September 29, 2016
16 mins read

የአንድ ሕዝብ አንድ ሀገር ድርጅት ምንድን ነው? አንዱዓለም ተፈራ

አንዱዓለም ተፈራ – የእስከመቼ አዘጋጅ

ውድ ኢትዮጵያዊያን፤

በፈረንጆቹ አቆጣጠር Sep. 18, 2016 አንድ ኢሜል ደረሰኝ። ሁለት መዝገቦችን አባሪ አድርጎ ነበር፤ አረንጓዴ ብጫ ቀይ ባሸበረቀ ምልክት፤ አንድ ሀገር አንድ ሕዝብ ከሚል ድርጅት። ሁለቱን በየተራ አነበብኳቸው። ወዲያው የበለጠ ለመረዳት፤ ከተወሰኑ ጥያቄዎች ጋር መልስ ላኩላቸው። ድምጻቸው ጠፋ። ቀጥለው ከአንድ ሳምንት በኋላ፤ አሁንም የጀምላ፤ “ድረገጻችን እይ!” ጥሪ ላኩልኝ። “ምነው መልስ ነፈጋችሁኝ!” በማለት መለስኩላቸው። ቀጥለው፤ “ያንተን ኢሜል አለገኝንም” ሲሉ መለሱልኝ። እድሜ ለቴክኖሎጂው ምጥቀት፤ በቀኗ የላኳትን ኢሜል ወደነሱ መራኋት። አይጥ እንደዋጠች ድመት፤ ድምጻቸውን አጠፉ። በዚህ ጥርጣሬዬ ላይ፤ በቫይቨር አንድ ቡድን ተፈጥሮ፤ የዚያ አባል ተደርጌ፤ ስልኬ በቫይቨር መልዕክት ይጣድፍ ገባ። “እንዴ! ይሄ የምን ቡድን ነው? እኔንስ ማነው ከዚህ ያስገባኝ?” ብዬ ላክሁ። መልስ የለም። እንዲህ ከሆነ አልኩና፤ “በሉ ያስገባችሁኝ ከማላውቀው ቡድን ስለሆነ፤ ያስገባኸን ሰው፤ ስልኬን ሰርዝ።” በማለት ጻፍኩ። ወይነሱ! ጉዳያቸውም አልሆነ። ሳገላብጥ፤ ያስገባኝን ስልክ ቁጥር አገኘሁ። ብዙም ጥረት የሚጠይቅ አልነበረም። ያንን ቁጥር በመጻፍ፤ “አንተ ሰው ስሜን ሰርዝ አልኩ።” ወይ ፍንክች! የስልኩን ባለቤት ስም አግኝቼ፤ ስሙንና የስልክ ቁጥሩን በማስፈር፤ “አንተ ሰው የስልክ ቁጥሬን ከዚህ የቡድን መልዕክት አውጣው!” አልኩት። ይሄን ሁሉ ያደረግሁት፤ እንደኔ ሌሎችም ተመሳሳይ ችግር አጋጥሟቸው ይሆናልና፤ እኔ ጥዬ በቀላሉ ከመሄድ፤ ምንአልባት ሌሎችም ይታዘቡት ይሆናል በማለት ነበር። በመጨረሻ ይህ ስም የስልኩ ባለቤት ሳይሆን፤ ስልኩን ከሁለት ዓመት በፊት ያስረከበውና ዛሬ ሌላ ስልክ የያዘ ሰው ስም ነው። ማለትም፤ በድሮ ባለቤቱ ስም፤ አሁን ተጠቃሚ በመሆን የወሰደ የድብቅ ድርጅት ስልክ ነው። የት እየሄደ እንደሆነ ገምቱ!

ዋናው ነገር፤ ይህ የተቀነባበረ፤ የፀረ-ትግሉ ቡድን ስልታዊ እርምጃ ነው። እኔ ከብዙዎቹ በተለየ መንገድ፤ በኢትዮጵያ ሀገራችን እየገዛ ያለውን የትግሬዎች ቡድን በጣም አደንቃለሁ። ይህ የትግሬዎች ቡድን ዓላማውን በደንብ ያውቃል። ለዚህ ዓላማው የማያደርገው ነገር የለም። ከዚህ ዓላማው ደግሞ ፍንክች አይልም። ዓላምውም አማራውን ከምደረ ገፅ ማጥፋትና ኢትዮጵያን መበታተን፤ ከዚያም የትግራይን ሪፑብሊክ ማቋቋም ነው። ይህን ለማድረግ የማያውጠነጥነው ሴራ፤ የማይደርተው ነገር የለም። እናም ጎበዝ ነው። ይህ ቡድን ይህን ሠራ፤ ያንን ደገመ ቢባል ደንታው አይደለም። አንዳንዶቻችን ዛሬ ይሄን ሠራ፣ ነገ ያን ደገመ ማለቱን ትግል አድርገን ይዘነዋል። ይህ ወራሪ ቡድን ግን ይስቃል። እኛ ምን እያደረግን ነው? የዚህን የአማራን ዘር አጥፊና ፀረ-ኢትዮጵያ ቡድን ተግባር መዘርዘር ላይ ተወዝፈናል።

እኔ ለዚህ ለደረሰኝ ኢሜል መልስ ስሠጥ፤ አንድ ነገር ይዤ ነው። ማንኛውም የሕዝብ ወገን የሆነ ድርጅት ሲልክልኝ፤ ምንም እንኳ መርኀ-ግብሩ ፍፁም የማልወደውም ቢሆን፤ የሕዝብ አካል ነውና፤ በጠቅላላ ሀገራዊ ትግሉ ይታቀፍ ዘንድ፤ ወደ አንድ እንድንካተት በማለት ነበር። ከዚህ በፊት፤ በትግሉ ያሉ ድርጅቶች በአንድነት እንዲሰባሰቡ ብዙ ሙከራ አድርጌያለሁ። አልተሳካልኝም። አሁንም ይህን ወራሪ ፀረ-ኢትዮጵያ አጥፊ ቡድን በአንድነት እስካልተነሳንበት ድረስ፤ ትግሉ ይራዘማል። ወደ ዋናው መልዕክቴ ልመለስ። ይህ የተላከልኝ ኢሜል – ለብዙዎቻችሁ ተልኮላችኋል – ሀገር ወዳድ የሚመስልና፤ ከአማራው ክፍል የወጣ የሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎችን ታሪክ ያላካተተ ከመሆኑም በላይ፤ ሌሎች አማራውን እንዲጠሉ “ይሄው የአማራው አደረጃጀት!” በማለት ይህ የትግሬዎቹ ገዥ ቡድን ለቀመረው ማቃቃሪያ ዘዴው፤ መረጃ እንዲሆን ነው። እናም የኢሜሎችን አድራሻዎች ከየትም ሰብስቦ፤ የስልክ ቁጥሮችን ለቃቅሞ ዶሴውን አዘጋጅቷል። ብዙዎቻችን ባለማወቅ መንገድ የዚህ ስብስብ አባል ተደርገናል። ተመከቱ፤ ይህ የትግሬዎች ገዥ ቡድን፤ የመንግሥታዊ መዋቅሩን ለሱ ዓላማ ሙሉ በሙሉ ሲያውለው! ይህ ለማንኛችንም አዲስ አይደለም። ነገር ግን፤ ዘዴው አዲስ ነው፤ ቢያንስ ለኔ።

እናም ለዚህ የትግሬዎች ቡድን አንዱ የትግል ማደናቀፊያ፤ ታጋዮችን መከፋፈል ነው። ይህ ድርጅት የተፈጠረው፤ ይህን በተግባር ላይ ለማዋል ነው። በሀገር ውስጥ አልሠራለትም። በሀገር ውስጥ ትግሉ በግልጽ ተቀምጧል። በውጪ ላለነው መንገድ አለው። አሁን በውጪ ባለነው ታጋዮች በኩል ሁለት ክፍሎች ዘልቀው ይታያሉ። የመጀመሪያው ክፍል፤ በእድሜ እንደኔ በገፋነውና፤ “ኢትዮጵያዊ ነኝ!” እያልን ባደግነው በኩል የሚቀነቀነው ነው። እኔ በንጉሰ ነገሥቱ ጊዜ፤ በዩኒቨርሲቲ ተማሪነትና በአስተማሪነት ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊነት ታግያለሁ። በደርግ ጊዜ ከጥንስሱ ጀምሮ እስከ ትጥቅ ትግል ድረስ፤ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊነት ታግያለሁ። ይህን የትግሬዎች ቡድንም ታጥቄ በጦርነት፤ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊነት ታግያለሁ። ይሄን ሁሉ ያደረግሁት በኢትዮጵያዊነቴና ለአንዲት ኢትዮጵያ ነበር። በዚህ ክፍል ያለነው በዚህ ዓላማ እንዳለን ነን። ከአርባ ዓመት ወዲህ ያሉትና የዛሬዎቹ ወጣቶች ደግሞ፤ ዛሬ በምድሯ ላይ ባለው የፖለቲካ ሀቅና፤ ዓይኑን አፍጥጦ ጎልቶ በመጣው ቅራኔ ተመስርተው፤ በትግሬዎቹ ገዥዎችና፤ እንዲጠፋ በፈረዱበት አማራ፤ በትግሬዎቹ ገዥዎችና በደሉ በበዛበት ኦሮሞ፣ አኝዋክ፤ ኦጋዴኒ፣ ወዘተ. ሆኗል። እኒህ ሁለት ክፍሎች፤ ማለትም ወጣቶቹና ቀደምተኞቹ፤ አንድ ጠላት አለን፤ የትግሬዎቹ ገዥዎች። እናም ባንድነት ብንሰለፍ የዚህን ወራሪ እድሜ ልናሳጥር እንችላለን። በመካከላችን ያለውን ክፍተት ለማስፋትና እርስ በርስ ለማባላት፤ ይህ ወራሪ የትግሬዎች ቡድን እየጣረ ነው። የግድ ይሄን ተገንዝበን፤ ተመካክረን ወደ አንድ ሰፈር መሰባሰብ ግዴታችን ነው። አንዳችን የሌላችን ጠላት አይደለንም።

በኔ በኩል እስከዛሬ በኢትዮጵያዊነት መታገሌ ትክክለኛና የምኮራበት ታሪኬ ነው። ይህ ከአርባ አምስት ዓመት በላይ የሆነው ትግሌ፤ በተጨባጩ የሀገራችን የፖለቲካ ሀቅ ተመርኩዤ የወሰድኩት የፖለቲካ ትግል ነበር። በሌላ በኩል ደግሞ፤ ምን ጊዜም ቢሆን፤ የፖለቲካ ትግል የትናንት አይደለም። የፖለቲካ ትግል እኛ እያንዳንዳችን ወይም በጥቅል በያዝነው እምነት ላይ አይመሠረትም። በኛ ፍላጎትም አይካሄድም። ምኞት ጥሩ ነው። ፍላጎት ጥሩ ነው። ምኞትና ፍላጎት ግን በመሬቱ ላይ ያለውን ሀቅ አይተኩም። የፖለቲካ ትግል በመሬቱ ባለው የፖለቲካ ሀቅ ላይ የተመሠረተ ነው። በሀገራችን ባለው የአሁን የፖለቲካ ሀቅ ላይ የተመሠረተ ትግል እንጂ፤ በኔ ጭንቅላት ወይንም ፍላጎት ላይ የተመሠርተ ትግል ዕርባና የለውም። ስለዚህ እኔ እስከዛሬ የነበረኝ አቋምና ያደረግሁት የፖለቲካ ትግል ትክክልነት እንደተጠበቀ ሆኖ፤ አሁን ግን፤ በሀገራችን ያለው ተጨባጭ የፖለቲካ ሀቅ፤ ሌላ ትግል ጠይቆኛል። አቤት ብየዋለሁ። በሀገራችን ያለው የፖለቲካ ሀቅ፤ የትግሬዎች የበላይነትና የአማራዎች እንዲጠፉ መደረግ፣ የትግሬዎች የበላይነትና የኦሮሞዎች መደቆስ፣ የትግሬዎች የበላይነትና የእኝዋክ ከቁጥር ውጪ መደረግ፣ የኦጋዴኑ መበደል ነው። እናም ትግሉ፤ “አማራ መሆኔ ለመጥፋት ከዳረገኝ፤ ለአማራነቴ፤ ለሕልውናዬ መታገል አለብኝ!” ሆኗል። ኦሮሞውም፤ አኝዋኩም፣ ኦጋዴኑም፣ በተመሳሳይ መንገድ።

