ዳግማዊ ጉዱ ካሣ
ስለአንድ የፋኖ መሪ “የአክስቴ ልጅ ነው” ከምትል ወጣት በቲክቶክ የሰማሁት እውነት ከሆነ የፋኖ ትግል አመራር – ሁሉም ባይሆን የተወሰነው ክፍል – ጥሩ አንደበት ግን መጥፎ ምግባር ባላቸው ሰዎች እጅ ላይ ወድቋል ማለት ይቻላል፡፡ ይህ ደግሞ መገለጥና መታወቅ መፍትሔውም መፈለግ ይኖርበታል፡፡ ያቺ የአክስት ልጅ ነኝ ባይ ወጣት ልጅ የተናገረችው ውሸቷን ከሆነ (ቢሆንልኝ ደስ ይለኛል) ኩነኔው ወደሷ ይሂድልኝ፡፡ ከአንድ ዕብድ ሰው ጋር ስታወራ በቲኪቶክ ሰምቻት ብዕሬን ከማንሣት ልቆጠብ አልቻልኩም፡፡ ልጂት የተናገረችው ውሸት እንዲሆን እየተመኘሁና እየጸለይኩ “እውነት ቢሆንስ?“ በሚል መነሻ ሃሣብ መማማሪያ ይሆናልና ቀጣዩን ሃተታ ጻፍኩ፡፡ ደግሞም ከአፍ የሚወጣ እንጂ ወደ አፍ የሚገባ ሰውን አያረክሰውምና የተነገረውና የሚነገረው ሁሉ እውነትም ሆነ ሀሰት በዚያ መስመር የሚነጉዱ ሰዎች ይመለሱ ዘንድ የማስጠንቀቂያ ደወል ስለሚሆናቸው በዚህ መልክ መነጋገሩ መጥፎ አይደለም፡፡ በሚያልፍ ብልጭልጭ ዓለም የማያልፍ የታሪክ ጠባሳ ማስቀመጥ ቀጣይ የራስን ትውልድ ሳይቀር መቅጣት ነውና ታጋዮቻችን ከትዕቢትና ከዕብሪት ሊቆጠቡ ይገባል፡፡ ምክርን መስማት ደግሞ የትልቅነት ምልክት ነው – በተለይ አለኝ የምትለውን ነገር በሴከንዶች ውስጥ ልታጣ በምትችልበት የአሁኑ ብልጭልጭ ዓለም፡፡ ዛሬ የኔ ነው ያልከው ነገ የለም፡፡
አንድ መሪ ቀርቶ ተራ ታጋይ ሴት አውል ወይም ሴሰኛና ዘማዊ ከሆነ እሱም ትግሉም አበቃለት፡፡ ዘማዊነት የኃጢኣቶች ሁሉ ቁንጮ ነው፡፡ ምክንያቱም ወሲብ ማለት ክርስቶስ የተሰቀለበትን የጌቴሰማኒ ትዕምርተ -ዕርፈ መስቀል አንገቱ ላይ ተሸክሞ የሚዞር አንድ ክርስቲያን በአንድ ካልተወሰነ ከብዙ ነገሮች ጋር የሚያነካካውን ኃጢኣት ይሠራል፡፡ ዝሙተኛ ሰው ፍቅር አያውቅም፡፡ አመንዝራ ሰው ጥዶ ዘለል ነውና ቤተሰባዊ ትስስሩ ልል ነው፡፡ ሴሰኛ ሰው የራሱንና ከሰውም ጭምር የሚቀማትን ሴት ቁሣዊ ፍላጎት ለማርካት ሲል ብዙ ገንዘብ ማግኘት ይኖርበታል፡፡ ያን ገንዘብ ለማግኘት ሲል ደግሞ የማይሠራው የሙሥናና የምዝበራ ወይም የማጭበርበርና የማታለል ዕኩይ ድርጊት የለም፡፡ ገንዘብ ለማግኘት ሲል ሌባ ነጋዴና አጋች ሸኔ እስከመሆን ይደርሳል፡፡ ሞራላዊ፣ ወግ-ልማዳዊ፣ ባህላዊ፣ ሃይማኖታዊና ሥነ ምግባራዊ ክሮቹን በወሲብና እሱን ተከትለው በሚጠናወቱት የሀብትና የሥልጣን ፍቅር ምክንያት በጣጥሶ ይጥላቸዋል፡፡ በዚያም ምክንያት ከብዙ እንስሳት የወረደ “animalism”ን