February 19, 2013
5 mins read

ወንጀለኛ የህወሃት ጀሌዎችን በህግ ለመፋረድ ድጋፍዎን ይስጡ

ኢትዮጵያዊያን በሀገራቸው ጭቆና፣ አድልኦ፣ ግፍና በደል አንገሽግሿቸው ተሰደው በሚኖሩበት ምድር ሁሉ ክብራቸውና ነጻነታቸው ተጠብቆ መኖር እንደሚገባቸው ፈጽሞ አጠያያቂ አይደለም። የህግ ልእልና በሰፈነባቸው አገሮችም ይህንን መሰረታው መብት ለማስጠበቅ ከህግ በላይ ምንም ሀይልና ጉልበት ያለው መሰሪያ የለም።
ህወሃት መራሹ የኢትዮጵያ መንግስት “አሰረን አሳደደን” በማለት በአውሮፓና በአሜሪካ የፖለቲካ ጥገኝነት በመጠየቅ በስደተኛ ስም በተለያየ የማምታቻ ሽፋን ተደብቀው ኢትዮጵያዊያን ያለስጋት የነጻነት አየር እየተነፈሱ እንዳይኖሩ ለማድረግ የሚጥሩ ሰላዮችና የጨቋኙ ስርአት አቀንቃኞች መኖራቸው በተለያየ ጊዜ የተረጋገጠ ሃቅ ነው።
ምንም እንዃን በርካታ ኢትዮጵያዊያን በተደጋጋሚ የነዚህ ወንጀለኛና አሸባሪ ግለሰቦች ሰለባ ቢሆኑም እስካሁን ጠንካራ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸው በቂ ጥረት አልተደረገም።
ባለፈው ግንቦት 10 2004 (May 18, 2012) ጋዜጠኛ እና የሰብአዊ መብት ተሟጋች የሆነው አበበ ገላው የቀድሞው አንባገነን መለስ ዜናዊን ወንጀሎች በአለም መሪዎች ፊት ስላወገዘ እና ስላጋለጠ እንዲሁም የታፈነ የኢትዮጵያን ህዝብ የነጻነት ጩኸት ስላሰማ በተለያዩ የህወሃት ጀሌዎች የሽብር ፈጠራ ወንጀል ሰለባ ሆኗል። በቅርቡ ከነዚህ በህገወጥ የወንጀልና የስለላ ተግባር ከተሰማሩ የህወሃት ጀሌዎች መሃል ጥቂቶቹን ያጋለጠው ጋዜጠኛ አበበ ገላው፣ ጠበቃ ይዞ በህግ ለመፋረድ እንቅስቃሴ ጀምሯል።
ይሄንኑ አላማ ለማሳካት እና ወያኔዎች የፈጠሩትን የጸጥታ ስጋት አቅም በፈቀደ መንገድ ለመቅረፍ ጥቂት የECAD የፓልቶክ መድረክ አባላት በራሳቸው አነሳሽነት ባዋጡት ገንዘብ ለዚሁ አላማ ማስፈጸሚያ የሚሆን ልዩ የባንክ ሂሳብ ተከፍቷል::
ነጻነትና የህግ ልእልና በሰፈነባቸው አገሮች ከህግ በላይ ወንጀለኞችን የመፋለሚያ መሳሪያ ባለመኖሩ፣ ጉዳዩ ይመለከተናል የሚሉ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ይህንን ጥረት አቅማቸው የፈቀደላቸውን ያህል እንዲያግዙ ወገናዊ ጥሪ ቀርቧል።
ህግን ተጠቅሞ ህገወጦችን መፋረድ አንድ የትግል ስልት በመሆኑ ለአንድ ሰው ብቻ የሚተው ጉዳይ አለመሆኑ ለማንም ግልጽ ነው። እርስዎም ለዚሁ እንቅስቃሴ የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ አስፈላጊነቱን ካመኑበት ከታች ከተዘረዘሩት አማራጮች በአንዱ መንገድ አስተዋጽኦ ማድረግ ይችላሉ:::
1/ በማንኛውም አሜሪካ በሚገኝ የWells Fargo ቅርንጫፍ AG Legal Fund, Acc. No. 3525090746 በቀጥታ ገንዘብ ማስገባት ይቻላል።
2/ አሜሪካ በሚገኝ ማንኛው Bank of America ቅርንጫፍ በኩል በቀጥታ ገንዘብ ማስገባት ይቻላል:
AG Legal Fund, Acc. No. 485010192701
3/ ከሌሎች አሜሪካ የሚገኙ ማንኛውም ባንኮች ለማስተላለፍ (wire) ለማድረግ AG Legal Fund, Acc. No. 485010192701 , ABA 121000248 መጠቀም ይቻላል::
4/ ከአሜሪካ ውጭ ከሚገኙ ባንኮች ገንዘብ ወደ AG Legal Fund ለማስተላለፍ Acc. No. 3525090746 SWIFT- WFBIUS6S መጠቀም ይቻላል::
5/ በኢንተርኔት አማካኝነት በ Paypal አስትዋጾ ማድረግ ከፈለጉ ከታች ያለውን ድር (link) በመጫን አስተዋጾ ማድረግ ይችላሉ። https://www.paypal.com/cgi-bin/webscr?cmd=_s-xclick&hosted_button_id=UHPF5RPB2PBSN
6/ ከዚህም በተጨማሪ በWestern Union ከላይ በተጠቀሱት የባንክ ሂሳቦች በአንዱ አማካኝነት ገንዘብ ማስተላለፍ ይችላሉ።
ስለጉዳይ ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁ. (001) 5718829882 በመደወል ወይንም በ [email protected] ኢሜይል ማድረግ ይችላሉ። እናመሰግናለን!!

Latest from Blog

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop