February 19, 2013
13 mins read

በሰሜን አሜሪካ የፍኖተ ጋዜጣ ዝግጅትድጋፍ አስተባባሪ ኮሜቴ

ጥሪ ለወገኖቻችን

 

በኢትዮጵያ ሀገራችን ባለፉት ዘመናት ተንሰራፍተው የቆዩትን ጨቋኝ ስርዓቶች ለመጣል ከፍተኛ መስዋዕትነት የተከፈለ ቢሆንም በመስዋዕትነቱ እስካሁን የተገኘው ውጤት የበለጠ መስዋዕትነትን እየጠየቀ የመጣበት ሁኔታ እንጂ ህብረተሰቡ ተጠቃሚ የሆነበት ስርዓት ለመመስረት አልተቻለም፡፡

በተለይም ባለፉት 21ዓመታት ራሱን በዲሞክራሲያዊ  ቀለም በህገመንግስት ጭምር ቀባብቶ ብቅ ያለው አምባገነናዊ የህውሃት ኢህአዴግ መንግስት ከጊዜ ወደ ጊዜ የተቀባው ቀለም እየተላጠ ውስጣዊ ማንነቱ ራሱን ሊደብቅ ከማየችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ ለተወሰነ ጊዜ በልማታዊ መንግስትነት የምዕራብዓያዊያን ሀገሮችንም ያነሆለለበት የሁለት አሀዝ እድገት በራሱ ቋንቋ እያሻቀለ መሄዱን ለመስማት ተችሏል፡፡

ይህ አዲስ  ክስተት አይደለም፡፡ የህብረተሰብ እድገት የአለም የፖለቲካ ሁኔታ መገለጫ ነው፡፡ በምንም ዓይነት ኃይል ማንኛውም አይነት አምባገነናዊ ስርዓት በረሱ ውስጣዊ ቅራኔም ሆነ በህብረተሰቡ የተደራጀና የተቀናጀ ህዝባዊ ትግል ተገርስሶ እንደሚወድቅ ዛሬ የምናያቸው የተሻለ ስርዓት የመሰረቱ አገሮች በተለያየ አካሄድ ያለፉበት ደረጃ ነው፡፡ ለዚህም ነው ወያኔ ኢህአዴግ የፈለገውን ያህል ራሱን ቢቀባባም እንደግለሰብ ህይወት የፖለቲካ ስርዓትም ማለፉ የማይቀር የታሪክ ሂደት ነው የምንለው፡፡

ቁምነገሩ ግን በማለፉ  ሂደት ውስጥ በህብረተሰቡ ላይ ጥሎ የሚሄደው ጠባሳና ትውልዱ ከስርዓቱ የሚያገኘው በጎና ቀና ተግባራት በታሪክ ውስጥ የሚኖረው ቦታ ነው፡፡ ለዚህም ነው ዛሬ በተለይም በሀገር ውስጥ ይሄንን ስርዓት በህዝብ ትግል አስገድዶ ባለፉት ትግሎች ያለፍንበትን በሰላማዊ መንገድ ህዝብን የስልጣን ባለቤት የማድረግ ሰላመዊ የፖለቲካ ትግል ላይ እውቀት፡ ጉልበትና ጊዜያቸውን ህይወታቸውን እና ንብረታቸውን ጭምር መስዋዕት በማድረግ ላይ የሚገኙ ወገኖቻችንን አይዞአችሁ በርቱ ከጎናችሁ ነን የምንለው፡፡ በመስዋዕትነት ደረጃ ግንባር ቀደሙ ገፈት ቀማሾች በመሆናቸውም ያኮሩናል፡፡

አንዳዶች እንደሚገምቱት ዛሬ ተቀዋሚው ኃይል 4ኪሎ ቤተመንግስት ባለመግባቱ ብቻ የመሪነት ብቃትና መመዘኛ ተደርጎ ሊወሰድ የሚገባም አይመስለንም፡፡ 4ኪሎ በብዙ መንገድ ሊገባ ይችላለል፡፡ በኃይልም፣ በመፈንቅለ ማንግስትም፣ በሸፍጥም፣ በማተራመስም፣ በሽብርም፡፡ ቁምነገሩ መንግስታዊ ስልጣኑ የሚቆምበት ህዝባዊ ኃይል የአገራችንን አንድነትና ሉኣለዊነት የህዝባችንን ሰላምና ደህንነት ፍትህና እኩልነትን የሚያረጋግጥ ማህበራዊ መሰረት ላይ የቆመ መሆኑን ማረጋገጥ እና መንግስት ወድቆ መንግስት ሲተካ ሌላ 100 እና 200 የሚሆኑ የፖለቲካ ተቃዋሚ ድርጅቶች የማይፈለፈሉበት ሁኔታን ማመቻቸት ሲቻል ብቻ ነው፡፡ ለዚህም ዋነኛው መሰረት የህዝቡን ንቃትና አስተሳሰብ መቀየር ወሳኝነት አለው፡፡ በተቀየረ አስተሳሰብ ላይ ተመስርቶ ነባራዊ ሁኔታን የመቀየር ችሎታን ማሳደግ ማለት ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ የመገናኛ ብዙሃን ሚዲያዎች እና ጋዜጦች ሚና እጅግ የላቀ ነው፡፡ የዛሬ የትኩረት ነጥባችንም የህብረተሰባችንን አስተሳሰብና አመለካከት ንቃት ብሎም ለማደራጀት ስራ ወሳኝነት ያለውን በሀገራችን የነፃ ፕሬስ መዳበር አስፈላጊነት ለመጠቆም እና የዚሁ ነፃ ፕሬስ አካል የሆነችውን ፍኖት ነፃነትን መልሶ ለህትመት ለማብቃትና ህይወት ለመስጠት ጥሪ ለማቅረብ ነው፡

አምባገነኑ የወያኔ  ኢህአዴግ መንግስትን አስከፊ ተግባራትን ከማጋለጥ ባሻገር ምን ዓይነት ስርዓት በአገራችን ሊገናባ እንደሚገባ በመስተማር   በነፃ ፕሬስ ውስጥ ቀዳሚነትን በመያዝ ላይ የነበረችው ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ በትንሹ ተነስታ በስርዓቱ ደባ ህትመቷ ቢቋረጥም በህትመቷ ጊዜ እስከ 30ሺ ኮፒዎች በማሳተምና በማሰራጨት በህዝብ ዘንድ  ተነባቢነትን እና ተአማኒነትን ያተረፈች ልሳን ነበረች፡፡ በዚህች ጋዜጣ ላይ ብርቅዬ የሀገሪቱ ወጣት ልጆች እና አዛውንቶች ያቀረቧቸው የነበሩት ፅኁፎች እና መረጃዎች ጋዜጣዋን ከዜና ወይም ከወሬ አቀባይነት አሸጋግሮ ወደ አቅጣጫ አመላካች ቀስቃሽና አስተማሪነት በአጠቃላይም ለትግሉ ከፍተኛ አነቀስቃሽነት መሳሪያነቷን የተረዳው አምባገነኑና አፋኙ የህውሀት ኢህአዴግ መንግስት በልዩ ልዩ ምክንያቶች ለመዝጋት የሞከረ ቢሆንም አዘጋጆቹ በከፈሉተት መስወዕትነት እስካሁን ጊዜ  መቆየቱዋ ይታወቃል፡፡ የወያኔ ኢህአዴግ መንግስት በመጨረሻ ላይ ጋዜጣ አታሚዎችን ‹እኛ ማተም እንፈራለን› እሰኪሉ ድረስ አሳታሚዎችን በፍርሀት ሰለባ ተቆጣጥሮ ህትመቷ እንዲቋረጥ መደረጉ ይታወቃል፡፡ ያም ሆኖ ምንም እንኳን በቋሚ መልኩ ባይሆንም በተለያዩ ድህረ ገፆች አማካይነት የህዝብ ልሳን በመሆን አገልግሎቷን ቀጥላለች፡፡

