September 13, 2022
10 mins read

በዳይ እንደ ተበዳይ   !

TPLFባለፉት ሶስት  ዓመታት ሶስት ጊዜ ተጣለቶ ሶስት ጊዜ በተኩስ አቁም ፣ በንግግር ……ላለመስማማት የተስማሙት ሁለቱ አካላት አንዴ ሠላም /በእጂ ፤ አንዴ ጦርነት/ በፈንጂ የሚሉት ትህነግ እና ኢህዴግ ናቸዉ ፡፡

ሁለቱም መመኪያቸዉ እና ጉልበታቸዉ ህገ- ኢህአዴግ በመሆኑ  የስያሜ ካልሆነ የይዘትም ሆነ የተግባር አንድነት ያላቸዉ ናቸዉ ፡፡ 2ኛዉ ኢህዴህ የስርዓት እና የህገ መንገስት ለዉጥ ቢያደርግ ኖሮ ጥል አለ ማለት በተቻለ ነበር ፡፡

ከዚህም የተነሳ ጥሉ ወይም ልየነቱ ያለዉ በኢትዮጵያ እና እኔ ካልኖርኩ ስርዶ አይብቀል ባይ ጋር ነዉ ፡፡

ይኸዉም ኢህአዴግ  ሲኖር ኢትዮጵያ ትኖራለች  ኢህአዴግ ሲከስም ኢትዮጵያ ትከስማለች የሚል በከንቱ አምልኮ ራሱን የሚቆጥር የድመት  ዲሞክራሲ በልቸ ልሙት የሚል ካለሱ ፈቃድ ጨለማ ዔነጋም ፤ ፀሀይ አትወጣም ባይ መሆኑ ነዉ ፡፡

በዚህ ባህሪዉ ጥቂት መገለጫዎች እንደሚከተለዉ ይታወቃሉ ፡-

Ethiopiabbbrr444

ኢትዮጵያ በቅድመ እና ድህረ ኢህዴግ ከቀደመ ስም ፤ ክብር ፣ ዳርድንበር  እና ገናና ታሪክ እንድትርቅ እና ህዝቧም ያሉትን ተቀባይ ሆኖ ሲረግሙት ዓሜን አንዲሆን ሆኖ ተፈርዶበታል፡፡

በቅድመ ትህነግ /ኢህዴግ ኢትዮጵያ እና ህዝቧ ብዙ ሠባዊ እና ቁሳዊ ጉዳት ደርሶባቸዋል ፡፡ በቅድመ ትህነግ /ኢህዴግ የተጠነሰሰዉ ኢትዮጵያን በዉስጥ እና በዉጭ የማዳከም ጥንስስ በድህረ ጊዜ (ከ1983)በመቀጠል ፡-

  • የተፈጥሮ የሁለት ባህር በር ባለቤት የነበረች ኢትዮጵያ በራሷ ልጆች የጥላቻ በቀል ፖለቲካ በግፍ ተነጥቃለች፣
  • ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት በጥልቅ እና ከንቱ መሰረተ ቢስ የፖለቲካ ስልጣኝ ጥመኝነት በጥላቻ ከዉስጥ እና ከዉጭ እንዲፈረጁ ተደርጓል፣
  • በአንድ አገር ዉስጥ ብዙኃን ህዝብ ኢትዮጵያ እንደ አገር ተመስርታ እና ፀንታ እንድትኖር በማድረግ የነፃ ኅዝብ አገር በማቆየት ከፍተኛ ሚና ያለዉን የዓማራበዓለም ላይ ነፃ እና የራሷ የሆነ ብሄራዊ መገለጫ ያላት አገር ሆና ለመኖሯ ፀንታ እንድተኖር ያደረገ ህዝብ ከድህረ ትህነግ/ኢህዴግ በፊት እና በኋላ በጠላትነት መፈረጂ ፣
  • ይህን በጠላትነት የፈረጀ  ህገ -ኢህዴግ ትርክት መሰረት ያደረገ ማንነት ላይ ያተኮረ ጥቃት፣ ስደት፣ ዉርደት ፣ ድህነት እና ሞት በማወጂ መፈፀም እና ማስፈፀም፣
  • በኅገ -ኢህዴግ እና በክልል አደረጃጀት ብዙኃኑን ያገለለ የግዛት አስተዳደር በማዋቀር በህዝቦች መካከል መቃቃር መፍጠር እና ይህም በአንድ አገር ጠላት እና ወዳጂ ህዝብ መፍጠር፣
  • የዚህ ብዙኃኑን የኢትዮጵያ ህዝብ ያላካተተ የህገ- ኢህዴግ እና የቋንቋ የግዛት አስተዳደር (ክልል) አወቃቀር አስካሁን ላለዉ የህዝቦች መከራ እና ስቃይ መደራረብ እና መራዘም ምክነያት መሆን ፣
  • የዚህ ሁሉ አድራጊ እና ፈጣሪ  ትህነግ -ኢህአዴግ በስልጣን በነበረበት የሶስት አሰርተ ዓመታት በአገር እና ህዝብ ላይ ያደረሰዉ መጠነ ሠፊ ግፍ፣ በደል እና ታሪክ የማይረሳዉ ብሄራዊ እና ታሪካዊ ክህደት ሳያንስ ላለፉት ሶስት ዓመታት በተደጋጋሚ በኢትዮጵያ አንድነት እና በህዝቦች አብሮ የመኖር ተስፋ ላይ ያደረሰዉ ዕብሪት እና ዕልቂት ፣
  • በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ጦርነት  ኤርትራን እና ሁለት ወደቦች (አሰብ እና ምፅዋ) አሳልፎ በመስጠት ኤርትራ ፤ ወደብ የሚል መንገዱን ጨርቅ ያርግለት ሲል የነበር ለዉስጥ ትኩሳት ማብረጃ የበሬ ግንባር ለማትሆን ቦታ ባድመ ጦርነት እንዳይካሄድ ማድረግ ሲቻል በታሪክ በአጭር ጊዜ ከፍተኛ የህይወት መስዋዕት መከፈሉ ፣
  • ይህ ከሆነ በኋላ በዓለም አቀፍ ህግ በአልጀርስ ዉሳኔ ባለፍርድ ኤርትራ መሆኗ እየታወቀ ያኔም ሆነ ዛሬ ስለባድመ ጦር መስበቅ ፣
  • ከትህነግ -ኢህዴግ የበረኃ ትግል 1968 ዓ.ም. ጀምሮ በጠላትነት ፈርጆ የፖለቲካ ትኩሳት ማቀጣጣያ ያደረገዉን ነባሩን የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም ዓማራ በሚል የጥላቻ ዘመቻ የዘራዉን የጥፋት እሾህ ላለፉት ሶስት ዓመት በቀቢፀ ተስፋ በወረራ እና ምዝበራ ኗሪዉን ስደተኛ እና ምፅዋተኛ በማድረግ ግዛት የማስፋፈት  ጊዜ ያለፈበት ከንቱ ህልም በዓማራ እና አፋር ህዝብ ላይ ከፍተኛ ሠባዊ እና ቁሳዊ ጥፋት ማድረሱ የሚዘነጋ አይደለም ፡፡

ባጭሩ የአንድን አገር ሉዓላዊ ህዝብ እና ዳር ድንበር አሳልፎ በመስጠት የኢትዮጵያን ጥቅም እና ስም አሳልፎ በመስጠት፣የኢትዮጵያን ታሪካዊ ዕዉነታ በማዛባት፣ የተሰሳተ የፖለቲካ ትርክት በማስፋፋት በህዝቦች መካከል ጥላቻ ማብዛት፣ በራሱ አገር እና ህዝብ ላይ ስር የሰደደ ጥላቻ ፣ ጥቃት ፣ ዉርደት ፣ሞት…በማድረስ የሚደሰት ፣ በማንነት እና በርዕዮተዓለም ልዩነት የተነሳ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ እና ማሕበራዊ አድሎ እና መድሎ ማድረስ፣ ዜጎች ኢትዮጵያዊ ተፈጥሯዊ ማንነታቸዉ የአንድ ማህበረሰብ በመሆናቸዉ ብቻ በማንነታቸዉ፣ በእምነታቸዉ እና ባህላቸዉ ላይ ጫና ማድረግ ፣ናሳደድ ፣ መግደል እና ማስገደል የተከናወነዉ በትህነግ -አህአዴግ አግላይ ህግ እና ስርዓተ ነዉ ፡፡

ይህ ሁሉ በኢትዮጵያ እና ህዝቦች ላይ ተሰፍሮ እና ተቆጥሮ የማያልቅ ክህደት ፣ ዉርደት እና ጥቃት በፈፀመ ፣ እየፈፀመ ባለ እና ከሰማያ በታች የሚደረገዉን ሁሉ ክፉ ስራ በኢትዮጵያ እና ህዝቧ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ እና ታሪክ ለማሳከር ዓማራን በማጥፋት ኢትዮጵያዊነትን ከኢትዮጵያ ጋር የመንቀል  ሀ.ሁ.. ዓማራን ጠላት አድርጎ በዕብሪት ለ50 ዓመት በላይ ለሚሰራ ኃይል ለዚህ ሁሉ ጥፋት ዋጋ ሳይጠየቅ ድርድር እና ዕርቅ ማለት በኅዝብ እና አገር ቁስል እንደመጫወት ይሆናል ፡፡

ተበዳይ እና በዳይ በሌሉበት ዕርቅ በማለት የሚደረግ ጥረት የአንድ ወገን ጥቅም ከማስታመም ዉጭ ለአገር እና ክብር ፣ጥቅም እና ዳር ድንበር መከበር ብሎም ሉዓላዊ ጥቅም ለማስከበር የሚያስችል ስለማይሆን ሳይጀመር ያለቀ መግባባት ነዉ  ፡፡

ምንጊዜም የሕዝብ ተሳትፎ እና ዕዉቅና የሌለበት የዕርቅ እና ድርድር ሂደት ያልተጣላ ማስታረቅ እንዳይሆን ሁሉም ይመለከተኛል ባይ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ልብ ሊለዉ ይገባል  ፡፡

በዳይ ሳይክስ፤ ተበዳይ ሳይካስ  በዳይን እንደተበዳይ ማስታመም ድርድር እና ዕርቅ ማራራቅ ስለሚሆን ሁሉም በየፈርጁ መሆን አለበት  ፡፡

አንድነት ኃይል ነዉ

NEILOSS –Amber.

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
Go toTop