ይዋረሳል፡፡ በአማራ ፋኖ አካባቢ እነዚህ ጠያፍ የኦሮሙማ መታወቂያዎች እየታዩ እንደሆነ መስማት ከጀመርን ቆዬን፡፡ የኦሮሞና የትግሬ ወሮበላ ሲዘርፍና ሲያግት ወንጀል፣ የአማራ ፋኖ ወይም በአማራ ፋኖ ስም የሚነሣ ወምበዴ ሲዘርፍና ንጹሕ ዜጋ ሲያግት ጽድቅ የሚሆንበት ሁኔታ ደግሞ ሊኖር አይችልም፡፡ ይህ ዓይነቱ double standard “ለራስ ሲቆርሱ…” ዓይነት ብልጥነትን የተመረኮዘ ሞኝነት ነው፡፡ አማራ ራሱን ማጥራት ያለበት ብዙ ነገር አለ፡፡ ቤትን ክፍት እየተው ሰውን ሌባ ማለትም በተለይ በዚህ ቀጣፊው በበዛበት ዘመን አያዋጣም፡፡ ከፍ ሲል ያዬነው ዓይነት ራሱን ወደሸቀጥነት የለወጠ መሪ በፊት የነበረው ጠንካራ ጎን በይሁዳዊ ገንዘብ ወዳድነት ይለወጥና መላ ትኩረቱ ኢጎውን ወደማስደሰት ተዛውሮ ሚሊዮን ዜጋ ቢጠበስ ቢቀቀል ደንታው አይሆንም፡፡ ሚሊዮን ከመኖሪያው ቢፈናቀል፣ በቆንጨራ ተጨፍጭፎ በዶዘር ቢቀበር ሃሳቡ አይበላውም፡፡ በአጭሩ ወደአቢይነት ይቀየርና ልጆቹንም ሆነ እናቱንና አባቱን ሳይቀር በጅምላም ሆነ በችርቻሮ ባወጡ እስከመሸጥ ይደርሳል፡፡ ይህ ዓይነቱ ሰው የቀንና የሌሊት ህልሙ ቆነጃጅቱ ሣዱላዎች ናቸው ወይም ይህን ፈተና እንኳን ቢያልፍ የአራት ኪሎ ምርኮኛ ሆኖ በሥልጣን ፍቅር እየናወዘ ዓላማውን ይስታል፡፡ ባለዝናና ባለገንዘብ የምታሳድድ አንዲት ሴት ትታው የምትመጣው ሌላ ወንድ – ባልም ሊሆን ይችላል – መኖሩ ደግሞ ሊዘነጋ አይገባም፡፡ ያ ሴሰኛ መሪ በምናብም በእውነትም ከስንቱ ጋር እንደሚቀያየምና ለነፃነት ትግል ሊያውለው የሚገባውን ጥይት በሴቶች ሳቢያ ለሚገጥምበት ሻምላ ውጊያ ሊጠቀምበት እንደሚችል ይታያችሁ – የደራሲ ሰርቫንቴስ ምናባዊ የልቦለድ ገጸ ባሕርይ ዶን ኪሾት በለው፡፡ አንድ መልካም ዝና የነበረው የተቃውሞው ፖለቲካ መሪ ደግሞ በጊዜ ሂደት በማይረባ ፍላጎት ተጠልፎ በዱሮ ስሙ እየነገደ ብዙ የዋሆችን በማታለል ከጎኑ ሊያሰልፍ፣ እንደበግም ሊነዳቸውና የበረከተ መርገሙ ተባባሪ ሊያደርጋቸው ይችላል – ይህ አዝማሚያም እየታዬ ነው፡፡ ምን አለፋችሁ – እንደነዚህ ያሉ መጥፎ ደባል ጠባያት ያሉት ሰው የፋኖን ትግል የሚመራው ከሆነ እመኑኝ ወደሊማሊሞ ገደል እንጂ ወደአራት ኪሎ ቤተ መንግሥት ሊሆን አይችልም፡፡ ይህን መሰሉን የሰው ውራጅ አለመታገል ደግሞ ከሰውነት ተራ መውረድ ነው፡፡ ነፃነት በይሉኝታ አትመጣምና፡፡
