ጦር እየመዘዙ ድርድር ለማንም አይበጅም !! (ከተዘራ አሰጉ)

ከላይ በርዕሱ እንደሚያሳየው ወደ ድርድርና ዕርቅ ለመምጣት በሃገረ ኢትዮጵያ ትብዕል መሰረት በሁለት ወይም ከዛ በላይ በተቃርኖ ባሉ ቡድኖች መካከል የሕግ ተገዥነት ስሜትና የሰላም መንፈስ አዝማሚያ ሊኖር የግድ ይላል።

እንዲሁም ተፋላሚዎች ጦራቸውን ወደ ሰገባቸው እንደሚያስገቡ ቃል ሊገቡና የፈፀሙትን ወንጀል በመፀፀትና ያለማወላወል ሲያምኑ ድርድሩ የተዋጣለት ይሆናል።

በኃይል ቦንብ አዝንብብሃለሁ ፣ ጉልበቴን አሳይሃለሁ ብሎ ድርድር የማይታሰብ ነው።

ከዚህ ባሻገር በሻከረ ፣ ቂም በያዘ ልቡና፣ የሰላም መሻት በሌለበት ከንፈርን ነክሶ የድርድርና የዕርቅ መነባንብ በማሰማት ወደ ድርድር መግባት እንቶ ፈንቶ ነው።

ድርድር በሁለትና ከዚያም በላይ በሆኑ ሕዝቦች ወይም ፓርቲዎች መካከል ችግሮችን ወይም ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚደርግ ውይይት ነው ። ድርድር ወይም ውይይት የጋራ የሕዝቦችን ጥቅም ማስጠበቂያ መሳሪያ መሆን አለበት።

ድርድር በሁለት ፖርቲዎች ወይም ከዚያ በላይ ባሉ ፓርቲዎችና ሕዝቦችን አካቶ  የሚከወን ሲሆን ተደራዳሪዎቹ ግልፅ በሆነ መንገድ ፍላጎታቸውን፣አጀንዳቸውን ወይም ከድርድሩ ሊያገኙት የሚሹትን ጉዳይ ዘርዝረው በግልፅ ማስቀመጥና ማስፈር አለባቸው።

ከድርድሩና ከውይይቱ በኋላ የተደረሱት ስምምነቶች  የፓርቲዎችን ከዚያም አልፎ የህዝብን የጋራ ጥቅም ለዘለቄታ የሚያስጠብቅ መሆን እንዳለበት ሳይንሳዊና ማህበራዊ ዳራው ያትታል።

“Negotiation is a dialogue between two or more people or parties to reach a desired outcome regarding one or more issues of conflict. It is an interaction between entities who aspire to agree on matters of mutual interest.[1] The agreement can be beneficial for all or some of the parties involved. The Negotiators should establish their own needs and wants while also seeking to understand the wants and needs of others involved to increase their chances of closing deals, avoiding conflicts, forming relationships with other parties, or maximizing mutual gains.[1]

በዚህ አጠር ያለ መጣጥፍ የሕወሃትና የብልፅግናን ፓርቲ የቁጩ በሉና የጓዳ ድርድርን የማያዛልቅ ማህበር በጠጅ ይጀመራል” እንዲሉ የሚታዮትን ዕፀፆች ነቅሰን በማውጣት እንገመግመዋለን።:: ሰሞኑን የቀድሞው የህወሃት የኦዲድ ሹመኛ የነበሩት የአሁኑ የአፍሪካ መንግስታት የጋራ እድገት ማህበር (IGAD) ሊቀመንበር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየው አይዞህ ባይነት ትላንት የኢትዮጵያ አካል በነበረችው ጂቡቲ “ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል” እንዲሉ ለዚህም በቅታ በዋና ከተማዋ ድብቅ ድርድር በህውሃትና በብልፅግና መካከል እየተከናወነ ወይም ሊከወን መሆኑን ሹክ ተብለናል። የሃገሬ ሕዝብ በሁለት ፓርቲዎች ( ህውሃትና ብልፅግና) የጥቅም ፣ የስልጣን ፣ የበላይነት መሻትና የስልጣኑን ቁንጮ የመቆነጠጥ ጥም እንደ ቅጠል እየረገፈ ነው። የሚገርመው እኮ ተፋላሚዎቹ ሃገር ሲባል አዲስ አበባና መቀሌ ነው የሚመስላቸው ሌላው አካባቢ ግን የሌላ ሃገር ሕዝብ ምድር አድርገውታል፣ ዘይገርም ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ለእኛ የሚበጀዉ “ኢትዮጵያን ለቀቅ ጠላቶቿን ጠበቅ” ነዉ፡፡

ይህን ተተርሶ ጦርነት ሲያገረሽ ድረሱልን የሚባሉት የአፋርና የአማራ ሕዝብ ግን ድርድርና ፌሽታ ሲታሰብ አፍንጫችሀን ላሱ  ፣  አይመለከታችሁመባላቸው ያስተዛዝባል  የክሎቹ መሪዎች ድክመትና ተለጣፊነት እንዳለ ሆኑ አካሄዱ ግን የቀልድ ቀልድ ነው። ይህን መሰረት አድርገን የጓዳው፣ ከመጋረጃ ጀርባ ፣የውስጥ ለውስጥና የሽፍጥ ድርድሩን ገመናዎች  እንደሚከተለው በቆረጣ ስልት እንበጣጥሰዋለን:

  • ድርድሩአሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ አስፈላጊ ነው ወይ? ለሚለው ጥያቄ። እደሚታወቀው ድርድር የሚከናወነው በሁለት ተቃርኖ ባላቸው ተፋላሚ ቡድኖች የኃይል መመጣጠን ሲለያይ ፣ የመሸናነፍ አቅም ሲያጡ ፣ ግጭቱ በአንዱ ቡድን የበላይነትና  እሸናፊነት ሊቋጭ ሲቃረብ ድርድር ሊከናወን ይቻላል።

ሁለቱ ተቃርኖ ወይም ግጭት ላይ ያሉ ፓርቲዎች ወይም ቡድኖች ሊያቀራረባቸው የሚችል የሕዝብ የጋራ አጀንዳ ሲኖራቸውም ድርድር መከወኑ ጠቀሞታው ከፍ ያለ ነው።  አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታና ከምንሰማው ጭምጭምታ አንፃር የብልፅግና መንግስት የበላይነት እያገኘ ነው እየተባለ ባለበት ወቅት አሸንፎ ጦርነቱን ከመደምደም ውጭ በተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት ረድፍ ከተፈረጀ ቡድን ጋር ያለ ምክር ቤቱ እውቅና ( ለነገሩ የይስሙላ ምክር ቤት ስለሆነ ይህን ያዙልኝ) ለመደራደር ማሰቡ ጉንጭ አልፊና ወንጀልም ነው ፣ ብልፅግና ተመከር።

ከዚህ ባሻገር ህወሃት ሃገራዊ ጠቀሞታ ያለው የጋራ አጃንዳ ስለሌለው ፣ የመገንጠል አባዜና ሃገረ ኢትዮጵያን የማጥፋት ህሳቤ የያዘ ቡድን በመሆኑ ከዚህ ጥባብና አጉራ ዘለል ፓርቲ ጋር መደራደር መቅለል ነው ፣ ይህ አካሄድ በደፈናው ከቀጠለ አሁን ያለውን የኢትዮጵያ መንግስት ከወያኔ እኩል ሊያስፈርጀው ይችላል የሚል ህሳቤም ይጭራል

ተጨማሪ ያንብቡ:  ፍሬወይኒ መብርሃቱ እንደ ፋና ወጊ!  -  አበጋዝ ወንድሙ

እንደሚታወቀው በደርግ መንግስት ወቅት ሕወሃት እያሸነፈ አምቦና አዲስ አበባ ንበር ላይ ሲደርስ የይስሙላ ድርድር በታላቅዋ ብሪታንያ-ሎንዶን ተካሂዶ ነበር ነገር ግን ድርድሩ ሕውሃት ቤተ-መንግስት እንዲገባ መንገድ ለመክፈትና የደርግ ባለስልጣናትን ለማሽሽት የተከወነ እንደነበረ የቅርብ የ 30 ዓመታት ትዝታ ነው።  ሰሞኑን እየተከናወነ ያለው ስውሩ ድርድር ለነ ደብረፂዮንና መሰሎቹ የብልፅግና የቀድሞ የልብ ወዳጆችና ለክፉ ቀን ይበጁናል ለሚሏቸው የሕወሃት ባለስልጣናት ጭምር የማሸሻ የማሪያም መንገድ ለመስጠት ከሆነ እናንተው ታውቃላችሁ፣

  • ድርድሩ ሕጋዊ መዓቀፍን የጠበቀ ነው ወይ? በዘመናት መካከል በተለያዩሃገራት ማለትም በተባበሩት መንግሥታት፣ ዮኒስኮና መሰል የዓለም መንግስታት ድርጅቶች ግፊት በደቡብ አፍሪካ ፣ በሩዋንዳ፣  በየመንና መሰል ሃገሮች ሕጋዊ ማቀፍ ተላብሰው ከተከናወኑት ድርድሮችና ውይይቶች አንፃር ሲታይ የብልፅግናና የህውሃት አሁናዊ ድርድር አገራዊ ሆነ ዓለም ዓቀፋዊ ሕጋዊ እካሄዱን፣ መስፈርቶችንና ማእቀፍን ጠብቆ እየተከናወነ ነው ለማለት አያስችልም ።

የድርድሩ ህሳቤ ግልፅነት የጎደለው በእውር ድምብር በድብቅ  የሚካሄድ የከከኝ ልከክልህ ድርድርና ከወሬ ያላለፈ የልምምጥ መድረክ ስለሆነ “ልፋ ያለው በሬ ቆዳው ለከበሮ “ እንዲሉ ትርፉ ድካም ነው  

