ተዋናይት ሜላት ዳዊት ከእስር እንድትፍታ ፍ/ቤት ትዕዛዝ ቢሰጥም ፖሊስ ይግባኝ ጠየቀ ! ( ይድነቃቸው ከበደ ) May 31, 2023 ሰብአዊ መብት Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email የፊልም ዳይሬክተር እና ተዋናይት ሜላት ዳዊት ፤ በዛሬው ዕለት ግንቦት 22 ቀን 2015 ዓ.ም. አስሯት የሚገኘው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ፣ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት እንድትቀርብ አድርጓል ። ፖሊስ ለባለፉት 7 ቀናት ፍርድ ቤት በሰጠው የምርመራ ቀናት ፣ ከዚህ ቀደም ይቀሩኛል የሚለውን የምርመራ ሂደት አጠናቆ እንዲቀርብ ጊዜ የተሰጠው ቢሆንም ፣ ፍርድ ቤቱ ተጨማሪ 14 የምርምር ቀናት እንዲሰጠው ጠይቋል ። ሆኖም ግን ፤ ፍርድ ቤቱ ከዚህ ቀደም ለፖሊስ የተሰጠው የምርመራ ቀናት በቂ በመሆኑ ፣ እንዲሁም ፖሊስ ከዚህ በፊት በተሰጠው ጊዜ የተለየ የምርመራ ሥራ አልተሰራም በማለት ፤ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ፣የፊልም ዳይሬክተር እና ተዋናይት ሜላት ዳዊት በ5 ሺህ ብር የገንዘብ ዋስትና ጉዳዩን ከእስር ተፈታ እንድትከታተል ፍ/ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል ። ጠዋት በዋለው ችሎት ፤ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፤ ተዋናይት ሜላት ዳዊት በ5 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንድትለቀቅ የሰጠውን ትዕዛዝ በመቃወም ፤ ፖሊስ ለከፍተኛ ደረጃ ፍርድ ቤት ከሰዓት በዋለው ችሎት ይግባኝ ጠይቋል ። ይግባኙን የተመለከው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ፤ በታችኛው ፍ/ቤት የተሰጠውን ትዕዛዝ መርምሬ ” ውሳኔ የምሰጠው ፤ ነገ ግንቦት 23 ቀን 2015 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ 8 ፡00 ሰዓት ነው ” ብሏል ። All reactions: 259259 Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email Leave a Reply Cancel replyYour email address will not be published. Δ Previous Story እስክንድር ነጋ የሻለቃው ማስታወሻና የአገዛዙ ጥቃት |Hiber Radio Special Next Story በሐዋሳ ተፈፅሟል ስለተባለው ዘመናዊዉ የጠለፋ ድርጊት መረጃ