የለገሰ ሎሌ ገልብጦ ባርኔጣ፣
“ኢትዮጵያ ሱስ ናት!” እያለ ሲመጣ፣
እልል ብለህ ወጣህ ሙዝ እንዳየ ጦጣ፡፡
እግዜር ለሰዎች ልጅ አይምሮ የሰጠው፣
ያለፈን መርምሮ እንዲተነብይ ነው፡፡
ከሃያ አመት በላይ ኢትዮጵያን ያደማው፣
በሁለት ጀምበር ውስጥ እንዴት ሱስ ሆነችው?
ጆሮ ጠቢ ሆኖ ልጆቿን ያስበላ፣
ምን ዛር አስገድዶት ሱስ ያዘው ከጦቢያ?
ፊደሏን በላቲን ሙልጭ አርጎ ፍቆ፣
“ኢትዮጵያ ሱስ ናት!” አይኑን በጨው ታጥቦ፣
ጎጋውን መንጋውን የዋሁን ሰልሎ፡፡
ሙሴና እያሱ እያልክ የፈዘዝክ አማራ፣
ጎንደርም ተሰደድክ እንኳን ጉራ ፈርዳ!
ዳር ዳር የነበረው የርስትህ ወረራ፣
ይኸው ሥሩን ሰዶ አዲሳባ ገባ፣
አቢይ ለማ እያልክ ሱስህን ስጠጣ፡፡
መቼም የሱስ ልማድ መዘዙ ክፉ ነው፣
በጆሮ ጠቢዎች አንፍዞ እስከ ወዲያው፣
ራስህ ራሱን ከምድር ሊያጠፋው ነው፡፡
ሱስም ሥሩን ሳይሰድ በጊዜ ታከሙት፣
ይድናል ቀስ በቀስ ከልብ ከታገሉት፡፡
ስለዚህ አማራ “ሱስ” መጋት ተውና፣
ወኔና ነፍጥህን ታጠቅ እንደገና፣
የዚች ምድር ክብር ምንጮች ናቸውና፡፡
ይኸን ላለመስማት ጆሮህን ከወተፍህ፣
እንኳን ስፍር መጉደል ዘርህን ታጣለህ፡፡
በሱስ ጥንብዝ ብለህ ስዘፍን ስትጨፍር፣
“አብይ ሙሴ ነው የሚሸለም ኖቤል”፣
አራጅ አስታጠቀ ለሃያ ዘጠኝ ዙር፣
በል ደምህን ጨልጥ ወገንህ ሲመተር!
ልንመክር ልንዘክር በብዕር ስንለፋ፣
በሱስ ሰባኪዎች ዛሬም ጥለህ ተስፋ፣
ከቅዠት ያልነቃህ ሞኝና ተላላ፣
ወገን እያሳረድክ በል ሱስህን ጠጣ!
በላይነህ አባተ ([email protected])
መጀመርያ የካቲት ሁለት ሺ አስራ አንድ ዓ.ም.
እንደገና ታህሳስ ሁለት ሺ አስራ ሁለት ዓ.ም.