September 26, 2024
9 mins read

 የአብይ አስተዳደርና የዶ/ር ብርሃኑ አኒ-ሚኒ-ማኒሞ

birhanu m000የጠ/ሚ አብይን የ2017 ዓ.ም. እንኳን አደረሳችሁ መልእክትን ከፌስቡክ ገጻቸው ላይ አነበብኩት፡፡ዘመኑ ላይ ተፈላሰፉበት ወይስ ምንድን ነው ነገሩ? ዘመን እድል ነው አሉን፡፡ እድል ማለት እንደ አማርኛው መዝገበ ቃላት ትርጉም ከሆነ እጣ ክፍል፣ ግንባር ወይም ድርሻ ማለት ነው፡፡

ለመሳሌ በአንድ አካባቢ ያለ አንድ ጋሻ የገበሬ መሬት ተሸንሽኖ ለአስር ገበሬዎች በእጣ ይታደላል እንበል፤ ለወንዙ የቀረበ መሬት አለ፡፡ ሜዳማ መሬት አለ፡፡ እንዲሁ ተዳፋት የሆነና ገደልስር ያለም ሊኖር ይችላል፡፡ ከዚህ ውስጥ ውሃ ገቡን ወይንም ሜዳማውን እድለኞች የሆኑ ያገኙታል፣ ይታደሉታል፡፡ እድለ ቢሱ ደግሞ ገደላማው ሸጥ ስር ይደርሰዋል፡፡

እንግዲህ አንዱ ምርቱን በቀላሉ ሲሰበስብ መጥፎ መሬት የደረሳቸው ደግሞ በብዙ ትጋትና ትግል እህላቸውን ያመርታሉ፤ ሰብላቸውን ይሰበስባሉ ማለት ነው፡፡ ቀጠል አድርገው፣ ዘመንን(እድል የሆነውን ማለት ነው) እግዚአብሔር ለሁሉም በእኩልነት ይሰጣል ይላሉ ጠ/ሚሩ፡፡ ይህን ብለውም አያበቁም፤በአግባቡ ላልሰራበት ዘመን መዓት ነው፤ በአግባቡ ለሰራበት ደግሞ ዘመን ምህረት ነው ይላሉ፡፡

በአውሎና በወጀብ ውስጥ ሆነን  አስገራሚ ስራዎችን እንድንሰራ የፈቀደ እግዚአብሄር ዛሬም፣ ነገም ከእኛ ጋር ነው ይሉና መስራት የእኛ ማከናወን ደግሞ የእሱ ነው ሲሉ ነገራቸውን ይቋጫሉ፡፡ እዚህ ላይ ውስጠዘው የእሳቸው ተቀዋሚዎች ሁሉ ወጀብ ፈጣሪ፣አውሎ ንፋሶች የእግዚአብሔርን አላማና እቅድ የሚገዳደሩ የሴይጣን ልጆች ናቸው ማለት ነው፡፡

ሐይማኖት ላለው ሁሉ እንዲህ ያሉ ቃላት ተደጋግመው ሲነገሩት ቀስ ብሎ የሚሰርጽበት (Subliminal message) ተቀዋሚዎቼ አጋንንት ናቸው የሚል መልእክት ነው፡፡ ዘመን የሰራባቸው የሚሏቸው በሰነፍ ገበሬ የተመሰሉት መዓት የመጣባቸው ብለው የሚጠቅሷቸው ለስድሰት አመታት ያህል እየዞሩ የገደሏቸው አማራዎች፣ትግሬዎች፣ጉራጌዎች፣ጌድሆዎች፣ጋሞዎች፣ ኦሮሞዎች…ናቸው፡፡ ፈጣሪ (የሳቸው?) ካለላቸው ደግሞ ኤርትራንም ሄደው ይጨምራሉ፡፡

እስኪ አብይ ከወያኔ ምን አይነት ዘመንና ግዜ ነበር የተረከቡት? አፈናና አስራት የነበረበት ቢሆንም የወያኔ ግዜ ዘረፋ በመንግስት በግልጥ እንዲህ የታወጀበት ግዜ አልነበረም፡፡ ዜጎችም ከሞላ ጎደል ወጥተው ገብተው መስራት ይችሉ ነበር፡፡ ግድያውም እንዲህ የትየለሌ አልደረሰም፡፡ እሳቸው ወደ ስልጣን ሲመጡም ህዝቡ፤ ትግሬው፣ ኤርትራውና ሃገር ውስጥ ያለው ሁሉ ግልብጥ ብሎ ነበር የተቀበላቸው፡፡

ውለው አድረው እነ ጀነራል ከማል ገልቹ እንደነገሩን አነ አብይ የመንግስት መዋቅርን ተጠቅመው ሸኔን አስታጠቁ፡፡ ህዝቡንም እንደ መንግስትና አማጺ ሆነው አሸበሩት፤ ገደሉት፡፡ ይህ በመላው ኦሮሚያና አዲስ አበባ ተፈጻሚ ሆኗል፤ እየሆነም ነው፡፡ አማራው ደግሞ የእዚህ ጥቃት አይነተኛ ሰለባ ነው፡፡ ሸኔ የደምቢዶሎ ዩንቨርስቲ ሴት ተማሪዎች ሲያግትና ሲሰውር፣ ጠ/ሚ ወጥተው፣ ተማሪዎቹ ለመታገታቸው ማስረጃ እንደሌላቸው ነው የነገሩን፡፡

ፈተው የለቀቋቸውን አራዊቶች  እነ አብይ አሁን መቆጣጠር አቅቷቸዋል፡፡ አሁን አሁን ብልጽግና ለራሱ ደንታ ሲል አስር ግዜ ሲቋጥር ሲፈታ የነበረው የፖለቲካው ቋጠሮ ውል ለእራሱ ጠፍቶበታል፡፡ ከእዚህ በኋላ ከብልጽግና ምንም የሰላም ነገር አይጠበቅም፡፡ ለዚህ ማሳያው ጠ/ሚሩ ሱማሌ ውስጥ የፈጠሩትን የፖለቲካ ውጥንቅጥ መመልከት በቂ ነው፡፡ ገና ብዙ-ብዙ ግንባር ይፈጥሩልናል፡፡

ዶ/ር ብረሃኑ ነጋ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ወስደው በ2017 ዓ.ም. ወደ ዩነቨርሲቲ የሚገቡ ተማሪዎች አስመልክቶ መግለጫ ሲሰጥ፣ እንዲህ አለ፡፡ ለፈተና ከተቀመጡት 845000 ተማሪዎቸውስጥ 422500 ያክሉ 26 ከ 100 በታች ነው ያገኙት፡፡ ይህ ደግሞ አብዛኛው ተማሪ እንደው ዝም ብሎ ኢኒ-ሚኒ-ማኒሞ ብሎ ፈተናውን ቢሞላ ሊያገኘው የሚችለው ውጤት ነው፡፡

ዶ/ር አብይ ወደ ስልጣን ላይ ሲወጡ 6ኛ ክፍል የነበሩት ተማሪዎች እኮ ናቸው አሁን የ12ኛ ክፍል ውጤታቸው እንዲህ የሆነው፡፡ ዶ/ር ብርሃኑ የት/ሚ ሚኒሰተር ሆኖ ይኸው አራት አመት እየሞላው ነው፡፡ ይህን ያህል የትምህርቱ ጥራት ሲወድቅ ምን ይሰራ ነበር?

እንግዲህ ይህች ኢኒ-ሚኒ-ማኒሞ ያላት ቃል ወክላ የገባችበት የአማርኛ ቃል “ነሲብ” የሚለውን ነው፡፡ ነሲብ ማለትን የአማርኛው መዝገበ ቃላት ሲተረጉመው እንዲህ ይላል፤ ያልተለካ፣ያለተመዘነ የግምት አስተያት፡፡ ከራሴ ተሞክሮ አንዳንድ ተማሪዎች የጥያቄዎቹ መልስ ምርጫዎች A,B,C,D አራት በመሆናቸው፣ ቅንድባቸውን እየነጩ ይመልሱ ነበር፡፡ አንድ ፀጉር ከተገኘ=A፣ ሁለት ፀጉር ከተገኘ=B፣ ሶስት=C፣ አራት=D  ይህ ነው እንግዲህ የነሲብ መልስ የሚባለው፡፡

