አማራውን እያጠፋ ያለው ራሱ አማራው ነው! – ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

እንደመግቢያ – “ሰድበህ ለሰዳቢ አትስጠን” የምትሉኝን ‹አማሮች› ምንም ልረዳችሁ አልችልም – ከማዘን በስተቀር፡፡ አማራ እጅግ ሰፊ ሕዝብ ሆኖ ሲያበቃ ለዚህ የተዋራጅነት ደረጃ ያበቃው ከውስጡ የፈለቁ የገዛ ሆዳምና ማይም ልጆቹና በዚህ ግዙፍ ማኅበረሰብ ዘንድ የነበሩና ያሉ ሃይማኖታዊ ልምዶች እንዲሁም ሥረ መሠረታቸው ድህነት ሊሆን የሚችል የምቀኝነትና የመጠራጠር፣ የቂም በቀለኝነትና የመሠሪነት ጎጂ ልማዶች ናቸው፡፡ እነዚህን መካድ ለለውጥ በር ባለመክፈት በነበሩበት መንቦራጨቅን መውደድ ነው፡፡ እውነትን ተናግሮ እመሸበት ማደር ብዙም አያከስርም፡፡ በገዛ አካባቢው ሠርቶ የሚያልፍለት አማራ ካለ የሎተሪ ያህል ነው፡፡ እናም ይህን ሕዝብ ቀይደው የያዙትን እሾሆች ለመንቀል ትግሉ መጀመር ያለበት ከውጭ ሣይሆን ከቤት ነው፡፡ ማስመሰልና ባለፈ ታሪክ ብቻ መኩራራትም ይቅር፡፡ ኩራት እራት አይሆንም፡፡ ታሪክም ዳቦ አይገዛም፡፡አዜብ ጎላ፣ ገነት ዘውዴ፣ ሙሉጌታ አሥራት፣ ብርሃኑ ዳምጤ (አባ መላ)፣ ክፍሌ ወዳጆ፣ ሰሎሞን ተካልኝ… አማሮች ነበሩ፡፡ የሚያለቅሱት ግን በቅንድባሙ መሪ ፍቅር ወድቀው ነው፡፡

በወያኔ ዘመን – በጣም በቅርቡ – ከትምህርት ጋር ለሚገናኝ የመስክ ሥራ በአማራው ክልል እዘዋወር ነበር፡፡ያኔ የታዘብኩት ነገር አማራነትን ያስጠላል፡፡ የመንግሥት ሠራተኞች በተለይም መለዮ ለባሾች ትምህርት እንዲማሩ አይፈቀድላቸውም፡፡ ሲማሩ ቢገኙ ይቀጣሉ ወይም የሥራ ቦታ ዝውውር ይደረግባቸዋል፡፡ በርቀት ትምህርት በድብቅ የሚማሩ ፖሊሶች እንደ እስላም ሴት ከእግር ጥፍር እስከራስ ፀጉር በሂጃብ ተሸፋፍነው ፈተና ሲወስዱ ታዝቤያለሁ፡፡ ዋናዎቹ ባለሥልጣናት ግን በፈለጉት የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት የርቀት ትምህርት ማዕከላት እንደሚማሩና በድግሪ እንደሚንበሸበሹ ተረድቻለሁ – በፎርጅድ ዲግሪ ጭምር፡፡ ይህ የሚያሳየን ምቀኝነት በአማራው አካባቢ ተወልዶና አድጎ ለወግ ለማዕረግም ደርሶ ወደ ሌሎች ክልሎች ኢክስፖርት የተደረገ መሆኑን ነው፡፡ በዚህ ጠባያችን ደግሞ አይደለም ከሦስት ሚሊዮን ሕዝብ የወጣው ወያኔ ከ20 ሽህ ገደማ ሕዝብ የሚወጣው አርጎቤም በሉት ሙርሲ እንደብረት ቀጥቅጦ እንደሰም አቅልጦ ይገዛናል፡፡ በነገራችን ላይ በዚያን ወቅት ትግሬና ኦሮሞ ፖሊስም ሆነ ሌላ ሠራተኛ ተደብቆ ሳይሆን በግዳጅ ነበር እንዲማር የሚደረገው፡፡ አማራን ለማደደብና ለማደህየት በውጤቱም እንደከብት ለመንዳትና እንደመጋጃ ለመጫን የተሄደው ርቀትና የተሠራው ሸፍጥ ይዘገንናል፡፡ አማራውም በኢትዮጵያዊነት ካባ ተጀቡኖ ዕልቂቱን ይጠባበቅ ይዟል፡፡ አማራው ሁለት ምርጫ አለው –  የተጠቀሱትን የገዛ ችግሮቹን ቀርፎ በአማራነቱ በመታገል ራሱን ከተደገሰለት ዕልቂት ማዳን ወይም በኢትዮጵያዊነቱ ሌሎችንም አስተባብሮ ከታሪካዊ የሀገራችን የእጅ አዙር ጠላቶቹ ጋር በመታገል የታላቋን ኢትዮጵያ ትንሣኤ ማብሰር፡፡…

