የለም እስቲባል ድረስ አማራ ራሱን እረስቶ ስለኖረ ዛሬ የህልውና አደጋ ብቻ ሳይሆን መቀበርያ እያጣና የተቀበረውም በግንዲር እየተዛቀ ሲጣል ይውላል፡፡ በቋንቋና በዘራቸው ተደራጅተው ቋንጃህን ስልንስብር መጣን ሲሉትም ምሁር ተብዬው “ለኢትዮጵያ ስንል፣ እንደነሱ አናንስም፣ ወዘተርፈ” የሚሉ ድስኩሮችና ሰበቦች እየደረደረ አማራ ተደራጅቶ ራሱን ስላልተከላከለ ዛሬ ላለበት የመከራ ዘመን እንደ ደረሰ ይታወቃል፡፡ ከዚህ የመከራ ዘመን አማራ ትልቅ ዘላለማዊ ትምህርት መቅሰም ሲኖርበት አንዳንዱ ከንቱ አንሁም እርስ በርሱ መናከሱንና መንዘላዘሉን ቀጥሏል፡፡
ከግማሽ ክፍለ ዘመን የከፋ የመከራ ዘመናት በኋላ እንኳ አማራ በዘሩ ምክንያት የግፍ ሰለባ መሆኑን ተቀብሎ ታሪክ የሚጠይቀውን ኃላፊነት ተወጥቶ እንዳያልፍ ሰበብ የሚደርድር የደነዘዘ ሆዳም አማራ ዛሬም ሞልቷል፡፡ ለምሳሌ ጭራቆች የሚሰሩትን ታሪክ የማይረሳው ወንጀል ለመሸፋፈን አንዳንድ ተአማራው አይደለንም የሚሉ “ግፍ የተሰራባቸው” ሰዎች በሕዝብ መገናኛ ብቅ ብቅ እያደረጉ ሲያስቀባጥሩ ሆዳሙ አማራ “የተፈናቀለው፣ ቤቱ ወይም መቃብሩ የፈረሰው እኮ የአማራው ብቻ አይደለም” የሚል ጅል ሰበብ ይደረድራል፡፡
ጅልና ሆዳም አማራ ለግማሽ ክፍለ-ዘመን በአማራ ዘንድ የተሰራውን ግፍ አሰላስሎ፣ አሁንም የሚሰራውን ግፍ በጥሞና አጢኖ ወደ ፊት የታቀደውንም ቁማር ለመተንበይ የሰፋው ከርሱ ይጋርደዋል፡፡ እንደ ፕሮፌሰር አስራት ያለ ልባም አማራ ግን እንኳን በፊት የተሰራውን ግፍ መርሳት ወደ ፊት የሚፈጠመውን ተንኮልም ጭራቆች ተማቀዳቸው በፊት አስቀድሞ ያውቃል፡፡
፩. የዘር ማጥፋት ወንጀል፡- ከወልቃይትና ራያ የጀመረው የአማራ ዘር ማጥፋት ዛሬ በመላው አገሪቱ በከፋ ሁኔታ በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡ የዘር ማጥፋት ዘመቻው በባሩድ ብቻ ሳይሆን ወላዶችን በማምከን፣ በጅምላ እያፈሱ በእስር በማንገላታት፣ በማሰደድ፣ ለበሽታ በማጋለጥና ለድህነት በመዳረግ ተካሂዷል፤ በመፈጠም ላይም ይገኛል፡፡
፪. ታሪክን የማጥፋት ዘመቻ፡- የአማራን ታሪክ የማጥፋት ዘመቻው ፊደሉና ቋንቋው ተአብዛኛው የአገሪቱ ክፍል መጠቀሚያ እንዳይሆን ተመከልከል ጀምሮ ዛሬ ቅድመ አያቶቹ በቆረቆሯቸው ከተሞች ያሉ ቅርሶች በተለያዩ ስበቦች እየተፋቁ እንዲጠፉ እየተደረገ ነው፡፡ ቤተክርስትያኖቹና ሌሎችም ታሪካዊ ቅርሶቹ በቦንብና በመድፍ እየጋዩ ነው፡፡ ይህ ሁሉ ሲፈጠም ሞኝ ሰው የሚታየው የቤት መፍረስና መፈናቀል ብቻ ነው፡፡ እየተሰራ ያለው ግን የአማራን ታሪክ ማጥፋት ነው፡፡ ታሪክ የሌለው ወይም ታሪኩ የጠፋ ሕዝብ ደሞ ስሩ የተቦደሰ ዛፍ ማለት ነው፡፡
፫. መቀበርያ ማሳጣትና የተቀበረውንም በግንዲደር እየዛቁ የመወርወር አረመኔአዊ ድርጊት፡- በልጅነታችን “የሞተን ሰው የሚያከብሩና የማይነኩ የዱር አውሬዎች አሉ” ሲባል እንሰማ ነበር፡፡ ዛሬ የሞተን ሰው መቀበርያ የሚከለክሉና ሲሻቸውም ስልጣናቸውን ተጠቅመው የራሳቸውን ሰዎች በሚፈልጉት ቦታ በሰፋፊ መቃብሮች ውስጥ እየቀበሩ ሌላውን በተለይም በመሰረታት አገሩ መጤ የሚባለውን አማራ ለመቀበርያ ከአስር እስከ አስራ እምስት ሚሊዮን ብር እሚጠይቁ፤ የተቀበረውንም በልማት ስም በግኒደር እየዛቁ የሚወረውሩ ከዱር አውሬም ያነሱ ፍጡሮች እያየን ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ብዙ ሰው ዘመዱ ሲሞት ከአገሩ ይልቅ ዉጭ አገር መቅበርን እየመረጠ ነው፡፡
አማራ የዘር ማጥፋት ወንጀልን፣ ታሪክን የማጥፋት ዘመቻን፣ መቀበርያ የማጣትንና እሬሳውን በግኒደር የመዛቅ ግፍ መታገል ያለበት በነቂስ ተደራጅቶና አንድ ሆኖ ነው፡፡ በእነዚህ ግፎች ዙርያ አንድ የማይሆን አማራ ከሰውነት የወጣ ከአውሬም ያነሰ ከንቱ ፍጡር ነው፡፡ አውሬ እንኳ ዘሩን የሚያጠፋ ኃይል ሲመጣ ሰበቡን እየደረደረ ሆዱን ሞልቶ ይተኛል ወይም እርስ በእርሱ ይናከሳል ማለት ዘበት ነው፡፡ አይኑ እያዬ ዘሩን አስጠፍቶ፣ ታሪኩን አስፍቆ፣ የመቃብር ቦታ የሚነፈገውና ሬሳው ተፈንቅሎ የሚወረወር አማራ ከእንሰሳም በታች መቆጠሩን ልብ ይበለው፡፡ አማራ በነቂስ ወጥቶ አንድ ሆኖ መታገል ያለበት ለመኖር ብቻ ሳይሆን ታሪኩ እየተገሸለጠ እንዳይጣል፣ መቀበሪያ እንዳያጣና የተቀበረውም በግኒደር እየታፈሰ መወርወሩ እንዲቆም ነው! አመሰግናለሁ፡፡
ነሐሴ ሁለት ሺ አስራ ስድስት ዓ.ም.