September 13, 2022
10 mins read

ነገርን በስም አለመጥራት ከፍርኃት እና ስስት  የሚመነጭ ነዉ  

ከሶስት አስርት ዓመታት  በፊት የተጀመረዉ አገሪቷን እና ህዝቧን የማዳካም  ሴራ በተለያየ ጊዜ በተግባር እንዲሆን ተደርጓል፡፡

tigrayታላቋን ትግራይ ለማቆቋም የታሰበዉ ሴራ ዕዉን ለማድረግ  ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም .ወረራ እና ጥቃት  ሲጀምር በዋነኛነት ኢትዮጵያን የሆድ ዕቃዋን ለመዘክዘክ የዓማራን ህዝብ እና መኗሪያዉን በወራራ እና ምዝበራ ትህነግ አከናዉኗል፡፡  ይህም ትህነግ ለሶስተኛ ጊዜ የወረራ እና ምዝበራ ዕኩይ እንቅስቃሴ ሲያደርግ መነሻዉም ሆነ መዳረሻዉ የዓማራ ህዝብ በብዙ ፤ የዓፋር ህዝብ በከፊል ስለመሆኑ በምድር ላይ ያለ ሀቅ ነዉ ፡፡

ይህ ሁሉ ሲሆን ዓላማዉ አገርን እና ህዝብን በማወክ የኢትዮጵያን አንድነት እና የዜጎች ደህንነት ስጋት ሆኖ እያለ ከአንድ ሶስት ጊዜ በአገር ክህደት እና በብሄራዊ ሽብር በህዝብ እና በአገር ከፍተኛ በደል እያደረሱ ከኃዴወች እና የአገር ታሪካዊ ጠላቶች መሆና ሲታወቅ  የኢትዮጵያ ጠላት ሆኖ ከኃዲ እና ባንዳ  ብሎ ከመጥራት ህግ ማስከበር ፣ሠላም ማስፈን…..ማለት የመከራ ጊዜ መግዛት ነዉ ፡፡

ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዉያን በተለይም የዓማራ እና አፋር ህዝብ የጥላቻ እና የትቃት መረጋገጫ ሆነዉ እያሉ የነሱ የተደጋገመ ጥቃት ፣ስደት ፣ሞት እና ዉርደት  …..እየተዳፈነ በአገር እና በህዘብ ላይ በማንአለብኝነት ይህን ሁሉ በደል ያደረሱት በስም እና በምግባር እያለባበሱ  የሚኖር  ሠላም በአንድ እጂ ማጨብጨብ እና ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ ነዉ ፡፡

ከዚህም በላይ በተደጋጋሚ በአገራችን ከትናንት አስከ ዛሬ  በዉጭ እና ዉስጥ ጠላቶች በተደረጉ የኃይል ጥቃት ሁሉ የሚሳተፈዉን እና እየተሳተፈዉን ዕዉቅና አለመስጠት እና በስም አለመጥራት በራሱ ሌላዉ በድል ጉዞ የሚደረገዉን ጉዞ ብስል እና ጥሬ ያደርገዋል ፡፡ ይህም በልዩነቶች ላይ አለመተማመን እና የሰራ የሚከበርበት ፤ያጠፋ የሚጠየቅበት ስርዓት በመገንባት የፍትህ እና ነጻነት መንፈስ የሰፈነበት አገር አገር እና ትዉልድ መግንባት በሚደረገዉ ጥረት ዉኃ መቸለስ ይሆናል፡፡

በቅርብ ጊዜ በገንጣይ እና አስገንጣይ የዉስጥ እና የዉጭ ቅጥረኛ ኃይሎች ላይ በተደረገዉ ተጋድሎ ላለፉት ሶስት ዓመታት በግንባር ቀደምትነት የጥቃት እና መስፋፋት ዒላማ የሆነዉ የዓማራ ህዝብ  ላለፉት ሶስት አስርተ ዓመታት ያስተናገደዉን ግፍ እንዲያስተናግድ ሲወረር የአካባቢዉ ህዝብ ፤ የመነግስት ልዩ ኃይል ፖሊስ ፣ህዝባዊ ታጣቂ፣ የዓማራ ህዝብ ልጂ “ፋኖ ” በነፍስ ወከፍ ጠበንጃ እና በባዶ እጂ  አካባቢያቸዉን ፣ የተከበበዉን ጦር ፣ ኢትዮጵያን እና መንግስትን የዕሳት ዕራት ሆነዉ ታድገዋል ፡፡ ይህም አሁን ላይ አገሪቷ እና ህዝቧ ለምንገኝበት ምክነያት ሆነዉ በህይወት እና የአካል ዋጋ የከፈሉትን አለመዘከር እና በስም እና ተግባር ለይቶ አለመጥራትም ሆነ ዕዉቅና መንፈግ ለአገር አንድነት እና የህዝቦች ሉዓላዊነት የሚደረገገዉን ሁለንተናዊ ጉዞ ማናቀፍ ይሆናል ፡፡

ይህ ዓይነቱ ግርድፍ  አካሄድ የዘመናችን ሆነ መጪዉ ትዉልድ የነበረዉን እና ያለዉን ከወደፊት  ታሪክ ጋር በግልፅ እና በብሩህ  አያይዞ ለመቀጠል እንዲቸገር ያደርገዋል፡፡