አታጋይ መሪ አርአያ መሆን ይገባዋል – ቢቻል እንደክርስቶስ ባይቻል ደግሞ እንደሆቺሚንና እንደቸኩቬራ ይህም ባይቻል እንደማኅተመ ጋንዲና እንደኔልሰን ማንዴላ፡፡ ታጋዮች እየተራቡና እየተጠሙ እየታረዙም ገና በጫካ ያለ መሪ ጌታዋን የገደለች በቅሎ የሚመስል ካገኛትም ጋራ የሚጋደም ከሆነ ትግሉን በአፍጢሙ ደፋው፡፡ አውቃለሁ – መፍረድ ቀላል ነው፡፡ ይገባኛል – መናገርና መጻፍም እንደዚሁ ቀላል ነው፡፡ ነገር ግን የነገሮች አካሄድ የተጣመመና አክሳሪ መስሎ እየታየኝ ዝም ብል የ35 ዓመታት ልፋቴን ገደል እንደመክተት ያህል ነው፡፡ ያበጠው ይፈንዳ የሚሰማኝን እናገራለሁ፡፡ አንድ ሰው ባለፈው ብሶቴ ምክንያት ሰለጠነች ቢሏት የባሏን መጽሐፍ እንዳጠበችው ሴት መስሎ አቅርቦኛል፡፡ እውነትን በመጻፌ ልሰደብም እንደምችል ስለተረዳሁበት በእውነቱ አልተከፋሁም – እንኳንም የክብርት ባልተቤቴን መጽሐፍ አጠብኩ፡፡ ማጠቤን የምቀጥልበት መሆኔን የምገልጠው ለትምክህት ሣይሆን ከእውነት መንገድ ላለመውጣት ያለኝን ፅኑ አቋም ለማሣወቅ ስል ብቻ ነው፡፡
ሌሎችን በስድብ ስታጥረገርግ መደሰትና የራሴ የምትለውን ግን ያጠፉ ቢያጠፉ ሳትተች ማሽሞንሞን የሚያዛልቅ አይደለም፡፡ ደግሞስ ገና ምን ታዬና! የአማራን ትግል የሚጠልፉና የመቶ ሺዎችን መስዋዕትነት ለግል መጠቀሚያ የሚያደርጉ ጥቁር ውሻ ይውለዱ ብዬም እራገማለሁ፡፡ በጊዜ የጮኸ ጅብ አያሳድረኝም የምንለው ወደን አይደለም፡፡ ይሉኝታና ሀፍረት ሲቀብር እንጂ ሲያነሳ አልታየም፡፡ “ትግሉን ይጎዳል፣ ትግሉን ያጓትታል፣ ቲሪሪም ቲሪሪም…” ከእንግዲህ አይሠራም፡፡ በመሠረቱ የአማራ ጠላቶች በፋኖ አመራርም ይሁኑ፣ በፋኖ ሠራዊትም ውስጥ ይሁኑ፣ ከፋኖ ውጪም ይሁኑ… ዕድሜያቸው ሊያጥር ቀኑ ቀርቧል፡፡ የሚጠበቀው ዓለም አቀፉ የአማራና የኦርቶዶክስ ጠላት በራሱ የቤት ሥራ ከአሁኑ በበለጠ በደምብ እስኪወጠር ድረስ ነው – ያንንም በከፍተኛ ጉጉት እየተከታተልነው እንገኛለን፤ ውስጠ ምሥጢሩ የሚገባን ጥቂቶች፡፡ ያም ሂደት ጊዜውን ጠብቆ እየተፋፋመ ነው፡፡ ዕድሜ ለወንድም ፑቲንና “ዘመድ አዝማዶቹ”፡፡ ምዕራቡ ዓለም ከአውሮፓ ጭምር የተሟላ የቤት ሥራውን ሲጀምር እንግሊዝኛ እኔስ ለምን ይቅርብኝ in the mean time ኢትዮጵያም እፎይታ ታገኝና ልጆቿ የዘመናት የችግር ቋጠሯቸውን ፈትተው የጋራ መፍትሔ በመፈለግ በማይማን የእነእንቶኔ ተላላኪዎች ተይዞ የነበረ መንበራቸውን በምርጫና በምርጫ ብቻ ይቆጣጠራሉ፡፡ ያኔ ሲ አይ ኤ የለ፤ ኤፍ ቢ አይ የለ፤ ኤም አይ ፋይቭና ሲክስ የሉ፤ ሞሳድ የለ – ሰላም ብቻ፡፡ ያኔ ጃዝ ብለው የላኩብን ዕብድ ኦሮሙማ ወደ … ይሄዳል፡፡ ቂላቂል ጸሐፊ እንዳልመስልህ “ወደ ማዳጋስካር” የምልልህ ጅሌ፡፡ ለነገሩ እሱም ያኔ ብርቅ ነው – አይገኝም፡፡ ኦሮሙማ/ኦነግሸኔ የሕወሓት ዕድል ይናፍቀዋል አልኩህ እኮ በቀደምለታ በሰደድኩልህ ጦማር፡፡ ፈጣሪ የውሻን ደም እንኳን በከንቱ አያስቀርም፡፡ ትንሽ ታገስ ብቻ፡፡ ግፍና በደል ባከማቹት ደመና ምክንያት የሚጥልን የበቀል ዶፍ ዝናብ ሊከላከል የሚችል ጃንጥላ የሠራ አካል እስካሁን በዓለም አልታዬም፡፡
አለባብሰው ቢያርሱ ባረም ይመለሱ እንላለን፤ እናም በግልጽ ነው የሚሰማኝን የምናገረው፡፡ የገዛ ዘመዱ በዚያ መልክ በገሃድ ራሷንም ሳትሸፋፍን ስትመሰክር ሳይ ወሽመጤ ነው የተቆረጠው፡፡ እንደዚህ ዓይነት ራሱ የሰይጣናዊ ምግባር መገለጫ ሆኖ እኔን ከሌላው ሰይጣን ከአቢይ ነፃ አወጣሃለሁ ቢለኝ ምፀት ነው፡፡ ለዚህ ነው ፋኖ እንደግመል ሽንት የኋሊት እየተጎተተ የመከራችን መራዘም፣ የትንሣኤያችንም መዘግየት ዋና ምክንያት ሆኖ እንደምናስተውለው የወቀሳና ስሞታ ሰለባ ሊሆን የቻለው፡፡ እንጂ እንደትግሉ አጀማመር ቢሆንማ ኖሮ ነፃ ከወጣን ሁለተኛ ዓመታችንን ልናከብር ወደ ፈንዲሻ መሸጫ ሱቅ ሄደን ወረፋ በያዝን ነበር፡፡ ደግሞ እኮ ዕድሉ ሆኖ ከአዳነች አበቤና ከአቢይ አህመድ ከነበለጠ ሞላና ከምርኮኛ አሥር አለቃ ጁላ በስተቀር ፋኖን የማይናፍቅ አዲስ አበቤ አልነበረም፤ አሁን ግን ሰው ተስፋ እየቆረጠና የ“እየመጡ ነው” መፈክርም እየደበዘዘ መጥቶ ኢትዮጵያውያን ከፋኖ ይልቅ የማይቀረውንና እንደሰውም የማይሆነውን የእግዚአብሔርን ፍርድ መጠባበቅን መርጠዋል – ለምን ይዋሻል፡፡ የፋኖኣዊ placebo effect ራሱ እየተሸረሸረ መጥቶ ፋኖ በመጥፎ መሪዎቹ በሠራው ስህተት ምክንያት ብዙዎቻችን የተስፋችንን የዲሽ አቅጣጫ እየቀየርን እንገኛለን፡፡ ስለሆነም ለአንድ ወይም ለጥቂት ራስ ወዳዶች ሥጋዊ ፍላጎት ዕርካታ ሲባል በተለይ 60 ሚሊዮኑ አማራና በአጠቃላይ ደግሞ 130 ሚሊዮኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ በቁሙ መቀመቅ መውረድ የለበትምና ኅቡኣን ባለምጡቅ አእምሮ ፋኖዎች ብዙም ሳይረፍድ የምታደርጉትን አድርጋችሁ ይህን ዕልቂት የታወጀበት ሕዝብ በአፋጣኝ ድረሱለት – የምታደርጉትን ስታደርጉ ግን ቆቅ ሆናችሁ እንጂ ዕርግብ ሆናችሁ እንዳይሆን አደራ፡፡ አቢይና የአቢይ ተፈጥሮ ያለበት ሰው ሁሉ ትንሽ ከጠረጠረ ማጣራት ሳያስፈልገው የምግብና የመጠጥ መርዝን ጨምሮ ባገኘው መሣሪያ ያገኘውን መረፍረፍ ነውና ጠባዩ ተጠንቀቁ፡፡ እናም ለሕዝብ ስትሉ ጥቂት ጥፋት ብትሠሩ ምንም አይደለምና ተመካከሩ፡፡
በከንቱ አትውቀሰኝ ወንድሜ፡፡ ምን ማለትህ ነው – 60 ሰው የጫነ የሕዝብ አውቶቡስ መንገድ ላይ ደንቃራ ሆኖ የገባበትን አንድ ሰው ለማዳን ሲል ገደል ገብቶ አንድ ሰው ያድናል ወይንስ አንድ ሰው ገጭቶ 60 ሰው ከሞት ይታደጋል? ንገረኛ! የምን መተፋፈር ነው፡፡ በማይገራ የግል ፍላጎቶቻቸው ኅሊናቸው ታውሮ – በሴት በለው፣ በንዋይ በለው፣ በሥልጣን በለው በሌላ ነገር – ትግሉን የሚያውኩ አመራሮች ካሉ እንዲመለሱ መምከርና ማስመከር ተገቢ ነው፡፡ ካልሆነ ግን ጥበብ በተሞላበት ሁኔታ እነሱን አስወግዶ ሀገርንና ሕዝብን ማትረፍ ቀጠሮ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም፡፡ የነሱ ኢጎ ክፍተት ተደፍኖ አያልቅምና ስንት ሰው እስኪያልቅ እሹሩሩ ይባሉ? ስንት ሀብት ንብረት፣ ስንት ላዕላይና ታኅይ መዋቅር፣ ስንት ትምህርት ቤትና ሀኪም ቤት እስኪወድም ይጠበቅ? የምን እሹሩሩ ነው፤ የምን እሽኮኮ ብሎ መዞርና መሰቃየት ነው፡፡ “ለዚህ ለዚህማ ብልጽግና ምን አለን?” ልል ከጅሎኝ ነበር የሚጠብቀኝን አሽሙርና የብልጽግናነት ፍረጃ ፈርቼ ተውኩት፡፡
የባለጌ አመራሮችን ወግ ገታ አድርገን ወደተዛማጅ ጉዳይ ጎራ ብለን ስለአንድ ጠቃሚ ነጥብ ብናወሳ ደስ ይለኛል፡፡ እሱም የአማራ ፋኖ አንድ አለመሆን የሚሰጠውን ጠቀሜታ በተመለከተ ነው፡፡ የአማራ ፋኖ አንድ አለመሆን ጥቅሙ ጎልቶ እሚታየው እዚህ አካባቢ ነው – የተለያዬ ባሕርይና ሥነ ሕይወታዊ ሥሪት ያላቸው ሰዎች በተለያዬ ሥፍራ የሚገኙ ፋኖዎችን በነፃነት መምራታቸው ለትግሉ በቀላሉ አለመጠለፍ የራሱ አወንታዊ ሚና አለው፡፡ እንዲህም ስንል ለአብነት ፋኖን የሚያውኩት አመራሮች በጊዜ ሂደት በየግዛታቸው እየታወቁ ይመጣሉ – አሁን አካባቢ በሁሉም ግዛቶች እየታወቁ እንዳሉት ማለት ነው፡፡ በአራቱም የአማራ ግዛቶች የሚገኙ ሃቀኛ የአማራ ልጆች በሂደት የአመራሮቻቸውን የንግግርና የተግባር ሥሙርነት እየተረዱና እየለዩ ይመጣሉ፡፡ ሴተኛ አዳሪዋ “አጭበርባሪ አይተኛኝም” ያለችውን አስተማሪ ብሂል የሚያስታውሰውና ለተግባራዊነቱም የሚተጋው ጨዋና አስተዋይ ታጋይ ፋኖ በብኩን አታጋዮቹ ላይ ይነሣል፡፡ በሰርጂካል ምጥን ውስጣዊ ኦፐሬሽንም እነዚያን በፍቅረ ንዋይና በፍቅረ ወሲብ የተመረዙ ወገኖች በዘዴና ትግሉን በማይጎዳ ሁኔታ ያስወግዳል፡፡ ይህ ክስተት እውን እንዲሆን ታዲያ የፋኖ decentralized ውቅር ጠቀሜታ አለው – ውድ ልሂቆቻችን “A blessing in disguise” ወይም “mixed blessing.” ይሉታልኝ ይህን መሰሉን አጋጣሚ፡፡ አንድ ቢሆን ግን በቀላሉ ይጠፋል፡፡ ፈጣሪ ሳይደግስ አይጣላም፡፡ “ሁሉ ነገር ለበጎ ነው” የመባሉ ምሥጢር ትዝ አላለህም እዚህ ላይ? አዎ፣ ወንድም እህቶቼ፡- መታመናችን ለአንድ አምላክ ይሁን እንጂ አምላከ ሰማይ ወምድር በቅርብ ይጎበኘናል፡፡
አሁንና በዚህች አጋጣሚም በቅርቡ ያልኩትን ልድገመው – አማራ ይሄን የከረፋና የጠነባ የኦነግሸኔ ሥርዓተ ካኒባሊዝም ዝንጥ አድርጎ ያሸንፋል፤ ወደመጣበት እንጦርጦስም ይመልሰዋል፡፡ እንዲህ ስናገር ውስጤን ምን ዓይነት ሃሤት እየተሰማኝ እንደሆነ ልገልጸው አልችልም፡፡ ግን ግን… ቢሆንም – “ሃታኡ መሌ – haa ta’u malee” ይላሉ ወንድሞቼ – ልድገመው ቢሆንም ነፃነት በእጅ የድንጋይ ውርወራ ሬዲየስ ውስጥ የምትገኝ መሆኗ ጥርጣሬ ውስጥ ባይገባም የምታስከፍለው ዋጋ ግን ከፍተኛ ነው፡፡ ይህ ዋጋ ሥነ ልቦናዊ ድንዛዜንና ምንግዴነትን ሁሉ ያካትታል፡፡ ለምሣሌ በአሁኑ ወቅት እጅግ ብዙው ዜጋ ብልጽግናንም፣ ፋኖንም፣ ኦነግንም፣ ወያኔንም፣ ኡጉጉሙ ኢትዮጵያንም … ከመጤፍ ሳይቆጥርና ጭርሱን ረስቶ የዕለት እንጀራው ላይ ብቻ ተደፍቶ ነው የሚታዬው፡፡ ይህ ጤናማ አይደለም፡፡ እኔን መሰሎች አንጋፋ ዜጎችን የሚያቃጥለን አንዱና ትልቁ ነገርም ይሄው ነው፡፡ በሌላ ምሣሌ ከ130 ሚሊዮኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይህችን መጣጥፍ የሚያነበው ከመቶ ከበለጠ ተዓምር ነው፡፡ አንድ ሚሊዮን ሕዝብ ያላቸው ሀገራት የኛን የመሠለ ችግር ቢገጥማቸውና አንድ ሰው የኔን የመሠለ መጣጥፍ ቢፖስት 1.5 ሚሊዮን ሕዝብ ያነበዋል ተብሎ ይገመታል – ግማሽ ሚሊዮኑ በድጋሚ ገርቦት ማለቴ ነው፡፡ [ይህን ጽሑፍ ጀምሬ እዚህ ገደማ ደርሼ ዕረፍት ማድረግ ላይ እያለሁ ከደቂቃዎች በፊት ዛሬ የደረሰኝ መረጃ ቅንፍ ከመክፈቴ በፊት የተናገርኩትን የሚያፈርስ ነው፡፡ የክፉ ቀን ደራሼና እጅግ ሲበዛ አስታዋሼ የኢትዮሰማይ ድረገጹ ጌታቸው ረዳ እንደመየለልኝ ከሆነ በትናንትናው ዕለት ብቻ 1636 ሰዎች ጽሑፌን ከእርሱ ድረገጽ እንዳነበቡ ነገረኝ – የዘሀበሻው ደግሞ ቢጣራ ከዚህ እንደሚበልጥ አልጠራጠርም፡፡ በተለጠፈ በአንድ ሰዓት ውስጥ ደግሞ 1002 አንባቢ እንደተመዘገበ አብሥሮኛል – ተመስገን ነው ኧረ]
ጥሩ ነው፡፡ ዋናው ደግሞ ተግባር ነውና ፋኖ እንዲጸዳ፣ ቤቱን እንዲጠርግና እንዲያሰማምር፣ ታጋዮችን በሁሉም ረገድ ለድል እንዲያበቃ፣ የጠላት ሠርጎ ገቦችን እንዲመነጥር ወዘተ. አቅሙ ያላችሁ ችላ አትበሉ፡፡ የነፃነት ትግሉ እየጠራና ይበልጥ እየሠመረ ሲሄድ ዘርና ሃይማኖት ሳይለይ የሁሉንም ሃቀኛ ኢትዮጵያውያን ተሣትፎ ይጠይቃል፡፡ ዘረኝነት ሊጠፋ ጥቂት ጊዜ ቢቀረውም በምኞት የሚጠፋ ነገር የለምና በተለይ ዕውቀት፣ ገንዘብና ሃቀኛ ፋኖዎችን የማግኘት access ያላችሁ ምሁራን፣ ሀብታሞች፣ ታዋቂዎች … በርትታችሁ ተሣተፉ፡፡ ነጻነት መምጣቷ እርግጥ ነው፡፡ ያኔ እንዳንተዛዘብ አሁን ማድረግ ያለብንን እናድርግ – ግን ራሣችንን ጠብቀን፤ (አቢይ ጋ ቀልድ የለም)፡፡ እኔ እንደሆንኩ ዘርፍጤ ነኝ፡፡ ከውሽንፍሩ ከተረፍኩ ማንም እየተነሣ “እንዲህ ነበርኩ፤ እንዲህ አድርጌያለሁ” ቢል መዝገብ ማገላበጣችንና ማጋለጣችን አይቀርም፡፡ ቆነጃጅቱ እየመጡ ነው … እነሱ ሲመጡ ሥራ ላይ የሚውለው ሰውነት ነው – ዝቅ ሲል ደግሞ ኢትዮጵያዊነት፡፡ አሁን አማራ አማራ የምንለው በወቅቱ ቅኝት ለመሄድ ሲባልና የተሻለ አማራጭም በማጣት ነው፡፡ አማራ ጠላቶቹ እንደሚሉት ሳይሆን በቁጥር የሰማይ ከዋክብትና የምድር አሸዋን የሚያስንቅ ሆኖ ሳለ በመቶዎችና በጥቂት ሽዎች የሚገመቱ ከሁሉም ነገዶች በተለይም በፊት ከትግሬና አሁን ከኦሮሞ የወጡ አሰለጥ ደም መጣጮች ሊጫወቱበት የበቃው በአማራነት መደራጀትን ከዘር ሐረግም ከባህልም ከሃይማኖትም ስላላገኘውና ስለሚጠየፈውም እንጂ እንደነሱ ቢደራጅ አንታርክቲካ ድረስ ሊያሳድዳቸው በቻለ ነበር፤ በዚያ ላይ አማራ በሆዳም ልጆቹ ብዛትና ራሳቸውንም ጭምር በመጨረሻው ለማይምራቸው ጠላት በሚያሸረግዱ፣ የገዛ ወገናቸውንም በሚያስጨርሱ የጥቁር ለጥቁር ባንዳዎቹ ኆልቁ መሣፍርትነት አይታማም – በሌላ በዚያ ላይ ደግሞ አማራ is highly porous for gatecrashers and has also been willingly intermingling with other tribes for millennia. በዚያም ሳቢያ አማርኛን የሚናገር ሁሉ አማራ ነኝ እያለ ተመሳስሎ ገብቶ ያጃጅለዋል፤ ይሰልለዋል፤ ለጠላቶቹ ሠይፍም አሣልፎ ይሰጠዋል፡፡ አሁን አሁን ግን የሚያስፈራ አማራ እየተፈጠረ ነው፡፡ ወዮልሽ አማራን ስትጨፈጭፊና ስታስጨፈጭፊ የነበርሽ ሁላ!! (አቤት ስንቱን ቀባጠርኩት! ማበድ ከዚህ በላይ ይኖር ይሆን? አፉ በሉኝ፡፡ አፄ ቴዎድሮስ በሎሬት ፀጋየ ገ/መድኅን ዋቀዮ በኩል “…ሳይነጋ እንዳስመሸሽብኝ ጊዜና ትውልድ ይፍረደን፤ ሳልነቃ እንዳስፈረድሽብኝ … ያም ሆኖ ለራስሽ እንጂ ለኔ ከቶም አታልቅሺ …” ያለው ለካንስ ወዶ አልነበረም፡፡)