January 23, 2025
3 mins read

በትግራይ የተፈጠረው ምንድነው?

473808061 1014575744050860 3414886213081821098 n

እነዶ/ር ደብረፅዮን እና በጠ/ሚ ዐብይ አህመድ በተሾሙት የትግራይ ጊዜያዊ መንግሥት መሪዎች እነጌታቸው ረዳ መካከል የነበረው አለመግባባት ተካርሮ ሰራዊቱን ወደውግንና አስገብቷል።

የትግራይ ሐይል አዛዦች ትላንት ባወጡት መግለጫ ውግንናቸው ከእነዶ/ር ደብረፅዮን ጋር መኾኑን አስታውቀዋል።

የትግራይ ሐይል አዛዦች በዶክተር ደብረፅዮን የሚመራው የህወሓት ክንፍ በትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ያለው ሃምሳ ሲደመር አንድ ድርሻ እንዲረከብ እንደሚሹ አቋማቸውን ይፋ አድርገዋል። ከዚህ በተጨማሪ በትግራይ ያሉ ታጣቂዎች በትግራይ ሰላም እና ፀጥታ ሴክሬታሪያት ስር እንዲሆኑ፥ ከዚህ ውጪ በሆነ ላይ ግን እርምጃ ይወሰዳል ብለዋል።

በሌላ በኩል ፓርቲውን ለማፍረስ እና አመራሩን ለመበተን እያሴሩ ነው በማለት ህወሓት የኢትዮጵያ መንግስትን እና የምርጫ ቦርድን ወንጅሏል። በዶክተር ደብረፅዮን የሚመራዉ የህወሓት ክንፍ ቁጥጥር ኮምሽን ከትላንት በስቲያ ባወጣው መግለጫ በአስቸኳይ የህወሓት ሕጋዊነት ሰውነት ሊመለስ ይገባል ብሏል።

በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ትላንት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ

የትግራይ ሐይል አዛዦች ያስተላለፉት ውሳኔ በትግራይ ሥርዓት አልበኝነትን የሚያነግስ ነው በማለት አስቸኳይ የካቢኔ ስብሰባ መጥራቱን ይፋ አድርጓል።

መግለጫው እንደሚለው የትግራይ ሐይሎች ከፍተኛ አዛዦች “ከተልእኳቸው ውጭ ለአንድ ሕገወጥ ቡድን ወግነው ግዚያዊ አስተዳደሩን የማፍረስ፣ ስርዓት አልባነት የማንገስ እና ሰራዊት የመበተን ግልፅ እንቅስቃሴ እያደረጉ መሆናቸውን አሳውቀዋል” ብሏል።

የትግራይ ሐይል አዛዦች በትላንትናው ዕለት ያስተላለፉትን ውሳኔ ግዚያዊ አስተዳደሩ የማያውቀውና “ሕጋዊ ይሁን ሞራላዊ ቅቡልነት የሌለው” ሲል ያመለከተው የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር መግለጫ፤ ከዚህ በተጨማሪ የፕሪቶርያ ውልንም ለአደጋ የሚያጋልጥ እና ኃላፊነት የጎደለው ብሎታል።

(ከጀርመን ድምፅ ተወስዶ የተቀናበረ)

3 Comments

  1. የፈጣሪ ረቂቅ ስራው እንዴት ይመረመራል? እኛ ዛሬ ካልሆነ ብለን ያዙኝ ልቀቁኝ እንላለን አምላክ ደግሞ ጠብቅ የኔ የጊዜ ሰሌዳ ዛሬ አይደለም ይልሃል፡፡ እነዚህ የቀን ጅቦች የሃገሪቱን አጥንት ግጠው ታይቶ ተሰምቶ በማይታወቅ ሁኔታ አገር ተሰብስቦ አንድ እንዳይሆን በህገ መንገስት አገር በትነው፤ የሃገሪቱን ሃብት እንዳሻቸው ሲጫወቱበት ትግሬ ቁጥሩ አንሷቸው ተጎራብች ክልሎችንም የትግሬ ዜግነት ሰጥተው ፤የሚጠብቃቸውን መከላከያ አርደው ይኸው የጥጋባቸው ስበት አመዝኖ ነገሩ ሁሉ ተጠቅልሎ ወደ እነሱዉ ሄደ፡፡

    ታዲያ ምን ያደርጋል ትላንት ምንም እንዳላደረጉ ሁሉ ዛሬም ተነቅለው አዲስ አበባ፤ ባህር ዳር፤ ጎንደር ፈልሰው ገብተዋል መቼም ይሉኝታ እንሱ ዘንድ የለችምና፡፡ ነገ ከጉዳታቸው ሲያገግሙ ወደ ተሰሩበት ተንኮልና ሸር ይመለሳሉ፡፡ እስቲ የአቶ ሰረቀ ብርሃን ጸሎት የት እንደሚያደርሳቸው ዝም ብሎ ማየት ነው፡፡ እንደው ሰው አይውጣልህ ተብሎ እንደተረገመ ሁሉ ጠቅላላ ሁሉም ከአንድ ፋብሪካ እንደተሰራ ሳሙና አንድ አይነት ሲሆን ይገርማል፡፡ ባለፈው እናቶች አባቶች በእምብርክክ ሲለምኑዋቸው የተምበረከኩትን እየረገጡ ያለፉት በታሪክ ተመዝግቦ ይቀመጥ ሳይውል ሳያድር ስብሃት ነጋና ቡድኑ ተበለሻሽተው ከዋሻው ሲወጡ ያለውን ትርኢትም አዳምሮ መመልከት ለቋሚ ጥሩ ግንዛቤ ይሰጣል፡፡

