ጉዞአችን ወዴት ነው?( ሉሉ ከበደ)

ዛሬ በመላ ኢትዮጵያ የተቀጣጠለው አብዮታዊ አመጽ ባለቤት እራሱ ህዝቡ ነው። እርግጥ ያኛው ወይም ይህኛው ወገን የቀሰቀሰው ነው የምንለው ሳይሆን እራሱ የትግሬው ነጻ አውጭ ቡድን ፤ ቧጦ፤ ነክሶ፤ ወግቶ አድምቶ አቁስሎ ፤ህዝቡን የመጨረሻው ሞት አፋፍ ላይ ቢወስደው አልሞት ባይ ተጋዳይ ሆኖ ሰዉ ተነሳ። ከልክ ያለፈ ስግብግብነት፤ ቅጥ ያጣ ሌብነት፤ ስርቆት፤የገንዘብ ስርቆት፤ የንብረት ስርቆት፤ የመሬት ስርቆት፤ የታሪክ ስርቆት፤ የተራራ ስርቆት፤ የሀገር ስርቆት፤ የማንነት ስርቆት፤ ህወሀት ህዝቡን አንገፍግፎት በግድ ከተኛበት አስነሳው።ጋዜጠኛም ፖለቲከኛም ቀስቅሶት ሀያአምስት አመት ያልተነሳውን ህዝብ። የህመምተኞች ስብስብ የሆነው የትግሬው ነጻ አውጭ ቡድን፤ለህዝቡ ቁጣ ማስታገሻ ብሎ ያቀረበው መዳኒት አንድ የሚያውቀውን ነገር ተኩሶ መግደል ብቻ ሆነና የህጻናትን ደም ማፍሰሱን ተያያዘው። ነገር ግን ወደኋላ የሚል ህዝብ ጠፋ። መልካም…. ህዝቡ ለለውጥ ዝግጁ ነው። ዋጋ ሊከፈል ቆርጧል። ይህን አመጽ አሰባስቦ፤ አስተባብሮ፤አንድ መቋጫ ያለው ግብ ላይ ማድረስ እንደሚገባ የሚያጠያይቅ ነገር የለውም። ይህ መኖር ያለበት የጋራ ግብ እስካሁን አልታየም። አልተሰማም። ሁለቱ አንጋፋ ክፍለ ህዝቦች አማራውና ኦሮሞው ናቸው የአመጹ ፊት አውራሪዎች። የተቀሩትም ሰማንያው ክፍለ ህዝቦች ሳይውል ሳያድር አመጹን እንደሚቀላቀሉ ምንም አያጠራጥርም። ምክንያቱም ወያኔ በኢትዮጵያ ውስጥ ያላቆሰለው፤ ያላደማው እና ደሙን ያልጠጣው የህብረተሰብ ክፍል የለምና! እና ?…… ይህ ስራት ከተወገደ በኋላ ስለምናቋቁመው የመንግስት አይነት ከየትኛውም ወገን የሚሰማ ነገር የለም። በሁለቱ አንጋፋ ክፍለ ህዝቦች ውስጥ ትግሉን እንመራለን ብለው ወደፊት የመጡ፤ ከአመጹ ውስጥ የወጡ፤ ወይም ደግሞ ቀደም ብለውም ትግል የጀመሩ አንድ ቦታ ላይ ተገናኝተው የጋራ ግባችን ይህ ነው ማለት ይጠበቅባቸዋል። ባስቸኳይ። ጉዞው ወደ አንድ ግብ ካልሆነ ወያኔን ጥሎ እርስ በርስ መያያዝ እንዳይመጣ መጠንቀቅ ያስፈልጋል። የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች በለስ እንዳይቀናቸው። ልብ ይሏል የቅርብም የሩቅም ወዳጅ የለንም ጠላት እንጂ። ይህ አመጽ የኢትዮጵያ ህዝብ አብሮነትን አንድነትን እንደሚፈልግ ባንደበቱ ያረጋገጠበት አጋጣሚም ነው። የኦሮሞ ደም ደሜ ነው ያለው አማራ፤ የአማራ ደም ደሜ ነው ያለው ኦሮሞ፤ ባጠቃላይ ሰማንያአንዱም ጎሳ አብሮ መኖር ያልቻሉበት ዘመን በታሪክ የለም። ባለፉት ሀያ አምስት አመታት ውስጥ የኢትዮጵያ ህዝብ በጎሳ ፖለቲካ ከሚገባው በላይ ቅጣት አግኝቷል። የእድሜ ልክ ትምህርትም አግኝቶበታል። የዘር ፖለቲካ ልክፍተኞች የሆናችሁ ኢትዮጵያውያን በቶሎ እራሳችሁን አስታሙና ጤነኛ ሁኑ። አለበለዚያ ህዝቡ ወያኔን ከቀበረ በኋላ ወደ ዘር ፖለቲካ እንመልስሀለን ብትሉት ወዮ ለናንተ ። ነጻነት ምናምን መገንጠል የምትሉ ቡድኖችና ግለሰቦች፤ የስልጣን ህልመኞች፤ ሌላ የመተላለቂያ ምእራፍ ልትከፍቱ ማንም አይፈቅድላችሁም።ራሳችሁን እንደ ህዝብ የምትቆጥሩ ተስፈኞች ወያኔ ካደረሰውና ከሚደርስበት አደጋ እንድትማሩእመክራችኋለሁ።ስለዚህ‰ የዜግች መብት ሙሉ በሙሉ የሚከበርባት፤ የህግ የበላይነት የሚነግስባት፤

ተጨማሪ ያንብቡ:  የፖለቲካ ማንነት በዛሬዋ ኢትዮጵያ - አንዱዓለም ተፈራ
Share