ኢትዮጵያ እና ህዝቧ በታሪካቸዉ ጠላቶቿ ሳይቀሩ የሚመሰክሩት ብዙ ዕዉነታዎች ይጠቀሳሉ ፡፡
ለዚህም አገረ መንግስት ለመመስረት እና አገር ለማፅናት ፣ ዳር ድንበር በማስጠበቅ፣ ቅዥ ግዛትን አጥብቆ በመታገል ፣ ለነፃነት እና ለብሄራዊ እና ክፍለ ዓለማዊ ነፃነት ተጋድሎ ትልቁን ሚና በመጫዎች የባርነትን እና ተገዥነት ቀንበር በመስበር የአፍሪካ የነፃነት ተምሳሌት ናቸዉ ፡፡
እኮ እንዲህ ዓይነቱን ኢትዮጵያዉያን ጊዜ አልፎ በተተካ የኢትዮጵያዉን እና አገር ባለዉለታዎች በበላይነት እና የቅዥ ግዛት ናፋቂዎች እና ተላላኪዎች ሲካዱ እና ሲዋረዱ የዘመናት ክፉ ልማድ ሆኗል ፡፡
ካሳለፍናቸዉ የመከራ እና የጨለማ ዘመናት ሳንማር እና ሳንመክር በአፈ ጮሌዎች የሚጫን የእንወቅልህ እና እንናገርልህ አለንልህ ማታለል እና መደለል መልኩን መቀያየር አገር እና ህዝብ በአገሩ እናበራሱ ተስፋ እንዲቆርጥ ግድ ሆኖበታል ፡፡
ዛሬ ላይ የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም የዓማራ ህዝብ ቁስሉ ሳይሽር፣ ዕንባዉ ሳይተበስ ፣ ደሙ ሳይደርቅ ሳይደርቅ ፣ ለአገራቸዉ እና ለህዝባቸዉ የከፈሉት ዋጋ ከምንም ሳይቆጠር ህይወታቸዉን የሰዉት ከህዝብ ትዉስታ እያሉ ዳግም አገር ለመፍታት የአንድን ህዝብ ራሱን እና አገሩን ለመከላከል ያለዉን ተፈጥሯዊ መብት የነፍስ ወከፍ መሳሪያ መግፈፍ ድርጊት ከስራ መፍታት የሚመነጭ አገር የማስፈታት አካል ሆኗል ፡፡
ይህም በኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዉን አንድነት እና ሉዓላዊነት ላይ ዕንቅልፍ የሚነሳቸዉ ታሪካዊ የዉጭ እና የዉስጥ ጠላቶች ጥርስ ዉስጥ የመግበታቸዉ የዘመናት ጥላቻ እና ቂም በቀል ነዉ ፡፡
ምዕራባዉያን በምስራቁ ዓለም እና በኢትዮጵያ ላይ በጥርስ ከማኘክ የዉስጥ ጉዳይን በማወክ ሳይደክሙ ማኘክ ምኞታቸዉን ያደረጉ ጠላቶች ኢትዮጵያዊነት እና ኢትዮጵያን ለመለያየት እና ለማፋታት ከዉስጥ እና ከዉጭ ፤ ከቅርብ እና ሩቅ ሆነዉ የሚያደርጉት ሴራ ኢትዮጵያን ከድጥ ወደ ማጥ እንዳይሆን ኢትዮጵያን ከማስፈታት እና ከመፍታት ጠላትን እና ፀረ -ኢትዮጵያ የሆኑት የሕዝብ እና የአገር አንድነት ጠንቆችን ተስፋ ማስፈታት እና አደብ ማስገዛት ከፍተኛ ስራ የሚደረግበት ወርቃማ አጋጣሚ እና ጊዜ ነዉ ፡፡
እናም ጠላት የጥፋት እና የክፋት ስራዉን ያቆመ ወይም ስራ የፈታ በመሰለዉ ቁጥር አገርን እና ህዝብ ለማፋታት እና ተፈጥሯዊ ማንነቱን እና ኢትዮጵያዊነቱን ከኢትዮጵያ ለማፋታት ፣ቀኙን ከግራዉ ለመለያየት መጣር ፀረ ኢትዮጵያዊነት አባዜ መቆም ለመላ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊያን የሚበጂ ነዉ ፡፡
ዛሬ በዉጭ እና በዉሥት አፍራሽ ኃይሎች ሴራ በመድማት እና በመቁሰል ላይ የሚገኙትን ህዝብ እና አገር አሜን ባይ እና ተንበርካኪ በማድረግ ጠላትን ማድለብ እና መንከባከብ ለኢትዮጵያ ቀርቶ ለአፍሪካ ጠንቅ መሆኑን ሁሉም ኢትዮጵያዉያን መረዳት አለብን ፡፡
የኢትዮጵያዉያን እና የኢትዮጵያ የአንድነት እና የህልዉና መስተጋብር ዕንቅልፍ የሚነሳቸዉ ጠላቶች የጥፋት ስራ መፍታት ጊዜ እየተሰጠዉ ለአገር መፈታት ምክንያትነት ቀርቶ የጠላትን ሴራ መስበር እና እና የኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዉያን ክብር እና ዳር ድንበር ማስከበር ትኩረት እና ተግባር መጠናከር ይገባል ፡፡
አንድነት ኃይል ነዉ !
Allen Amber !