የውኃውን ቁልፉ እንጫነው? የትኛውን ፈረስ እንጫነው? ፋኖ በአማራ ክልል በቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማ ይጥራ!!!

እግዚአብሔርን የምለምነው ነገር አለኝ፡፡ እርሱም “ምንም የሚሣንህ ነገር የሌለህ አምላኬ ሆይ! ሀገራቸውንና ወገናቸውን ሸጠው በሚያገኙት ገንዘብ የተንደላቀቀ ሰይጣናዊ ኑሮ የሚኖሩ ብኩን ዜጎች በደም የተገዛ ኑሯቸው ኅሊናቸውን እየኮሰኮሰ የአእምሮ ዕረፍት ሲነሣቸው፣ በሀገር ሸያጭ ገንዘብ የሚበሉት ወፍራም እንጀራ ደም ደም እያለ ወይም እየመረረ አልዋጥ ሲላቸውና ከሆዳቸው ወደ ሕዝባቸው ሲመለሱ በዕድሜ ዘመኔ እንድታሳየኝ እማጸንሃለሁ፡፡

አሜን፡፡”

6 Comments

  1. ዳግማዊ ጉዱ ካሣ ሆይ! ለአቶ ሰመረ ከግርጌ የለጠፍኩት ለዚህ ለከፍተከው አጀንዳ ይመች ስለመሰለኝ አምጥቼዋለሁ (ከይቅርታ ጋር)። በመጀመርያ በ “አሜን እንደምኞትህ ያድርግልን ” ልጀምረው። የእለትም ጸሎቴ ስለሆነ። ዋናውን ሚስጢር አግኝተህዋል። የተኛህበት አልጋ እንደጋሬጣ እየወጋ እንደምንስ ያሸልባል እንኳንስ ሊተኛ? ሊታረቀን ነው መሰለኝ ፌዴራሌዎች እየከዱ ነው ህውሃትን። ይህ ከባድ የምስራች ነው። እነሆ ለአቶ ሰመረ የመለስኩት።
    ================
    አቶ ሰመረ፣ ሸብረክማ የሚያደርግ ብዙ ጉዳይ አለ። ዋንኛውና ፊታችን ተጋርጦ ያለው ህወሃት ነው “ምናባታቸው ያመጣሉ” ካላልን በቀር። ፌዴራሌዎቹም ይመስገነውና እስከትላንት ድረስ ህውሀት ጉያ ተሸጉጠው የነበረው እያፈተለኩ ነው። ይህ በእንዲህ እያለ አሁንም ጥቂት የበቀለ አይነት ቀላዋጮች ህወሃት እግር ስር ናቸው። ተቃዋሚ ይሁን ተጻራሪ ተብዬዎችማ ተኩስ አቁመው በአባይ ጉዳይ አገር ነቅንቅ እምቢኝን ቢያቀነቅኑ ግብጽስ እንዲህ ትዳፈረን ነበር በገዛ ውሃችን? ሌላው ያልተረዱኝ ነገር ትራምፕ ሆነ ባይደን የውስጥ ሰላምንና ጥንካሬያችንን ነው ቀድመው የሚገመግሙት በቀላጤዮቻቸው። አሁን ምን የሚያኮራ ውስጠ ሰላም አለንና ነው “ሙሌቱን ዝንፍ ሳንል በሃምሌ እንጀምረዋለን” የሚያስብል? ለዚህም ነው ዶር አቢይ እያስታመሙ እስከ አሜሪካ ምርጫ ያድርሱልን የምለው። ዋናው ጉዳይ የውስጥ ጥንካሬያችን ቢሆንም በግልጽ ለግብጽ ወግኖ በአሜሪካ ገንዘብ ሚር እጃችንን ለመጠምዘዝ የሚሞክረውን ቅሌታሙን ትራምፕ” ወግድ ወዲያ፣ የውሃችንን ሙሌት መጀመሩን የሚያስቆም ምንም ምድራዊ ሃይል የለም” ማለት ዋጋ እንዳያስከፍለን ከመስጋት ነው። ሌላው እርስዎ “ዘገምተኞች” ያሉዋቸው ዲፕሎማቶች ብቻ አይደሉም እየተፋለሙ ያሉት። ምርጥ አለምአቀፍ አንቱ የተባሉ ያገራችን ምሁራን ከጀርባ ዋልታና ማገር ያሉ ይመስለኛል በቪኦኤ እንደሰማሁት። ይህ የአባይ ጉዳይ ከጅምሩ ወያኔዎቹ ያግማሙትን ነው አቢይ ነፍስ እየዘሩበት ያለው። ምን ያረጋል ታድያ ። አሁንም ቢሆን መቀሌ መሽገውም መች ተኙላት ለዚች ምስኪን አገር? እንግዲህ ይህ ሁሉ እየሆነ የዚህን ሙሌት ጉዳይ ገፋ ማድረግ ብልህነት አይመስሎትም? አለበለዚያማ የኔው ቢጤ ወታደር ዛራፍ ማለቱ ተስኖኝ መስሎት? አያዋጣንምና ነው። እኔ ይልቅስ የምመኘው ይህን የአባይ ብሄራዊ ጉዳይ ከፍተኛ ቦታ ተሰቶት ፣ ምድረ ተቃዋሚ ሁሉ እስከከርሞ ምርጫ የሚባለውን ጉዳይ እርግፍ አርጎ ትቶ ስለ አባይ ብቻ ቢመክርና ቢዘክር ምናልባት ግብጽም እንዲህ አትፈንጭብንም፣ ሱዳንም ሸርተት አትልብንም ነበር። እናም እስቲ በመጀመርያ የውስጥ ወገኖቻችን በዚህ አባይ ጉዳይ በሙሉ ልብ ከጠቅላያችን ጋር ይቁሙ እስቲ። ወያኔዎቹን ሁሉ ተማልጄ ነበር ለህሊናዬ። አሁንም አልመሸም። ልክ አብላጫው ፌዴራሌዎች ህውሃትን እንደከዱ ሁሉ የቀሩትም ቢያደርጉት ትልቅ እርምጃ ነው። ሙሌቱ አይቀር እንደሆን። ወቅቱ ግን ለኛ አመቺ አይደለም ለማለት ነው። ያገራችን ተቃዋሚዎች ምናለ ከኤርትራ ተቃዋሚዎች ቢማሩ እላለሁ አንዳንዴ። ኤርትራውያን ድንቅነታቸው የሚገርመኝ ኢሳያስን እየጠሉ እንኳ በአገራቸው ጉዳይ የሚያስደምም ህብረት ይፈጥራሉ። ባለፈው ለህዝባቸው ገንዘብ ሲያሰባስቡ እንኳ በሁለት ሳምንት 3 ሚሊዮን ዶላር ከአሜሪካ ብቻ ያዋጡ ጀግኖች ናቸው። ለህዝባቸው ሲቆረቆሩ ኢሳያስን አይደለም የሚያዩት ወገናቸውን እንጂ። ባለፈው አመት ያንን ሁሉ ህዝብ ይዘን ለዲያስፖራው ፈንድ ያዋጣናት ሁለት ሚሊዮን እንኳ አልደረሰም። ይቅርታ ያድርጉልኝ ኢትዮጵያውያን ባብላጫው ወሬኞች ነን። ክፉዎችም ጭምር ። ወያኔዎቹ ደግሞ ከክፋትም በላይ ናቸው። ፈጣሪ ምህረቱን ያውርድልን ብቻ።

  2. Teaching the usual muslim teachings as we always did thought the teachings is our right , we Ethiopian Muslims shouldn’t be forced to change our teachings just because mosques are closed now due to Covid-19 and we resorted to public medias to transmit the Muslim teachings for all to hear it in Ethiopia , saying it on public media’s doesn’t necessarily make what we teach wrong. These media modems shouldn’t stop Muslim teachers from teaching our teachings the way we always had been teaching it while mosques were open. Those Orthodox Christians who don’t like our Muslim teachings should not listen to our Muslim teachings , we are teaching it to our members . Same as you don’t step into mosques in the previous years , now you shouldn’t listen to Muslims teachings if you are not a Muslim person , but if you choose to listen to muslim teaching while not being a Muslim it is not Muslims fault if you hear something you don’t agree with or that might offend you , because we are going to teach it the way we thought it in previous years, we will not change our regular teachings just because now it is thought on a public media.

    Borkena › 2020/05/15 › inter-religi…
    Web results
    Inter-Religious Council of Ethiopia Passes a Decision over Remarks of … – Borkena

  3. በሰዉ አእምሮ ያገራችን ጉዳይ ይህን ይመስላል ቤት ማስተዳደር የማይችሉ ጁዋርን የመሳሰሉ ባስተሳስብ የተጎዱ አለም አቀፍ ሚዲያ ላይ ኢትዮጵያዊ አይደለሁም ክርስቲያንን በቆንጮራ ቀንጥሱ ብለዉ የነገሩን ዛሬ በሺመልስ አብዲሳ ሆነ በሌላዉ እኛ እያለን ጁዋርን ማን ይነካዋል እያሉ ያስፈራሩናል። ወ/ት ብርቱካንም ሞክራ ነበር ታክቲካዊ ማፈግፈግ አደረች መሰል። ጁዋር ኢትዮጵያ ፖለቲካ ዉስጥ እንዲሳተፍ ከተፈቀደለት ጆንሰን ካሜሪካ ሂዶ መወዳደር ምን ያግደዋል ሁለቱም የዉጭ ሰዎች ናቸዉና።
    በተረፈ በእኔ በኩል ባለፈዉ እንዳልኩት ሐይለ ማርያም ደሳለኝ እንዲህ ያለ ዘመን ተሻጋሪ ዉል ላይ መላኩ ዉሉ እንዳይሳካ ከማሰብ ካልሆነ በስተቀር ጥቅሙ አይታየኝም። ሰዉየዉ ታሪኩ ሲመረመር የሚገርም ነዉ በብስጭት ከዚህ በላይ እንዳልሄድ ቤተ ሰብ አለዉ። ሀገሬ ላይ የመለስ ጉዳይ አስፈጻሚ ሁኖ የሰራዉ ግን የሚረሳ አይደለም። ጉዱ ካሳ እንዳለዉ እነዚህ አገር አፍራሾችና በታኞችንን ቀፍድዶ ቢያስር አንድ ሰሞን አራግበን አገር ሰላም ይሆናል ሌላዉም አርፎ ይቀመጣል። መራራ ጉዲና፤ብርሀኑ ነጋ፤ጁዋር መሀመድ ፤አረጋዊ በርሄ ፤ዳዉድ ኢብሳ ፤በቀለ ገርባ፤ሌንጮዎችና በተለያየ ምክንያት ሆን ብዬ ስማቸዉን ያላነሳሗቸዉን ሰዎች ቦታ የማይሸፍን ኢትዮጵያዊ ከየትኛዉም የኢትዮጵያ አካባቢ ይኖራል ብዬ በሙሉ አፍ መናገር እችላለሁ። ምን ይሰራሉ? ጡረታስ የሚወጡት መች ነዉ?
    ኦሮሚያስ ሰዉ ጠፍቶ ነዉ እንደ ሺመልስ አብዲሳ እንዲመራዉ የተሰጠዉ ይህስ የኦሮሞን ነገድ መስደብ አይሆንም? በዚህ ሁኔታ እንኳን ድምበር አስከብረን ሀገር አረጋግተን አባይን የእኛ ለማድረግ ይቅርና ስድስት ወር ለኢትዮጵያ መቆየት ዋስትና የሚሰጥ አይኖርም። ክልላዉያንም እንደ በሬዉ ክልል ክልላቸሁን ስታዩ ከአገር በፊት እናንተ እንደምትፈርሱ መረዳት ከባድ አይሆንም። ለማንኛዉም ለሀገር ተቆርቁራችሁ በአቅማችሁ የተኛዉን ለማንቃት ለምታበረታቱ ኢትዮጵያን ክብር ለናንተ ይሁን። እንግዲህ የእግዚሀሩንም አንርሳ ሁልጊዜ ለኢትዮጵያ ተአምራዊ ደህንነት ይኖረዋል። እስቲ በያላችሁበት አገር የኮንግረስ ሰዎችን ጋዜጠኞችን ለመድረስ ሞክሩ። ያሳዝናል የአንድነት ሀይሉ አገሩን እንደሚወድ ግልጽ ነዉ ሀይል አስተባብሮ ቁም ነገር ግን አይሰራም። የተናጥል ትግል የትም አያደርስም።
    አምላክ ኢትዮጵያን ይጠብቅ

  4. ጎበዝ በኢትዮጵያ አምላክ ተመልከቱት ትግሬዎች ያስቀመጡልን የኢትዮጵያ መሪ ሐይለ መለስ ደሳለኝን ht ጎበዝ የኢትዮጵያ አምላክ ጠብቆን ነዉ እንጂ ከዚህም በታች ቁልቁል መዉረድ ነበረብን። ተቀልዶብናል እግዚኦ ምን ብንበደል ነዉ ግን እንዲህ አይነት ሰዉ ኢትዮጵያን አስተዳድር ተብሎ የተሰጠዉ አስተዳዳሪዉ በረከት ስሞን ቢሆንም አሳዛኝ ነገር ነዉ የተፈጸመዉ።

  5. በቦርድ አመራሮች ውዝግብ ሳቢያ የዳያስፖራ ትረስት ፈንድ ህልውና አደጋ ውስጥ መውደቁ ተሰማ::.

  6. ስለ ሐ/ማርያም ከላይ የጻፍኩት ላይ ሐይለ ማርያም ከቲም ሰባስቲያን ጋር ያደረገዉ ቀለ ምልልስ አስፈንጣሪዉ ተቀንሶብኛል እባካችሁ አዉጡት ማንንም ሳይጎዳ ወገንን ያነቃል እንዲህ ያለ አስነዋሪ ሰዉ ነዉ ኢትዮጵያን ወክሎ አባይን የኢትዮጵያ ያደርጋል ተብሎ በአብይ አህመድ የተካተተዉ ።https://www.youtube.com/watch?v=JNVtk8777mY

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share