  2. አይ ጊዜ ትላንት ጌቾን ያየ ደ/ጽዮንን ያየ ዛሬ ይሄ ይመጣል ብሎ ይጠረጥራል? አንዱ ጦርነት ባህላችን ነው ሲል ሰየ አብረሃ ጦርነት እንሰራለን ይልሃል አቶ ጻድቃን ደግሞ በታላቅ ኩራት ሌላ ይልሃል አቶ ታደሰ ወረደ ጦሩን አሽመደመድነው ይልሃል፡፡ እረ ተው ቢባሉ አንት ሽንታም ማለት ጀመሩ፡፡ ታዲያ ያ ሁሉ ጥጋብ አልፎ ፕሪቶሪያ ላይ ለጌቾ ያሉህን ሁሉ ፈርመህ ነብሳችንን አድነው ብለው ተማጸኑ፤ ያለንን መሳሪያ ሁሉ እናወርዳለን ተረክቡን አሉ፤ ሬድዋን ሁሴን የመኖር ስጋት አለባቸው አያስረክቡም አሉ ሳይውል ሳያድር ጥጋባቸው ባረቀባቸው፡፡ አሁን አሁን ላይ ጌቾም ነብሷ ተጨንቋል ደ/ጽዮንም ጦርነት ቢከፈት የሚንደባለሉ ትግሬዎች ላይወጡልኝ ይችላሉ ብሎ ስጋት በስጋት ሁኗል ተንደባላዮቹም በየሃገሩ አይን ይብላችሁ ሲባሉ ቀሪውም ትያትሩ ገብቶት ምላሱን ቆልፎ ቁጭ ብሏል፡፡ እስቲ የሚሆነውን ማየት ነው በርቱ

  3. ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ ሁኖ ነው እንጅ አብይ የሾመውን ባለስልጣን እንዲህ እንዳይሆን አድርጎ ማባረር ምን ይባላል እዚህ ላይ አይቆሙም እኮ ጻድቃንንም አብረው ሳይሸኙት አይቀሩም፡፡ ጌቾ በዛ በክፉ ጦርነት እንኳን እንዲህ ተጎሳቁሎ አላየሁትም ራያነቱን መዘውበት ይሆን? ነግረን ነበር ሰሚ ጠፋ እሱም ተወደድኩ ብሎ ከቄሱ በላይ ቄስ ሆነ እንግዲህ ማን ያውጣህ አብይም ሆነ ስብሃት፤አረናል ሆነ ባይቶና(ባይተዋር) ከኔ ጋር ይቆማሉ ብለህ አታስብ በእኛ በኩል ስራህ ያውጣህ ነው የምንለው ብዙ ፋይል ውስጥ ያስቀመጥናቸው ቪዲዮ፤ኡዲዮና ማህደሮች ስላሉን፡፡ ንስሃ እንዳትገባ ለነብሱ ያደረ ቄስ በዚያ በኩል የለም፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

የኦህዴድ መራሹ ብልፅግና  መንግስት  በአማራ እና በኦሮሚያ ክልል በንጹሀን  ዜጎች ላይ እየወሰዳቸው ያሉ የነፃ እርምጃ  ግድያዎች  መንግስት ያሰበውን የፖለቲካ ግብ ያሳካለታል  ወይ ? በኔ አመለካከት እነዚህ የንፁሃን ዜጎች  የጅምላ ግድያዎች  በሁለት በኩል እንደተሳለ ቢላዎ (double edge sword) ናቸው:: ፩- መንግስት እያሰላው

 የኦህዴድ መራሹ ጅምላ ግድያዎች ስሌት (ሸንቁጥ- ከምዕራብ ካናዳ)

January 24, 2025
የድሮ መሪዎች ያላደረጉትን ምሁር ጳጳሳቱ ያላስተዋሉትን ከፈረሰች ጎጆ ከባልቴት ቤት ገብቶ ክብሩን ዝቅ አድርጎ ውሀዋን ጠጥቶ ምግቧንም ተጋርቶ ያላለቀሰ ሰው ያንን ትይንት አይቶ ማን ይኖራል ከቶ? በዉሸት ፈገግታ ፊቱን አስመስሎ ፀሀይ የበራበት

ሰው በሰውነቱ – ከ ይቆየኝ ስሜ

የአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የነበረው እና አሁን ላይ በአማራ ፋኖ በጎጃም የሁለተኛ (ተፈራ ) ክፍለጦር ሰብሳቢ የነበረው ፋኖ ዮሐንስ አለማየሁ በክብር ተሰዋ። የአማራ ህዝብ የተጋረጠበትን የህሎና አደጋ ለመቀልበስ ያለ

ከአማራ ፋኖ በጎጃም የተሰጠ የሐዘን መግለጫ ታጋይ ይሰዋል ትግል ይቀጥላል !

January 22, 2025
Go toTop