የአሁን ተቀባይነት ለማግኘት ሲባል እና የነበረዉን ለማጣጣል የሚደረግ የታሪክ ግርታ የሚያስከትለዉን ዕንከን ከትናንት መማር ያስፈልጋል ፡፡

የኢትዮጵያ የነፃነት እና የሉዓላዊ ተጋድሎ ከዉጭ እና ከዉስጥ ጥቃት ስንዘራ አኳያ የቅርብ ዘመን ሲነሳ የአደዋ፣ የዳግም ኢጣሊያ ወረራ(1928 -1933 ዓ.ም) እና የሶማሊያ እና የዉስጥ ከኃዲዎች  ኢትዮጵያን የመዉረር እና የመመዝበር ብሎም ግዛት ማስፋፋት የሚነሱ ናቸዉ ፡፡

ሆኖም የቀደሙትን ኢትዮጵያዉያን መልካም ተጋድሎ ባለማንሳት ባልተሰራ  ስራ መከበር እና መወደስ የሚፈልጉ ኃይሎች  ቢገመዝዛቸዉም የአደዋን  የድል ታሪክ በመንቀስ  ሌላዉን እና ትልቅ ብሄራዊ መስዋዕት የሆነበትን ኢትዮጵያን ግዛት ለማስከበር የተደረገ የሁለተኛዉን እና የካራ ማራ የድል ታሪክ ማሳነስ ለኢትዮጵያ አንድነት እና ለዜጎች ሉዓላዊነት የተከፈለዉን ዋጋ መርሳት ወይም ክህደት እንዳይሆን  ሶስቱም የድል ምዕራፎች ለኢትዮጵያ እና ህዝቧ ከፍታ የድል ማማዎች ሆነዉ በታሪክ እና በትዉልድ ሊዘከሩ ይገባል ፡፡

ወደ አሁንም ስንመጣ በዉጭ እና በዉስጥ ጣምራ ሴራ በሶስት ዓመት ዉስጥ ሶስት ጊዜ በኢትዮጵያ አንድነት እና በህዝቦች ደህንት በተለይም በዓማራ እና በአፋር ህዝቦች የደረሰዉ እና የሆነዉ ክህደት እና ለዚህም በከፍተኛ ብሄራዊ  ፍቅር እና ወኔ ህይወታቸዉን ቤዛ ላደረጉ የአካባቢ ህዝቦች ፤የክልል ልዩ ኃይል ፖሊስ አባላት ፣ ለሚሊሽያ እና ፋኖ ኃይል(የዓማራ ህዝባዊ ፈጥኖ ደራሽ ኃይል) በስም እና በተግባር ልክ ዕዉቅና እና ተገቢዉ ክብር እና ጥቅም መስጠት ለአገር እና ህዝብ ከሚኖረዉ ፋይዳ አኳያ ትንሹ ነዉ እና ቢታሰብበት ለሁሉም የዉዴታ ግዴታ እና የአገር አለኝታ ማሳያ ነዉ ፡፡ ጣምራ ጦር  የሚለዉም እንደተጠበቀ ሆኖ የጣምራ ጦር አባላት የሚገኙበት ጀግናዉ እና የአገር አለኝታዉ መከላከያ፣ የዓማራ እና አፋር ልዩ ኃይል ፣ ሚሊሽያ፣ ፋኖ…..ማለት ህዝባዊነት ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያዊ ማንነት እና ዕዉነተኛ ታሪክ ስራ ግንባታ ይሆናል፡፡

አገርን እና ህዝብን አይተኬ አንድያ ህይወታቸዉን እና አካላቸዉን ለሚሰጡት የአገር ባለዉለታወች  ከተቀመጥንበት ተነስተን ኖሩ ማለት ፣ በሚሄዱበት ቅድሚያ እና ነፃ መጓጓዣ ፣ ህክምና እንዲሁም ለቤተሰቦቻቸዉ የትምህርት ዕድል……የመሳሰሉትን መስጠት የሚስችል አሰራር ሳይዉል ሳያድር ማድረግ አገር ላለዉ እና አገሩን ለሚወድ ሁሉ ቀላሉ መሆኑን ተረድቶ ያለምንም አድርባይነት የቄሳርን ለቄሳር ….የእ/ርን ለእ/ብሄር..ማለት በዚህ በአዲስ ዓመት ይጀመር ዘንድ ምኞታችን ብቻ ሳይሆን ቁርጠኝነታችን መሆን አለበት ፡፡

በምኞት እና በፍላጎት ጠብ የሚል እንደማይኖር አዉቀን ሁላችንም ከራስ ወዳድነት እና ከንቱ ዉዳሴ ወጥተን በቁርጠኝነት መንፈስ ሁሉን በስም እና ምግባር ልክ በአዲሱ ዘመን እንድንጠራ ይቻለን ዘንድ የዘመናት ባለቤት  መድኃኒት ዓለም ይርዳን ፡፡

ታላቁ መፅኃፍ ጨለማ ከብርኃን፤ ክርስቶስ ከቤርሆም …ምን ስምምነት አላቸዉ ? እንዲል ክፉን ፤ሠነፉን….በስም እና በምግባር መጥራት አለመቻል ከፍርኃት ወይም ስስት ስለሚሆን  ካለፈዉ ተምረን ፤ዛሬን ተመክረን ለነገ  ዕዉነት ያልሆነዉን ዕዉነት እንዳንል ማስተዋሉን ይስጠን ፡፡

 

 

አንድነት ኃይል ነዉ

NEILLOS –Amber.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
Go toTop