Hiber Radio – ፓትርያርክ ሆነው የሚሾሙት አቡነ ሳሙኤል የወ/ሮ አዜብ መስፍን የነብስ አባት ናቸው

/

የህብር ሬዲዮ ዕሁድ የካቲት10 ቀን 2005 ፕሮግራም 

<<…የግብጻዊው ንግግርና የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሰላማዊ እንቅስቃሴ የሚያገናኘው ነገር የለም።በወቅቱም ሰውዬው ያንን ሲናገር በመድረኩ ላይ እኔም ታማኝም በቤቱ ያለውም ሰው ተቃውሟል።ሰውዬው ዲሲ ያለ ያንድ መስጊድ ዒማም ነው።መጀመሪያም መጋበዝ አልነበረበትም። ሰውዬው በኢትዮጵያ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ እንኳ የሚያውቅ አይደለም።…የሙስሊሙ እንቅስቃሴ ከመስጊድ ያልወጣበት የራሱ ስትራቴጂ አለው። ሙስሊሙና ክርስቲያኑን ለማጋጨት የሚደረግን ትንኮሳ ያስቀራል።….>> ወጣቱ የፖለቲካ ተንታኝና ተመራማሪ ጃዋር መሐመድ ለህብር ሬዲዮ ከሰጠው  ቃለ ምልልስ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡ)

<<…የኢትዮጵያ ዲያስፖራ የሚያደርገው የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ ተዳክሟል የሚለውን እኛም እየታዘብነው ነው። አገር ውስጥ ያለው እንቅስቃሴ ሲዳከም ውጭ ያለው ይዳከማል።እዚያ ሞቅ ሲል እዚህም ሞቅ ይላል።የዚያ ነጸብራቅ ነው።..ከዚያ ባሻገር ግን እዚህ ያለነው ኢትዮጵያውያን ማድረግ የምንችለውን ያህል ባለማድረጋችን እና ስርዓቱ እንደሚፈልገው በተለያየ መንገድ ተከፋፍሎ የሚሰራ ስራ አገር ውስጥ ያለውንም እዚህ ያለውንም ትግል እየጎዳ ያለ ይመስለኛል።ይህን ቀርፎ የተሸለ እንቅስቃሴ ማድረግ ይቻላል። ..ፕ/ት ኦባማ የጠቀሱትን የተለያዩ አገሮችን የዲሞክራሲ እንቅስቃሴ መደገፍ ሰምቼዋለሁ። ምዕራባውያን እኛ ጠንክረን ስንቆም  …>> ዶ/ር ካሳ አያሌው የማርች ፎር ፍሪደም  እንቅስቃሴን  ከሚያስተባብሩት አንዱ (ሙሉውን ቃለ መጠይቅ አድምጡ)

 

ዜናዎቻችን

በቤይሩት ለኢትዮጵያዊቷ ዓለም ደቻሳ ሞት ተጠያቂ የሆነው ግለሰብ ጉዳኢ በፍ/ቤት ሳይደመጥ ለሌላ ጊዜ ተላለፈ

– ፓትርያርክ ሆነው የሚሾሙት አቡነ ሳሙኤል የወ/ሮ አዜብ መስፍን የነብስ አባት ናቸው

ኢትዮጵያውያን በዓለም ዙሪያ በ22 ታላላቅ ከተሞች የየካቲት12 ጭፍጨፋን አስታከው  የፋሺስት ኢጣሊያን ድርጊት ይቃወማሉ

ተጨማሪ ያንብቡ:  ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ከቅዱስ ላልይበላ ካህናትና ህዝብ ጋር የነበረው ውይይት
Share