March 17, 2013
14 mins read

“ልጄ በእሳት ተቃጥላ እንድትሞት ተደርጋ፣ ቤቴን ተነጥቄና ንብረቴ ወድሞ ከሀረር ተባረርኩ” – የ67 አመቷ እናት

“ልጄ በእሳት ተቃጥላ እንድትሞት ተደርጋ፣ ቤቴን ተነጥቄና ንብረቴ ወድሞ ከሀረር ተባረርኩ” ሲሉ አንዲት የ67 አመት ባልቴት በተለይ ለፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ አስታወቁ፡፡ ወ/ሮ ኢትዮጵያ ይልማ የሚባሉት እኚሁ  እናት የ75 ዓመት አዛውንት የሆኑት ባለቤታቸውም እንደ እሳቸው ሁሉ ጎዳና ላይ መውደቃቸውን ለፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ዘጋቢ  ከዕንባቸው ጋር እየታገሉ አስረድተዋል፡፡

“በሐረር ከተማ ቀበሌ 17 ውስጥ ከ30  ዓመት በላይ ኖሬ፤ ሀብትና ንብረት አድርቼ እኖር ነበር አሁን ግን በአካባቢው እንዳልኖር ተደርጌያለሁ” የሚሉት ወ/ሮ ኢትዮጵያ ይልማ “ከ30 ዓመት በላይ የኖርኩበትን ቤቴን የወረዳው አስተዳዳሪ እና የወረዳው ፓሊስ አዛዥ አስጠርተው ቤትሽን ለወ/ሮ አኒሳ መሐመድ ሸጠሽ ግቢውን እንድታስረክቢያት አሉኝ፡፡ እኔ ቤቴን የመሸጥ ሐሳብ የለኝም፡፡ ቤቴን ሸጪ የት እወድቃለሁ? አልሸጥም አልኳቸው እንቢ ካልሽ ከአገራችን እናባርራሻለን በገንዘብ አልሸጥም ካልሽ በባዶሽ ተባረሽ ወደ አገርሽ ትሄጃለሽ አሉኝ፡፡ እኔ ሌላ አገር የለኝም የምሄድበትም ቦታ የለኝም መንግስት ባለበት አገር ቤትሽን ተቀምተሽ ውጪ የሚለኝ የለም ብዬአቸው ተመለስኩኝ” በማለት የችግሩ መነሻ ነው ያሉትን ጉዳይ ወደኋላ መለስ ብለው ያስረዳሉ፡፡ ጎስቋላዋ የ67 ዓመት ባልቴት በመቀጠልም “በማግስቱ እኔ ቡና አፍልቼ፣ ባለቤቴም ጫማውን አውልቆ ፍራሽ ላይ አረፍ ብሎአል፤ አንድ ፓሊስ በሩን በሰደፍ እና በእርግጫ መቶት በሩን በረገደው፡፡ ምንድነው? ብለን ስንወጣ ከ30 በላይ ፓሊሶች ቤታችንን ከበውታል፡፡ ይህች ናት፡፡ ነይ ውጭ! ብሎ ለሁለት ሶስት ሆነው ጎተቱኝ፡፡ እባካችሁ ምን አደረኩ ብዬ ስለምናቸው አንቺ ለህግ አልገዛ ያልሽ አመጸኛ ነሽ! ወንጀለኛ ነሽ እያሉ መሬት ለመሬት ጎተቱኝ፡፡ እባካችሁ ምንም የሰራሁት ወንጀል የለም ብዬ ጮኩኝ፡፡ ጎረቤት ተሰበሰበ ምንድነው ብሎ ጠየቀ ማንም ምላሽ አልሰጠም” የሚሉት ወ/ሮ ኢትዮጵያ ይልማ ሟች ልጃቸውን በሀዘን ተውጠው እያስታወሱ ይቀጥላሉ “ልጄ ባል አግብታ የምትኖረው ሌላ ቦታ ነው፡፡ ቀን ቀን ምግብ እየሰራች ትሸጣለች ፓሊሶች እናትሽን ከበው እየደበደቡ ናቸው ብሎ ጎረቤት ሲደውልላት ሮጣ መጣች፡፡ ደርሳ ምን አድርጋ ነው ብላ ብትጠይቅ ቤቱን አስረክቢ ስትባል እንቢ ብላ ነው አሏት፡፡ የተወለድንበትና ያደግንበትን ቤት ከህግ ውጭ እንዴት እንነጠቃለን ብላ ስትጮህ ጥላው ሄዱ” በማለት በለቅሶ ያስረዳሉ፡፡