ውድ ኢትዮጵያውያን ፣ ዛሬ በዚህ አምባገነን ስርዓት የነፃ ፐሬሶች ከመቼውም ጊዜ በላይ ተዳፍነው የሚገኙበትና ወያኔ አፍንጫ ስር ሆነው የዚህን አስከፊ ስርዓት ገበና በማጋለጥም ሆነ እንደ ማደራጃ ኃይልም በማገልገል ላይ የሚገኙ የብርቅዬ የኢትዮጵያ ልጆችና ልሳኖቻቸው በምንም መልኩ እንዲዘጋ መፍቀድ ያለብን አይመስለንም፡፡የነአንዱአለም፣ የነእስክንድር፣ የነተመስገን እንዲሁም በርካታ የተሰደዱ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ብዕሮች ይሄንን ስርዓት ምንያህል እደሚያስፈሩት እየወሰዳቸው ያለው አስከፊ እርምጃዎች ማስረጃዎች ናቸው፡፡ ስርዓቱ አስሮ የማይጨርሳቸው ልጉዋም የሚያቅማቸው በሺህ የሚቆጠሩ ወጣቶች ከቀን ወደቀን እየፈሉ ናቸው፡፡ ከሁሉም በላይ የለውጡ ባህር በሆነው ህዝብ መሃል የሚያሰሙት ድምፅ ከምንም መሳሪያ የበለጠ ህዝባዊ እምቢተኝነት ይፈጥራል፣ያደራጃል፣ ያስታምራል፣ይቀሰቅሳል፣  አቅጣጫ ያለው በፅኑ መሰረት ላይ የተገነባ ህዝባዊ እምቢተኝነትን ይፈጥራል፡፡ ለዚህ ነው ፍኖተ ጋዜጣ በሳምንታዊ ህትመት እስከ30ሺህ ኮፒ ታትማ ሁለት ሰዓት በማይሞላ ጊዜ ውስጥ በገበያ ላይ የማትገኘው፡፡ ነፃ ፕሬስ በራሱ ብቻውን ለውጥ ያመጣል ማለት አይደለም፡፡ የለውጥ ኃይልን ያሰባስባል፡፡ ከኢቲቪ፣ ከአዲስ ዘመን ለህብረተሰባችን የሚነሰነሰውን ሳይወድ በግድ እንዲጋት የሚደረገውን ህዝባችንን አማራጭ ሃሳብና እውነታን ያስጨብጣል፡፡

በመሆኑም በአሁኑ ወቅት የፍኖተ ጋዜጣን ህትመትና ስርጭት ከወያኔ ኢህአዴግ የተለያዩ የመቆጣጠሪያ ዘዴዎች በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ሊያላቅቅ የሚችል የራሱ የህትመት መሳሪያና ዝግጅት ለማደራጀት የሚያስችል ፕሮጀክት ተዘጋጅቷል፡፡ ለዚህ ፕሮጄክት መሳካት የአገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን እና ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ተፋላሚዎችን ድጋፍና እገዛ ይጠይቃል፡፡ ለዚሁም እንዲረዱ ከ20 እስከ 500 ዶላር(ብር) የሚደርስ ትኬቶች ተዘጋጅተው በቅርቡ ለገበያ እንዲቀርቡ ይደረጋል፡፡ በተለይ በውጪ አገር  የሚገኙ ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን ይህን ለማሳካት ከፍተኛ ጥሪ ቀርቦልናል፡፡ ጎዳናችን የተለያየ ሊሆን ይችላል፣ የማይለወጥ የጋራ ግባችን ግን በሀገራችን ፍትህ ሰላምና እኩልነት የሰፈነበት፣ ሉአላዊነት የተረጋገጠበት ስርዓት ማየት ነው፡፡ ይህ ደግሞ በምኞት ሳይሆን ሁላችንም ትንሽ ጠጠር ስንወረውር ብቻ ነው የሚሳካው፡፡ የአምባገነኑ ህውሀት ኢህአዴግ መንግስትን በተሻለ አስተሳሰብና ኃይል በልጦ የሚገኝ የፖለቲካ ሀይል ለመፍጠር የነፃ ፕሬሶች በጥራትና በብዛት ለህዝባችን ማዳረስ ምንም አማራጭ የሌለው የዴሞክራሲ ስርዓት ቁልፍ መክፈቻ ነው፡፡ የፖለቲካ ስልጣን በየትኛውም መንገድ ቢመጣ የተገኘውን ስልጣን የራሱ አድርጎ የሚመለከት አስተሳሰብና ህብረተሰብ እስካልተፈጠረ በሚነሱ ህዝባዊ ችግሮች ሁሉ የሚሰጡት ምላሾች ስልጣን የማቆየትና ያለማቆየት ጥያቄ ስለሚሆን በጠማንጃ ታፍኖ ለማይኖር ስርዓት እና ህዝብ በንቃት ላይ ለተመሰረተ ለውጥ የነፃ ፐሬስ ወሳኝነትን እንረዳ፡፡

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

በሰሜን አሜሪካ የፍኖተ ጋዜጣ ዝግጅትድጋፍ  አስተባባሪ ኮሜቴ

Latest from Blog

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop