ከታመነ ይህዓለም
ህወሐት የአማራን ህዝብ እንደገና በጎሳ ለመከፋፈል በትግርኛ ጽፎ ለሕወሐት አባሎችና በነርሱ ስር ላሉ ተጠርናፊዎች እያሰራጨው የሚገኘው አጭር እቅድን የውስጥ አርበኞች አደባባይ አውለውታል:: ትግረኛውንም ወደ አማርኛ እንዲተረጎም “ትንሳኤ ሃገር” አድርጎ ለሕዝብ ይፋ ሆኗል:: የትግረኛውን ከላይ – ከታች ደግሞ የአማርኛውን ትርጉም ያንብቡ::
ንዛኤኤ
‹‹መጀመርታ ህዝቢ አምሓራ ኹሉ ሸነኻት ክንምልከቶ አሎንና፤ሎሚ ግዜ አብ ውሽጢ ህዝቢ አምሓራ ብዙሕ ብሄረ ብሄረሰባት አለዋ፤እንተኾነ ግና ከይተፈላለያ ይነብራ፤እዚ ሓድነቶም ንህዝቢ ትግራይ ሐደገኛ ስለዝኾነ ህዝቢ አምሓራ ንምፍልላይ አስታት አምሓራ ግጉይ ታሪኽ መ ፅናዕትን ምርምርን እናተገብረሉ ብመልክዕ መጽሐፍ ተሰናዲኡ ሕብረተሰብ ክጥቐመሉ ዝኽእለሉ መገዲ ንምምዕርራይ ፃዕሪ እናተገብረ እዩ፡፡ብተወሳኺ ዋላ’ውን እቲ ስራሕ ብርቱዕ እንተኾነ ህወሓት እዚ መጽሐፍ ዓቕሙ ብዝፈቕዶ መጠን ብተኸታታሊ ንምህታም መደብ ከም ዘለዎ በዚ አጋጣሚ ንምግላፅ ይፈቱ፡፡ምጅምርታ ግጉይ ዘንታ ዝሐዘ መጽሐፍ ተሓቲሙ ንህዝቢ አምሓራ ክቐርብ እዩ ፤ድሕሪኡ ህዝቢ አምሓራ እንተተባእሳ ህዝቢ ትግራይ በዓለ ርስቲ ይኸውን ማለት እዩ፤እንተዘይኾይኑ ህዝቢ አምሓራ ንህዝቢ ትግራይ ምህረት ዘይብሉ እዩ!
ኣብ ርእሲ’ዚ ናይ ትግራይ ስእሊ ታሪኽ ዝሐዘ መጽሐፍ ብብእዋኑ እናተመሐየሸን እናማዕበለን ተሓቲሙ ንህዝቢ ክቐርብ እዩ ዝብል እምነት አለና፡፡እዚ መጽሐፍ ናይ ኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ካአ ብዛዕባ ታሪኸ ትግራይ ዘለዎ ርእይቶ ክብንምባል ይሕግዝ፡፡ካአ ብዛዕባ አምሓራ ዘለዎ ርእይቶ ግና ንብዙሕ መዋእል ይደቁስ፤››አጸ
ከላይ ‹‹ንዛኤኤ›› ከታች ‹‹አጸ›› የሚሉት ምህጻረ ቃሎች ባይገቡንም በግርድፉ ልናስተረጉመው እንደሚከተለው ሞክረናል፡፡
“በመጀመሪያ የአማራን ህዝብ ከተለያዩ ጎኖች ማየት አለብን፤በአሁኑ ጊዜ በአማራ ህዝብ ውስጥ የተለያዩ ብሄር ብሄረ ሰቦች ይገኛሉ፤ ቢሆንም ግን ሳይነጣጠሉ እየኖሩ ነው፡፡ ይህ አንድነታቸው ለትግራይ ህዝብ አደገኛ ስለሆነ የአማራን ህዝብ ለመነጣጠል ስለአማራ የተዛባ ታሪክ ጥናትና ምርምር እየተደረገበት በመጽሃፍ መልክ ተዘጋጅቶ ህዝብ እንዲጠቀምበት ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ነው፤ በተጨማሪም ይህ ስራ ከባድ ቢሆንም ህወሀት ይህን መጽሐፍ አቅሙ በፈቀደ መጠን በተከታታይ ለማሳተም እቅድ እንዳለው በእዚህ አጋጣሚ መግለጽ ይወዳል፡፡ በመጀመሪያ የተዛባ ታሪክ የያዘ መጽሐፍ ታትሞ ለአማራ ህዝብ ይቀርባል ከእዚያም እርስ በእርሱ ሲጣላ ትግራይ ባለ እርስት ትሆናለች ማለት ነው፡፡ አለበለዚያ የአማራ ህዝብ ለትግራይ ህዝብ ምህረት የለውም፡፡
ከእዚህ በተጨማሪም የትግራይን ካርታና ታሪክ የያዘ መጽሐፍ በእየጊዜው እየዳበረና እየተሻሻላ ታትሞ ለህዝብ ይቀርባል የሚል እምነት አለን፡፡ ይህ መጽሐፍ የኢትዮጵያን ማህበረሰብ ስለ ትግራይ ያለውን አመለካከት ከፍ ለማድረግ ሲያግዝ ስለአማራ ያለውን አመለካከት ደግሞ ለብዙ ዘመን እንዲደቆስ ያደርጋል፡፡
ይላል አፈትልኮ የወጣው የቀቢጸ ተስፋው የሕወሓት ወንበዴ ቡድን እቅድ::
እንግዲህ ስለ አማራ ተዛብተው የተጻፉ ታሪኮችን መዝገበ-ቃላቶችን ብታነቡ እንዳይደንቃችሁ፡፡ በአማራ ክልል ውስጥ ያሉትን የአማራ
ተወላጆችም የተለያየ ስያሜ በመስጠት ለመከፋፈል ታቅደው ተዛብተው የተጻፉ የታሪክ መጻሕፍትን ብታነቡም አዲስ አይሁንባችሁ፤ ግን
ለህብረታችሁ ይበልጥ ተጠንቀቁ፤‹‹ተላላ ቃልን ሁሉ ያምናል ፤ብልህ ግን አካሄዱን አንድ በአንድ ያጤናል›› እንዲል ታላቁ መጽሐፍ ቅዱስ
በመጻፈ ምሳሌ 14፡15፣ ስለኢትዮጵያ ታሪክ እያሳተሙ የሚያድሉትን መጽሃፍ እንመርምር፡፡ ይህን በስንት ጥረት የተገኘ መረጃ ሼር በማድረግ ለኢትዮጵያ ህዝብ እናዳርስ፡፡
በእዚህ አጋጣሚ ሀከሮቻችንን አመስግኑልን! ብዙ ለአማራ የሚቆረቆሩ የውስጥ አርበኞችን ሁሉ እናመሰግናለን፡፡