እንዲህ አይነቱ ምርጫን በነሲብ መመለስ በሳቸው ግዜ ኢኒ-ሚኒ-ማኒሞ ተብሎ ይጠራ እንደነበር አላውቅም፡፡ የቃሉ መነሻ ግን ኦሮምኛ ይመስለኛል፡፡ ይኸውም “አነ ናማ ናማ አኒሞ” ትርጉሙም እኔ የሰው ልጅ ነኝ፣ እሱ ግን አየውቅም ነበር እንደማለት ነው፡፡ ይህ ቃል ከዶ/ር ብርሃኑ አፍ ድንገት አምልጦ የወጣ ቃል ነው ወይስ ሁን ብሎ በለሆሳስ ሊያስተላልፈው የፈለገው መልእክት አለ? ቢያብራራው?

መቼም ያ የኢሕአፓ ፓርቲ ዘመን ትውልድ እኮ የማይሰራው ነገር አልነበረም፡፡ በኢሕአፓ ግዜ የኢለመንተሪ ተማሪ ሳለን የሁለተኛና ሶስተኛ ክፍል ተማሪዎች ሆነን ኢሕአፓዎቹ መምህራኖቻችን መዙሙር ያዘምሩን ነበር፡፡

ግባ ጫካ ተው ግባ ዱር

ነጻነትን ሃርነትን ለማሰከበር፡፡

የኢሕአፓ አንበሳ አቅራራ አገሳ

በዱር በገደል ብረት አነሳ…

2 Comments

  1. ብሬ ምን ብትለው ተዋርዶ አጎምብሶ በፎቶው እንዳየኸው ክብሩን ሽጦ አሜሪካኖች አይዞህ ጠሚኒስቴር ትሆናለህ ያሉትን እየጠበቀ ነው። በፎቶው ከታዩት መሀል ሽማግሌው እሱ ነው ኮሜዲያኑም እሱ ነው ቸገረው እንዳይባል ሀብታም ነው ይሉታል። ባደረሰው ጥፋት ሁሉ ጸጸት አይታይበትም ግርማ ሰይፉ ጋር ኢዜማ ነው አዚማም የተባለ ድርጅት ይዘው ይንገታገታሉ።ልብ ይስጣቸው እንደ ሆዳቸው ሁሉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

193730
Previous Story

የካንሰር መድሀኒት ፈጣሪው ዶ/ር ሰለሞን ታደሰ ጋር የተደረገ ቆይታ

Esemecu
Next Story

የኢሰመኮ ሪፖርት እጅግ አሳዛኝና አስደንጋጭ ነው። የአብይ አህመድ ሰራዊት በአማራ ክልል በሶስት ወራት ብቻ የፈፀመው ጭፍጨፋ በመንግስታዊው ኢሰመኮ ሪፖርት ይፋ ሁኗል።

Latest from Blog

የኢሰመኮ ሪፖርት እጅግ አሳዛኝና አስደንጋጭ ነው። የአብይ አህመድ ሰራዊት በአማራ ክልል በሶስት ወራት ብቻ የፈፀመው ጭፍጨፋ በመንግስታዊው ኢሰመኮ ሪፖርት ይፋ ሁኗል።

©ሰኔ 2 ቀን 2016 ዓ.ም. ሌሊት በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላት ከክልሉ አዊ ብሔረሰብ ዞን፣ ቲሊሊ ከተማ አሽፋ ቀበሌ እንደወጡ የመንግሥት የጸጥታ አካላት ወደ ቀበሌው በመግባት ሰኔ 3 ቀን

የባልደራስ ፓርቲ መግለጫ: የአዲስ አበባ ህዝብ የብልፅግና መንግስት የቤት ፈረሳ ይበቃል ሊል ይገባል

ከባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ የኦህዴድ ብልፅግና  የጎጥ ፖለቲካ ወላጅ አባቱን ተክቶ አራት ኪሎን ከተቆጣጠረ ስድስት አመታትን አስቆጥሯል። በዚህ ሁሉ ጊዜ ከሀሰት ትርክት የተወለደ የጥላቻ ፓለቲካን በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች፣ በከፋ መጠንና
Go toTop