January 24, 2025
3 mins read

 የኦህዴድ መራሹ ጅምላ ግድያዎች ስሌት (ሸንቁጥ- ከምዕራብ ካናዳ)

Oromo 6 1 1 1የኦህዴድ መራሹ ብልፅግና  መንግስት  በአማራ እና በኦሮሚያ ክልል በንጹሀን  ዜጎች ላይ እየወሰዳቸው ያሉ የነፃ እርምጃ  ግድያዎች  መንግስት ያሰበውን የፖለቲካ ግብ ያሳካለታል  ወይ ?

በኔ አመለካከት እነዚህ የንፁሃን ዜጎች  የጅምላ ግድያዎች  በሁለት በኩል እንደተሳለ ቢላዎ (double edge sword) ናቸው::

፩- መንግስት እያሰላው ባለው “አሳውን ለመግደል ባህሩን ማድረቅ ስሌት  የንፁሃንን ግድያ እንደ collateral damage አስልቶ ይልቅስ ግድያው እየበዛ ሲመጣ ህዝቡ በመሰላቸትም ይሁን በመሳቀቅ   ነፍጥ ያነሱብኝን ልጆቹን አሳልፎ ይሰጠኛል (flush out ማድረግ እችላለሁ)  የሚል ሂሳብ ነው::

፪- መንግስት ቀደም ሲል በጠቀስኩት ስሌት መሰረት የሚያደርሳቸው የተናጠልም ይሁን የጅምላ ግድያዎች ህዝቡን ” ከቤቴ ፣ ከእርሻ ቦታዬ ፣ ከማምለኪያ ስፍራዬ እየተጎተትኩ የጨካኝ ወታደሮች እና ድሮኖች እሳት እራት ከምሆን አልሞት ባይ ተጋዳይ ልሁን  ገድዬ ልሙት ወደሚል ሲቃ አስገብቶ የሸማቂ ታጋዮችን ቁጥር እጥፍ ድርብ ወደማድረጉ ይሄዳል።

ይሄ ኦህዴድ መራሹ መንግስት ታሪክ ምናባቱ ብሎ አይኑን  በጨው ካላጠበ በስተቀር  ደርግ  አስቦትም ይሁን በተሸረበ ሴራ በአስመራ ጎዳናዎች እና በሀውዜን ባደረሰው እልቂት  ከላይ የጠቀስኩትን ሁለተኛውን የሰይፉን ስለት ነው የጨበጠው:: አልያማ ወያኔም ሆነ ሸአብያ የትኛውን  የትሻለ አማራጭ አቅርበው ህዝቡ አይ ከደርግስ እነሱ ይሻሉኛል ብሎ ተቀላቀላቸው? በርዮተ አለምም ቢሆን በማሌ ርዮታቸው ደርግን ያስከነዱ የነበሩ ናቸው።

ዛሬም እየሆነ ያለው ያው ነው …የዛሬ ስድስት አመት

“ከወያኔስ ሰይጣንም ቢሆን ይምጣ !’ ብለን ነበር… ዛሬ

አብይ” አረ ወያኔ በስንት እጁ” እያስባለን የሚናፈቅ መላእክ አደረገው። …የዛሬ ስድስት አመት ጀዋር መሀመድ የቀኝ. ጠርዝ ረጋጭ አብይ መሀል ነበር …ዛሬ አብይ የቀኙን ጠርዝ ይዞ ጀዋር” እኔ መሀል ነኝ ; ኑ አብረን እንደንስ” እያለን ነው።

አብይ መገንዘብ ያቃተው ይሄ የንፁሀን ኢትዮጵያዊ ያን ግድያ እየሰፋ እና እየጨመረ በሄደ ቁጥር ህዝቡን አስደንግጦም ይሁን አስልችቶ ተገዢ ሊያድርገው የመቻሉን ያህል ለ ቃይ ደንዳና ነቱን (endurance)   ጨምሮ የትግል ምክንያት (cause) ሆኖት ይሄ መንግስት  ባንገቱ የጠለቀውን ገመድ ይባስ እያጠበቀው እንደሚሄድ ነው።

 

 

2 Comments

  1. የኦህዴድ መራሹ ጅምላ ግድያዎች ስሌት

    ኢትዮጵያውያንን ለማሸበር/ ለማስደንገጥ እና ለምዕራቡ ዓለም ኢኮኖሚያዊ “ሾክ ቴራፒ” ( ዘረፋ )ዝግጁ ለማድረግ ነው። በዚህ ክስተት ውስጥ ኦህዴድ ዕድሉን ተጠቅሞ የቆየውን የኦነግን ሀገር የመበታተን ዓላማ ከግብ ለማድረስ ይጠቀማል።

  2. አቶ ሸንቁጥ በእውነቱ ከላይ ያስቀመጥካቸው ሰዎች ፎቶ ጭንቀታቸውን ከመናገሩ በስተቀር ጥሁፍህ ምስጢሩ በእጅጉ ረቅቆብኛል፡፡ እንደው ከዚህ በተሻለ ለተራው ህዝብ በሚገባው ቋንቋ ማቅረብ አይቻልህም ነበር? ለተራውም ህዝብ እዘኑለት እንጅ፡፡ እንግሊዝኛውን ሽሽት እዚህ ብንመጣ አማርኛውም ጀርመን ሁኖብን አረፈው፡፡ አይ የኛ ነገር በሳይበሩም ሳይደላን እንደተንሳፈፍን ልናልፍ ነው ማለት ነው? ሰላም ሁን በርታ እሱን አልገባውም ብለህ ጽሁፍህ አይቋረጥ ብዙ አርበኞች ተሰውረውብናል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከሰሞኑ ታዛቢዎች በተገኙበት ከመንግስት ጋር ውይይት እንዳደረገ እና ለድርድር ዝግጁ እንደሆነ የገለፀው በእስክንድር ነጋ የሚመራው የፋኖ ክንፍ ድርድሩ በውጭ ሀገራት እንዲሆን እየጠየቀ መሆኑ ታውቋል። የመሠረት ሚድያ ምንጮች እንደተናገሩት ታጣቂ ክንፉ ድርድሩ በአውሮፓ

በእሰክንድር ነጋ የሚመራው ፋኖ’ ከመንግስት ጋር ለመደራደር ተዘጋጅቷል

January 26, 2025
እነዶ/ር ደብረፅዮን እና በጠ/ሚ ዐብይ አህመድ በተሾሙት የትግራይ ጊዜያዊ መንግሥት መሪዎች እነጌታቸው ረዳ መካከል የነበረው አለመግባባት ተካርሮ ሰራዊቱን ወደውግንና አስገብቷል። የትግራይ ሐይል አዛዦች ትላንት ባወጡት መግለጫ ውግንናቸው ከእነዶ/ር ደብረፅዮን ጋር መኾኑን አስታውቀዋል።

በትግራይ የተፈጠረው ምንድነው?

January 23, 2025
የድሮ መሪዎች ያላደረጉትን ምሁር ጳጳሳቱ ያላስተዋሉትን ከፈረሰች ጎጆ ከባልቴት ቤት ገብቶ ክብሩን ዝቅ አድርጎ ውሀዋን ጠጥቶ ምግቧንም ተጋርቶ ያላለቀሰ ሰው ያንን ትይንት አይቶ ማን ይኖራል ከቶ? በዉሸት ፈገግታ ፊቱን አስመስሎ ፀሀይ የበራበት

ሰው በሰውነቱ – ከ ይቆየኝ ስሜ

Go toTop