አሁን በውስጤ፤ የፖለቲካ አማራ ተፈጥሯል። አማራነትን ፈልጌ ወይንም ኦሮሞነትን ጠልቼ አልተወለድኩም። ኢትዮጵያዊነቴን ስወለድ ያገኘሁት የፖለቲካ ማንነት ነበር። ያኔ ሌላ የፖለቲካ ማንነት አልነበረም። አማራነት በሰውነት ውስጥ የሚዘዋወረውን ደም መምጫ ተናገሪ እንጂ ሌላ ሚና አልነበረውም። አሁን ግን አማራነቴ የፖለቲካ ማንነት ሆኗል። ያን ወደድኩም ጠላሁም መቀበል፤ ግዴታዬ ሆኗል። ይሄ ለሁላችሁም ግልጽ ስለሆነ ማተቱ መደረት ነው። እኔም በአማራነቴ፣ የአማራውን ሕልውና ለመጠበቅ፤ አማራ ነኝ ብዬ ተነስቻለሁ። ለአማራው በአንድነት መነሳት እታገላለሁ። ለሃያ አምስት ዓመት ተዘርዝሮ የማያልቅ በደል የደረሰበት ወገኔ፤ ሕልውናውን ለመጠበቅ ትግል ላይ ነው። ያሁኖቹ ከአርባ ዓመት በታች ያሉት ወጣቶች የያዙት ትግል ይህ ነው። አሁን በሀገራችን ባለ የፖለቲካ ሀቅ የጎላ ቅራኔ ላይ የተመሠረተ! ለዚህ ሲታገሉ፤ ይህ የኔ ትግል ሆኗል። እስከዛሬ ኢትዮጵያዊያን ታጋዮች ወደ አንድ እንድንሰባሰብ ጥሬ ነበር። ዛሬ ትምህርት ወስጃለሁ። እኔ ስለፈለግሁ የሚሆን ነገር የለም። በቦታው ያሉ ታጋዮች ወሳኞቹ ናቸው። የወደፊቷ ኢትዮጵያ ዕድልና ዕጣ፤ በምናውቃቸው በውጪ ባሉ የፖለቲካ ድርጅቶች ሳይሆን፤ በትግሉ በተሰማሩት የአማራ ወጣቶች፤ የኦሮሞ ወጣቶች፣ የአኝዋክ ወጣቶች እና አሁን በትግሉ በሀገራችን በተጠመዱት ታጋዮች እጅ ነው። አሁን የምጥረው፤ በአማራ ስም ተለያይተው የሚንቀሳቀሱ በውጪ ያሉ ታጋዮች፤ ወደ አንድ እንዲሰባሰቡ ነው። በጎን ደግሞ ሌሎችም ተሰባስበው በዚህ በወራሪ የትግሬዎች ቡድን ላይ እንዲነሱ ነው። ይህ በሀገራችን ላይ ያለው የፖለቲካ ሀቅ ግድ ያለው ነው። እኔ ሀቁን ተቀብዬ መታገል እንጂ፤ ራሴ በጭንቅላቴ ሀቅ ፈጥሬ፤ በዚያ ሀቅ መታገል አይደለም ሀገራዊና ታሪካዊ ግዴታዬ። ስለዚህ በዚህ ጉዳይ ላይ ከማንም ጋር ለመሥራት ዝግጁነቴን አብስሬ፤ ታታሪው የትግሬዎች ቡድን የሚያደርገውን አስተውለን መገንዘብ አለብን! እላለሁ። ገና ለገና ነገ በትግሬዎች ላይ አደጋ እንዳይደርስ ትግሬዎች ግራና ቀኝ አሁን በአማራው ላይ የግፍ ዶፍ ለሚያደርሱት ትግሬዎች ሲቆሙ፤ እኔ አማራ ነኝ የማልልበትና፤ ለአማራው እንዳልቆም የሚያግደኝ አእምሮ የለኝም። ዛሬ በአማራው ላይ ኢንተርሐውሜ እየተሰራ፤ ነገ በትግሬዎች እንዳይሠራ ብሎ መቆም መታወር ነው።

Latest from Blog

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop