December 17, 2024
6 mins read

በግርግር 5 ሽህ ካሬ ሜትር ቦታ ቅርጥፍ አድርጎ የበላው የትናትናው የቲቪ ሪፖርተር ያዛሬው ሚሊኒየር የግሩም ጫላ አስቂኝ ቃለ ምልልስ

470222985 988241926684242 7031984139796941723 n
“30 አመት አሜሪካ ውስጥ ታክሲ እየነዳህ እዚህ መጮህ አይቻልም” አነጋጋሪው የግሩም ጫላ ቃለ ምልልስ
***
የቻይናው “ሴጂቲኤን” ቴሌቪዥን ጣቢያ ወኪል ጋዜጠኛ (correspondent) የሆነው ግሩም ጫላ ለብዙዎች አነጋጋሪ የሆነው ቃለ ምልልስ ከሰሞኑ አካሂዷል፡፡
አላይቭ ቶክ ከተሰኝ ፖድካስት ጋር ቃለ ምልልስ ያደረገው ይህ ጋዜጠኛ የብልፅግና መንግስት ታማኝ ሰው ነው በሚል ስሙ ይነሳል፡፡ ለዚህ ደግሞ ከጥቂት አመታት በፊት “GTNA” የተባለ አፍሪካን የሚወክል ቴሌቪዥን ጣቢያ ለመመስረት አዲስ አበባ ውስጥ 5 ሽህ ካሬ ሜትር ቦታ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መረከቡን እና እስካሁን የቴሌቪዥን ጣቢያው ነገር የውሀ ሽታ ሆኖ መቅረቱን በማሳያነት ያነሳሉ፡፡
ያም ሆነ ይህ ግሩም በዚህ ቃለ ምልልሱ የልማት ተቃዋሚ ናቸው በሚል የፈረጃቸውን ሀይሎች በጠንካራ ቃላት ተችቷል፡፡ በዚህ ትችት በዋነኝነት ዲያስፖራው ተቆጥቷል፡፡
“አሜሪካ ውስጥ እጅግ በተደጋጋሚ ሰልፍ በመውጣት የሚታወቁት ኢትዮጵያዊያን ናቸው” ሲል የሚናገረው ግሩም – “በተለያዩ መሪዎች ዘመን የተቃውሞ ሰልፎች በተደጋጋሚ ተደርገዋል” ሲል ይሞግታል፡፡ “አሳዛኙ ነገር ሰልፍ ስንወጣ ብዙ የሆንን መሰለን እንጅ አሜሪካ ውስጥ ሰፊ የዳያስፖራ ቁጥር ካላቸው 10 የአፍሪካ ቀዳሚ ሀገራት ተርታ እንኳን አንመደብም” ሲል ሞግቷል፡፡
“እረ ተዉ – ሰው ይታዘበናል” ሲል ሰልፍ የሚወጡትን ዳያስፖራዎች የሞገተው ግሩም “በመሰረቱ ለውጥ የሚመጣው በዚህ መንገድ አይደለም፡፡ ጀግና ሰው የሚያወራውን ይተገብራል፡፡ በኢኮኖሚ ሀገራችን አልተለወጠችም ብሎ የሚሞግት ዳያስፖራ ሀገር ውስጥ ግባና ሰርተህ አሳየን” ሲል በእልህ ሲሞግት ይታያል፡፡
ጋዜጠኛው “30 አመት በአሜሪካ ታክሲ እየነዳህ እዚህ መጮህ አይቻልም” ሲል ክልከላ ያስቀምጣል፡፡ አክሎም “ይሄን በድፍረት የምናረው ከ0 – Hero የደረስኩ ሰው በመሆኔ ነው” በማለት ይገልፃል፡፡ “ዛሬ የአሜሪካን ህልም እዚህ ሀገር ውስጥ መኖር ጀምረናል” የሚለው ግሩም ጫላ “ብዙ ሰው እንዲለወጥ መንገድ መክፈት አለብን፣ አነሱ የሚኖሩበትን ምእራባዊያን ሀገራት መንግስታት ያማከርን ሰዎች አለን፣ ሰርተን የተለወጥን – ያገኝን ሰዎች አለን፣ ይሄንን ዋጠው እመነው” ሲል ሞግቷል፡፡
“ይሄን ያሳካነው የጠቅላይ ሚንስትሩ ጓደኛ ስለሆንኩ፣ የከንቲባው ዘመድ ስለሆንኩ ሳይሆን ስለቻልኩ ነው ያደረግኩት” ሲልም ተደምጧል፡፡ ኢትዮጵያው ውስጥ የሚሰራ ሰው ይወረፋል እንጅ አይደነቀም ሲል የሚከራከረው ግሩም ጫላ – በሌላ አፍሪካ ሀገር ግን ሰርቶ የተለወጠ ሀብታም እጅግ ይከበራል ሲል ቁጭቱን ገልጾአል፡፡
“ሀገር የጋራ ነው፡፡ የምንለወጠው በጋራ ስንሰራ ነው” በማለት ለዚህ ደግሞ ሁለት አማራጭ እንዳለ ይጠቁማል፡፡ አንደኛው “ለውጡ እንዲቀጥል ማገዝ ሁለተኛው ከማደናቀፍ ተቆጥቦ አፍን መዝጋት ነው” ሲል መክሯል፡፡
“የኮሪደር ልማትን መቃወም ጤነኝነት አይደለም – በዚህ ልማት የፖለቲካ እና አስተዳደራዊ በደል የሚደርስባቸውን – ቤት እና የንግድ ሱቃቸው ለሚያጡት ወገኖች መከራከር ግን ወንጀል አይደለም” ሲልም ተከራክሯል፡፡
“በደፈናው አሜሪካ ተቀምጦ ካዛንችስ ፈረሰ – ቄራ ፈረሰ የሚለው እና የኮሪደር ልማት የሚቃወም ሰው ግን ጤነኛ አእምሮ የለውም” በማለት የተቸው ግሩም ጫላ “ዱባይ ሄደን የምንዝናና ሰዎች እስከ መቼ በቆረቆዘ (ghetto) ከተማ እና ሀገር ውስጥ እንድንኖር ትፈልጋላችሁ” በማለትም ነው የገለጸው፡፡
(ሸገር ታይምስ)

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop