የኦህዴድ መራሹ ብልፅግና መንግስት በአማራ እና በኦሮሚያ ክልል በንጹሀን ዜጎች ላይ እየወሰዳቸው ያሉ የነፃ እርምጃ ግድያዎች መንግስት ያሰበውን የፖለቲካ ግብ ያሳካለታል ወይ ?
በኔ አመለካከት እነዚህ የንፁሃን ዜጎች የጅምላ ግድያዎች በሁለት በኩል እንደተሳለ ቢላዎ (double edge sword) ናቸው::
፩- መንግስት እያሰላው ባለው “አሳውን ለመግደል ባህሩን ማድረቅ ስሌት የንፁሃንን ግድያ እንደ collateral damage አስልቶ ይልቅስ ግድያው እየበዛ ሲመጣ ህዝቡ በመሰላቸትም ይሁን በመሳቀቅ ነፍጥ ያነሱብኝን ልጆቹን አሳልፎ ይሰጠኛል (flush out ማድረግ እችላለሁ) የሚል ሂሳብ ነው::
፪- መንግስት ቀደም ሲል በጠቀስኩት ስሌት መሰረት የሚያደርሳቸው የተናጠልም ይሁን የጅምላ ግድያዎች ህዝቡን ” ከቤቴ ፣ ከእርሻ ቦታዬ ፣ ከማምለኪያ ስፍራዬ እየተጎተትኩ የጨካኝ ወታደሮች እና ድሮኖች እሳት እራት ከምሆን አልሞት ባይ ተጋዳይ ልሁን ገድዬ ልሙት ወደሚል ሲቃ አስገብቶ የሸማቂ ታጋዮችን ቁጥር እጥፍ ድርብ ወደማድረጉ ይሄዳል።
ይሄ ኦህዴድ መራሹ መንግስት ታሪክ ምናባቱ ብሎ አይኑን በጨው ካላጠበ በስተቀር ደርግ አስቦትም ይሁን በተሸረበ ሴራ በአስመራ ጎዳናዎች እና በሀውዜን ባደረሰው እልቂት ከላይ የጠቀስኩትን ሁለተኛውን የሰይፉን ስለት ነው የጨበጠው:: አልያማ ወያኔም ሆነ ሸአብያ የትኛውን የትሻለ አማራጭ አቅርበው ህዝቡ አይ ከደርግስ እነሱ ይሻሉኛል ብሎ ተቀላቀላቸው? በርዮተ አለምም ቢሆን በማሌ ርዮታቸው ደርግን ያስከነዱ የነበሩ ናቸው።
ዛሬም እየሆነ ያለው ያው ነው …የዛሬ ስድስት አመት
“ከወያኔስ ሰይጣንም ቢሆን ይምጣ !’ ብለን ነበር… ዛሬ
አብይ” አረ ወያኔ በስንት እጁ” እያስባለን የሚናፈቅ መላእክ አደረገው። …የዛሬ ስድስት አመት ጀዋር መሀመድ የቀኝ. ጠርዝ ረጋጭ አብይ መሀል ነበር …ዛሬ አብይ የቀኙን ጠርዝ ይዞ ጀዋር” እኔ መሀል ነኝ ; ኑ አብረን እንደንስ” እያለን ነው።
አብይ መገንዘብ ያቃተው ይሄ የንፁሀን ኢትዮጵያዊ ያን ግድያ እየሰፋ እና እየጨመረ በሄደ ቁጥር ህዝቡን አስደንግጦም ይሁን አስልችቶ ተገዢ ሊያድርገው የመቻሉን ያህል ለ ቃይ ደንዳና ነቱን (endurance) ጨምሮ የትግል ምክንያት (cause) ሆኖት ይሄ መንግስት ባንገቱ የጠለቀውን ገመድ ይባስ እያጠበቀው እንደሚሄድ ነው።