ተጨማሪ ያንብቡ:  እኛና አ መላ   (ገበየሁ ባልቻ)

ከፍ ሲል በተጠቀሰው መልክ ደንቁሮ የቀረ ዜጋ ከመሬት ተነስቶ “አፄ ቴዎድሮስ ተብሎ የተተነበየው ለኔ ነው” ቢል ማንም ሊፈርደበት አይገባም፡፡ ብአዴን የምን ስብስብ እንደሆነ በግልጽ እያየን ነው፡፡ ሰው የለውም ፡፡ እውነተኛው ልጅ እየተጣለ የእንግዴ ልጁ እያደገ ሀገራችን ለይቶላት የከብቶች በረት ሆነች፡፡ ትምህርት ከጠፋ ሆድ ይነግሣል፡፡ አእምሮ ከጫጫ ጉልበት ይገናል፡፡ ተናግሮ ማሳመን ዕርም ከሆነ ኃይል ህግ ይሆናል፡፡ “Mighty is Right.” ብሏልና የቀደመው ፈረንሣዊ ንጉሥ ናፖሊዮን (አንደኛው)፡፡

በዶክተር አቢይ የሰባተኛ ንጉሥነት (ለእውነት የቀረበ) እማዊ ትንቢት ተደንቀን ሳናበቃ አሁን ደግሞ አንድ የብል(ፅ)ግና ፓርቲ የአማራው አካባቢ ሹም ቴዎድሮስ የተባለው ንጉሥ እርሱ እንደሆነ ቅንጣት ሳያፍር መናገሩን ሰማን፡፡ ወዴት እየሄድን እንደሆነ ለማወቅ ቸገረኝ፡፡ ሀገር ሲያረጅ ጃርት ማፍራቱ በግልጽ እየታየኝ ዙሪያው ገደል ሆነብኝና መሄጃ አጣሁ፡፡ እውነት እንኳን ቢሆን ምናለበት ዝም ቢልና ሣቃችንን ባያስጨርሰን? ወይ ብአዴን! እዚያ ውስጥ ያሉ አብዛኞቹን ካድሬዎችና ባለሥልጣናት ፕሮፋይልና የስብዕና ልኬት ብናጠና ብዙ ጉድ መዘርገፉ አይቀርም፡፡ ኤቢሲዲንና ሀሁን ከመለየት አንጻር ያለውን ገመና ትተን ሌላ ሌላውን ነውራቸውን ብናስተውል በድንጋጤ ገደል እንገባለን፡፡ በነገራችን ላይ ብልጽግና ፓርቲ የአለቆቹን ዓርማ ማክበሩን በአግራሞት እየተከታተልን ነው፡፡ ኢትዮጵያን ስለመጠየፉ የሚወራውን ግን ብዙም አልገዛውም፡፡ እርግጥ ነው – ኢትዮጵያ የፍየል ሥጋ የሆነችባቸው ሰዎች የሚሰባሰቡበት ፓርቲ ኢትዮጵያን በበጎ የሚያወሳ ነገር ሁሉ ስለሚያንዘፈዝፋቸው በዚያ ፓርቲ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ የሚሸት ነገር እንዲወገድ ቢደረግ ሰዎችን ለማስደሰት ታስቦ መሆኑ አይካድም፡፡ ለነገሩ ካዋጣቸው ይግፉበት፡፡ ግን የሚያዋጣቸው አይመስለኝም፡፡

እንደመውጫ – በወያኔ ግፍና በደል የደረሰባችሁ ወገኖቻችን በተሠራባችሁ ነውር ምክንያት አንገታችሁን አትድፉ፡፡ ወዳችሁ ባልገባችሁበትና ፈቅዳችሁ ባልሆናችሁት ማንነትና ነውር እየተሸማቀቃችሁ ከመኖር ወያኔን እያጋለጣችሁ በአዲስ መንፈስ ታገሉ፡፡ አንገታችሁን መድፋት ይቅር፡፡ ነውሩ በነሱ እንጂ በናንተ አይደለምና፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የማናንስ ህዝብ ሆነን: ሳለን ሆሎዶሞር! የስታሊን ፍሬ! -ገለታው ዘለቀ

ጆሮ ያላችሁ የመንግሥት ባለሥልጣናት ካላችሁ በአዲሱ ቀረጥ ሳቢያ አገርና ሕዝብ እየተተረማመሱ ነውና ጉዳዩን እንደገና ተመልከቱት፡፡ ማንን እያስተዳድራችሁ እንደሆነ ዕወቁ፡፡ለአንድ መቶኛ ሀብታም ስትሉ 99 መቶኛውን ድሃ ሕዝብ አትፍረዱበት፤ በኑሮ ውድነት ጨንገር አትቅጡት፡፡ ሌላውን ነገ ስንገናኝ፡፡

 

4 Comments

 1. በዲሞፍተር ጥይትኘ አናት የሚያፈርስ ይላል ያገሬ ሰው ሲገጥም፡፡ዲሞፍተርን ምን አመጣው ካልከኝ የዘረዘርካቸውን ገራሚ እውነታወች ኢላማን አልሞ ከምታት ጋር ስለሚመሳሰልብኝ ነው፡፡የሚገርምህ ይሄንን ሀሳብ በቅርቡ 4 ኪሎ ግንፍሌ አካባቢ በሚገኘው የአብን ጽ/ቤት ውስጥ በነበረን የአመራሮች ስብሰባ አቅርቤው ነበር፡፡ነገር ግን ማንም ችግሩን መስማት ስለማይፈልግ የገላመጡኝ በርካታወች ነበሩ፡ውስጣዊ ችግርንና ውስጣዊ ጠላትን አቅፎ ይዞ ከውጭ በሚወረወር የዛፍ ፍሬ እየተፈነከቱ ማለቃቀስ መሳቂያ ከመሆን አልፎ የሙትቻነት ምሳሌ ከመሆን አያድንም፡፡ብአዴን ያን ሁሉ ግፍ ሲፈፅም ኖሮ ዛሬም መሪህ እኔ ነኝ ሲለው ዝም የሚልን ህዝብ ፈጣሪ እንኳን ሊረዳው አይችልም፡፡ 1ጥይት ለመግዛት በሬ ከመሸጥ የማይመለስ ህዝብ ለጠላቶቹ ሲላክ በድንገት እጁ የገባለትን 5 ሚሊየን ጥይት ተንከባክቦ ለጠላት መልሶ ያስረከበበትን አጋጣሚ ስትመለከት ምቀኝነት ምን ያክል በደሙ እንደተዋሀደ ትረዳና ተስፋ ትቆርጣለህ፡፡ስለዚህ ዝም ብሎ ማየት ይሻላል፡፡አንተ ግን እድሜ ይስጥህ ፡፡

  • Thanks for the compliment dear “Pitohu”, and if you are willing we may have contacts for the same purpose of standing for our right(s). Here is my email – ma74085@gmail.com
   Let’s call a spade a spade, otherwise it gonna be a repetition of what has been done in the past millennia. We have to grow. We have to see inward to have positive change. We have to get out of the shackles we have been tied up with.
   Thanks Enqoqo too. The name you chose speaks much. Unless we take enqoqo and metere or koso, our illnesses will remain the source of our suffering.
   Dear Beza, I loved your words, but I wish you knew me and my interests. My livelihood is not based on insulting Amharas. Do not misinterpert my motive. My little fellow, I hope you must be very young, please focus on reading, reading, and reading. Try to widen your scope of observing things. Do not be over-judgmental. I write what I feel. I write in every subject when I see the need. I have been writing about almost all issues in our economic and political life. To write about the Amharas is not taboo; if I write about Tigray’s TPLF and Oromo’s OPDO, if I write about bad Tigrians and bad Oromos, why not about bad Amharas and bad ADP members? There is nothing untouchable.

 2. Many Amaras insult and demoralize others they find since mostly it is Amaras they find with other ethnicities staying away from them, other ethnicities were liberated by TPLF so it is Amara against Amara now, insulting demoralizing hating is the highlight of their existence they do it to whoever that got close enough to them with their children being at the forefront of all the attacks . Amara children get abused by their parents , by their priests , by their teachers , by their neighbors than any children in Ethiopia with the children not having any freedom privacy or self respect until they disassociate completely isolated from their tormentors .

  They want to prove they are the leaders of those they insult not knowing the ones constantly antagonized being made fun out of demoralized is waiting for a chance to take revenge by adding all the abuses together just like Abebe Gellaw did at ( the former PM Meles Zenawi the Addis Ababa Amaranized Tigre who supported ADP) at the G 20 meetings in Washington DC USA. Many Amaras that stay single for life are contemplating revenge, they are unable to move forward eventually to end up being mad killers , gays or other sorts of lunatics since they bottle up all the anger and release it all at once the best chance they get.

 3. Yes Amaras need to do house cleaning and get rid of the leaches no question about it. Amaras are not inherently jealous but are victims of their own innocence and trust of people of position. It has been the trend for 27 tears. They have to be supicious of the people in position and make them take responsibility, essentially make them pay.

Comments are closed.

Share