ወ/ሮ ኢትዮጵያ ይልማ በመቀጠልም “ያንለቱኑ ማታ ልጄ ምግብ የምትሸጥበት ቦታ ሁለት ሰዎች ተመጋቢ መስለው ከገቡ በኋላ (ረመዳን የተባለ ፓሊስና እንዳለ ወ/ሮ ኢትዮጵያ ይልማ(ከሀረር ጠሰብአዊ መብት ጥሰት ተፈፅሞባቸው የተባረሩ አዛውንት) ግርማ የተባለ ወጣት) ቤቱን አስረክቡ ስትባሉ አናስረክብም የምትሉት ለምንድነው ብለው ረመዳን ልብሷና ሰውነቷ ላይ ጋዝ ሲደፋባት እንዳለ ግርማ የተባለው ላይተር ለኩሶ አቃጥለዋታል፡፡ ሳትሞት ሆስፒታል ደርሳ ነበር፡፡ በማግስቱ አዲስ አበባ አምጥቼ ላሳክም መኪና ተከራይቼ ይዤ ስወጣ ፓሊስ እዚህ ትታከም እንጂ ከሐረር አትወጣም ብሎ ከለከለኝ፡፡ እኔም ገንዘብ ካለኝ እንኳን አዲስ አበባ አሜርካን ወስጄ ባሳክም ለምን እከለከላለሁ ብዬ ብጮህ ባለቅስ ማንም ሊደርስልኝ አልቻለም፡፡ ልጄ ህክምና አጥታ ሞተች፡፡” ብለዋል፡፡ ባልቴቷ ከልጃቸው ሞት በኋላ የደረሰባቸውን በምሬት ያወጋሉ “እኔንም ከቤቴ አስወጥተው ቦታውን ሺጭላት ላሏት ሴት ሰጧት፡፡ አሁን ቦታዬ ላይ ፎቅ እየተገነባ ነው፡፡ እኔና ባለቤቴ ግን ጎዳና ተጣልን፡፡ የአካባቢው ህብረተሰብ አዋጥቶ የሰጠኝን 3ሺ ብር እንድ ፓሊስና አንድ ደላላ መጥተው ነጠቁኝ፡፡ ሐረር ውስጥ አደሬ ወይም ኦሮሞ ካልሆንክ አቤት የሚባልበት ቦታ የለም፡፡ አማራ ነው ከተባለ ሁሉም ባለስልጣን በደረሰበት ግፍና ስቃይ ይስቅበታል፡፡ በደርግ ጊዜ የሐረር ፓሊስ አዛዥ ትግሬ ነበር፤ የማረሚያ ቤት አዛዥም ትግሬ ነው፡፡ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ትግሬ ነው፡፡ ለምን ትግሬ ሆነ ያለ አንድም ሰው የለም፡፡ ዛሬ በሀረር በየትኛውም መስሪያ ቤት አማራ ባለስልጣን የለም፡፡ ባለቤቴ ኦሮሞ ነው፡፡ ልጆቼም ኦሮሞ ናቸው፡፡ እኔ አማራ በመሆኔ ብቻ ይህ ሁሉ ጉዳት ተፈጸመብን፡፡” የሚሉ ወይዘሮዋ የተፈፀመባቸው የሰብአዊ መብት ጥሰት ዘራቸውን መሰረት ያደረገ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ አክለውም “አዲስ አበባ መጥቼ ለእንባ ጠባቃ ተቋም አመለከትኩኝ፡፡ ፌደራል እንባ ጠባቂ ተቋም እንዴት እንዲህ ይፈጸማል ብለው ይዘውኝ ሐረር ተመለሱ፡፡ የቤቴ ካሳ እንዲከፈለኝ ተወሰነልኝ፡፡ የክልሉ ባለስልጣናትም እሺ ይፈጸምሎታል ብለው ቃል ገቡልኝ፡፡ እንባ ጠባቂዎቹ ወደ አዲስ አበባ ተመልሱ፡፡ እነሱ ከተመለሱ በኋላ ግን ምንም መፍትሄ አልሰጡኝም፡፡ በድጋሚ አዲስ አበባ መጥቼ ለእንባ ጠባቂ ተቋም ባመለክት እነሱም ውሳኔያቸውን እንደ አጀማመራቸው ሊያስፈጽሙልኝ አልቻሉም፡፡ ጉዳዬንም ለመስማት ፍቃደኛ አልሆኑም፡፡” በማለት የበደላቸውን ስፋት ለፍኖተ ነፃነት ዘጋቢ በዝርዝር አስረድተዋል፡፡

“ዛሬ እኔ አዲስ አበባ ላይ ባለቤቴ ደግሞ ሐረር ላይ ጎዳና ላይ ነን፡፡ መፍትሔ ማግኘት አልቻልኩም” ሲሉ ተስፋ መቁረጥና ምሬት ተሞልተው በለቅሶ የመንግስት ያለህ … የህዝብ ያለህ በማለት ጥያቸውን ያቀርባሉ፡፡

የወ/ሮ ኢትዮጵያ ይልማን ጉዳይ አስመልክቶ የፌደራሉ እንባ ጠባቂ ተቋም ለሐረሪ ክልላዊ መንግስት ጸጥታ ቢሮ የጻፈውን ደብዳቤ እንደተመለከትነው ደብዳቤው ከዚህ በፊት ስለጉዳዩ ተጠይቆ መልስ አለመስጠቱን በማስታወስ አሁን በድጋሚ በ 15 ቀን ውስጥ መልስ እንዲሰጥ ያለበለዚያ በህግ በተሰጠው ስልጣን መሰረት አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ የሚገልጽ ነው፡፡ ሆኖም የእምባ ጠባቂ ተቋም ውሳኔ ባልቴቷንና ባለቤታቸውን ከጎዳና ተዳዳሪነት የሚታደግ አልሆነም፡፡ በጉዳዩ ላይ የፊደራል እንባ ጠባቂ ተቋም አስተያየት እንዲሰጥበት ወደ ተቋሙ ህዝብ ግንኙነት ክፍል በማምረት ባለሙያዎችንም አነጋግረን ነበር፡፡ በቅድሚያ ያነጋገርናቸው የህዝብ ግንኙነት ባለሞያ ጉዳዩን ከስሙንና በእጃችን ያለውን መረጃ ከተመለከቱ በኃላ ወደ ሌላው የህዝብ ግኑኝነት ባለሙያ መሩን፡፡እሳቸውም በተመሳሳይ ሁኔታ ማስረጃችንን ከተመለከቱ በኃላ ይህንን ጉዳይ የሚያውቁት ዋና አማካሪው አቶ ቀነአ ሶና ናቸው፡፤ እሳቸውን አነጋግሩ አሉን፡፡ አቶ ቀነአን በወቅቱ ማግኘት አላቻልንም፡፡ በሌላ ጊዜ ተመልሰን ቢሮአቸው ያሉትን የተቋሙን ሰራተኛ አቶ ቀነአን እንደምንፈልግ አስረዳናቸው፤ አቶ ቀነአን ወደ መስክ ወጥተዋል፡፡ ሰሞኑን ቢሮ አይገቡም አሉን፡፡ በዚህ ምክንያት የፌደራሉን እንባ ጠባቂ ተቋም አስተያየት ማካተት አልቻልንም፡፡ ጉዳዩ ተከቷል ወደ ተባለለት ወረዳ ፖሊስ ደወልን የሐኪም ወረዳ ፖሊስ ወንጀል መከላከል ሀላፊ የሆኑትን ሳጂን ተሾመ ሰይፉን አግኝተናቸዋል፡፡ ወ/ሮ ኢትዮጵያ ይልማ ደረሰብኝ የሚሉትን በደል ወቅቱን ጠቅሰንም አስረድተናቸዋል፡፡ ሆኖም ሳጂን ተሾመ ሲመልሱ ‹‹እኛ ፖሊሶች በየሁለት ዓመቱ እንቀያየራለን፡፡ አሁን በዚህ ወረዳ ያለነው ከሁለት ዓመት ወዲህ ተዛውረን የመጣን ነን፡፡ ስለዚህ ጉዳይ የሚያውቅ ሰው የለም፡፡ በአሁኑ ወቅት በወረዳችን ሮመዳን የሚባል ፖሊስ የለም፡፡ ምናልባት የወረዳው መስተዳድር የሚያውቁት ነገር ካለ እነሱን ብትጠይቁ ይላል፡፡›› በማለት መልሰውልናል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ያሉትን የወረዳውን አስተዳዳሪ አቶ ኢስማኤልንም ስለጉዳዩ ጠይቀን በሰጡን መልስ ‹‹እኔ በቅርብ ጊዜ ነው የመጣሁት ስለዚህ ጉዳይ የማውቀው ነገር የለም፡፡ የሚያውቁት ነገር ካለ ከእኔ በፊት የነበሩትን ጠይቋቸው›› ብለውናል፡፡ ከእሳቸው በፊት የወረዳው አስተዳዳሪ የነበሩትን አቶ ጀማል አህመድን አፈላልገን ጠየቅናቸው፡፡ “እኔ ድርጊቱ ተፈፀመ በምትለኝ ወቅት እዚያ ወረዳ አልሄድኩም፡፡ ስለዚህ ጉዳይ የማውቀው ነገር የለም፡፡ ከእኔ በፊት የነበረውን ሰው አፈላልጋችሁ ጠይቁ ብለውናል፡፡” ከእሳቸው በፊት የነበሩትን አስተዳዳሪ ማንነትና አድራሻ ማግኘት ባለመቻላችን ዜናውን በተገቢው ሁኔታ ሚዛናዊ ማድረግ አልቻልንም፡፡

ምንጭ፡ ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ከአዲስ አበባ

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop