March 2, 2023
4 mins read

የአገዛዙ መልክ ሜክ አፑ እየለቀቀ አሁን ትክክለኛ ገጽታው እየታየ ነው- ዜጠኛ መሳይ መኮንን

5665556 1 1ዛሬ የሆነው ወዴት እንደሚወስደን ለመግለጽ ነብይ መሆን አይጠይቅም። በሚኒሊክ አደባባይ የአድዋ ድል እንዳይከበር መደረጉ ነገ ምን ዓይነት እርምጃ ሊወስዱ ምልክት እያሳዩን እንደሆነ በግሌ ገብቶኛል። ጊዮርጊስ አጠገብ የቆመውን የሚኒሊክ ሀውልት ማፍረስ በቀጣይ የምንመለከተው ነገር እንደሚሆን አልጠራጠርም። የሀጫሉ ሞት ጊዜ ታስቦ እንደነበረ አስታውሳለሁ። አዲስ አበባን ስሟን ቀይሮ ወደ ኦሮሚያ ክልል የመጠቅለል ውሳኔም ከጠረጴዛ ላይ የተቀመጠ ፋይል ሆኗል። ከወደጨፌ ኦሮሚያ ሀሳቡ ተነስቶ አራት ኪሎ ቆይ ትንሽ ታገሱ ብሎ እንዳዘገየው ሽው የምትል መረጃ ከጆሮዬ ከጠለቀች ሰነባብታለች።
የኦሮሚያ ብልጽግና የኦነግን አጀንዳ አንድ በአንድ በማስፈጸም ላይ ይገኛል። ከእንግዲህ ሸኔ ሰው ማረድ አያስፈልገውም። ኦነግ ነፍጥ ተሸክሞ ጫካ ለጫካ መርመጥመጡ ትርጉም የለውም። በኢትዮጵያ ስም የሚምምል በገቢር ኢትዮጵያን የሚገዘግዝ መንግስት አጀንዳቸውን በቅደም ተከተል እያስፈጸመላቸው ነው።
ጎበዝ፥ ኦነግ ሸኔ ብላችሁ በማጉሊያ መነጽር ሩቅ አትመለከቱ። ያርዳል፡ ይጨፈጭፋል ብላችሁ ስትርግሙት ስትከሱት ከኖራችሁት ቡድን ላይ የጠነቆላችሁትን ጣት አንሱት። ኦነግ ሸኔ የጦስ ዶሮ ነው።
ኢትዮጵያ ብርቱ አደጋ ላይ ናት። የተፈራው ነገር ድሆ ድሆ መጥቷል። የኢትዮጵያዊነት ካባ ለብሶ አራት ኪሎ የገባው አገዛዝ ቀስ በቀስ፡ እያስታመመ የመገዝገዝ ስራውን አከናውኖ አሁን በአደባባይ ተግባራዊ ወደማድረግ ምዕራፍ በይፋ ገብቷል። ለጨዋታ ማሳመሪያና፡ በድንዛዜ ውስጥ ላሉት፡ ዓይን ልቦናቸው በባዶ ትርክት ለተሸበቡት ወገኖች አሁንም ‘ኢትዮጵያ አትፈርስም’ ዲስኩር እየተለቀቀላቸው ጥቂት ጊዜያት መቆየቱ አይቀርም። ኢትዮጵያን የማወላለቁ ስራ ከጓዳ ወደ ደጅ መውጣቱን የሚያሳዩ ተግባራት በየዕለቱ እየበረከቱ መጥተዋል። መደባበቅ አያስፈልግም። በሀገር ጉዳይ መሽክርመሙ ዋጋ እያስከፈለ ነው። ይህ ሟርተኝነት አይደለም። ካስባለም እኔ ሟርተኛ ሆኜ ልቅር፡ ይሄን ሳልተነፍስ ከምቀር።
ኢትዮጵያን ለማዳን ጊዜው አልረፈደም። በጣም ከባድ ቢሆንም የማይቻል ግን አይደለም። መቃብር የማሱላትን ወደጥልቁ መቃብር የከተተች ተአምረኛ ሀገር ናት። አለቀላት ሲባል ብድግ ብላ የምትገዝፍ ድንቅ ሀገር ባለቤቶች ነን። አጎንብሰን ሊሆን ይችላል እንጂ አልተሰበርንም። መጀመሪያ በድንዛዜ ያሉ የቀሩ ወገኖች እንዲነቁ ማድረግ ቢቻል ጥሩ ነው። ካልሆነም ለውጥ ለማምጣት ጥቂት የቆረጡ በቂ ናቸው። እናስብ። ምን እየተደረገብን እንዳለ በጥልቅ እንመርምር። እየሆነብን ያለውን ከፍርሃት ወጥተን እንፈትሽ። ኢትዮጵያ ስሟ ደስ ስለሚለን፡ ስለምንወዳት አይደለም። ህልውናችን ስለሆነች እንጂ!
331534101 906982410627755 5729230093331574485 n 1 1

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
Go toTop