በአማራ ክልል በፌደራል መንግሥት ሠራዊትና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በሚካሄደው ግጭት 4,5 ሚሊየን ሕጻናት በጦርነቱ ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸው ተገለጸ። መምህራን መሰደዳቸው እንዲሁም ቀየው በጦርነት እና በሰው አልባ አውሮፕላን ማለትም ድሮን ጥቃት መታረሱ አዲስ አበባ ላይ የተካሄደው በአማራ ክልል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መድረክ ይፋ አድርጓል።
በክልሉ 969 የሚደርሱ የጤና ተቋማት መውደማቸውን ያመለከተው መድረኩ ይህ ቁጥር በሰሜኑ ጦርነት ወቅት የተጎዱትን እንደማይጨምርም ገልጿል። በጤና ተቋማቱ ላይ የሚደርሰው ችግር አሳሳቢነቱ መቀጠሉም ተመልክቷል።
በክልሉ በጦርነት የወደሙ ተቋማትን መልሶ ለማቋቋም ዓለም አቀፍ ተቋማት ጫና እንዲያደርጉ በአማራ ክልል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መድረክ ጥሪ አቅርቧል።
DW