  • ህዝባዊና ሃገራዊ የሆኑ አጀንዳዎች ተቀርፀው ቀርበዋል ወይ? ለሚለው ጥያቄ በገደምዳሜ ከምንሰማቸው በስተቀር ሰለትግራይ ሕዝብ የማያወላውል ታሪካዊኢትዮጵያዊነት ፣ ስለወልቃይትና ራያ የኢትዮጵያ አካልና የአማራ አፅመ እርስት ስለመሆናቸው፣ የሕወሃት ከአሸባሪነት ረድፍ በተወካዮች ምክር ቤት ስለመፈረጅ ጉዳይ እንዴት ምላሽና እልባት ያግኝ በሚለው ጉዳይ ላይ፣ በቀጣይ ህውሃት በመንግስትነት ተካፋይና አካል ሆኖ ስለመቀጠሉና አለመቀጠሉ ወዘተ የጠራ አጀንዳ ይዘው ሳይቀርቡ ለድርድር መደርደር ትርፉ ለመዳለጥ፣እንቅፋትና ወድቆ ለመላላጥና ለመጋጋጥ ነው እንላለን

በአጠቃላይ ድርድሩ የተሟላ አካሄድና ቅርፅ (Road Map) ወዘተ ሳይኖረው ይስሙላ ሕዝብን ባላሳተፈ መልኩ የሚከወን ድርድር ትዝብት ለማትረፍ ካልሆነ በቀር ፣  ሙከራው አልቦ ነው

  • ድርድሩ – አካታች ነው ወይ (Inclusivness):ከላይ ሊዳሰስ እንደተሞከረው የግጭቱ ወይም የጦርነቱ ዋና ተዋናኞች የአማራ ሕዝብ ፣ የወልቃይት የመሬት አስመላሽ ኮሚቴ ፣ የራያ የመሬት አስመላሽ ኮሚቴ ፣ የአፋር ህዝብና ፓርቲዎች በዚህ ድርድር ተሳታፊ እስካልሆኑ ድረስና ከድርድሩ የሚጠብቁት ፍሬ ነገርና ፍላጎታቸውን  ዘርዝረው እስከአላቀረቡ ድረስ  “ውሃ ቅዳ ፣ የውሃ መልስ” ሆኖ ግጭቱ የሚቀጥል፣ ለሌላ የተራዘምና አዙሪቱ ከማያልቅ ጦርነት ውስጥ እደሚገቡ ጥርጥር የለውም።
ተጨማሪ ያንብቡ:  በኢትዮጵያ የእርስ በእርስ ጦርነት የሚያስቀር የአስቸኳይ ጊዜ ማኒፌስቶ - ዮናስ ብሩ (ዶ/ር)

ከዚህ ሌላ ታሪክ አዋቂዎች ፣ የሃገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት ተወካዮች፣ ወጣቶች ፣ ሴቶች ወዘተ አልተሳተፉበትም። ስለዚህ ከአለም አቀፉ የድርድር መስፈርት አንፃር ድርድሩ ያገባቸዋል የሚባሉትን የህብረተሰቡንና የማህበረሰቡን  አካላት ያላካተተ ከመሆኑ ባሻገር ተፅህኖ ፈጣሪ ሃገራትን እነ አሜሪካን ለማስደሰት ሲባል ብቻ ሊከወን የተሞከረ ድርድር በመሆኑ ድርድሩ ከጅምሩ ፉርሽ መሆኑን መረዳት አያዳግትም፣

  • አደራዳሪዎች በሕዝብ ውክልናን ያገኙ ናቸው ወይ?

አንድ ነገር ሊታወቅ የሚገባው ድርድር የሚከወነው በአደራዳሪዎች ነው። ይህ የማዕድ (የኩሽና) ቤት ድርድር ከማንም የማይወግኑ ተፅህኖ ፈጣሪ በሆኑት በተባበሩት መንግስታት ፣ በአፍሪካ አድነት ድርጅትና መሰሎቹ አደራዳሪዎች፣ ታዛቢዎችና ሃገር ውስጥ ተዋቀሩ ሃገር በቀል አደራዳሪ አካላትም በድርድሩ ሊካተቱ የግድ ይላል

ር ግን ዓለም አቀፍ አደራዳሪዎች ገለልተኛ ስለማይሆኑ ህሉን ፣ ወጉንና ቱፊቱን በሚያውቁት በህዝብ ተሳትፎ በተመረጡና በተወከሉ አደራዳሪዎች በበላይነት እየተመራ ድርድሩ ቢከናወን አዋጭ እንደሚሆን ልምዶች ያሳያሉ።

  • ተደራዳሪዎች

ማለትም ብልፅግናና ሕወሃት ወንጀልና የዘር ማጥፋት በሕዝብ ላይ ፈፅመው ከሆነ ለፍርድ ለመቅረብና ለመካስ ዝግጁ መሆናቸው ቃል ሊገቡ የግድ ይላል። በአጠቃላይ ብልፅግናና ሕወሃት ወደ ድርድር ከመግባታቸው በፊት ዓለም አቀፍ የድርድር ፅንሰ ሃሳብን ተግባራዊ ማድረግ የግድ ይላቸዋል።

ብልፅግና ከጦርነት አዙሪት ለመውጣት ወያኔም ትንፋሽ ውጦ ፣ ለሌላ ጦርነት ዝግጅት ጊዜ ለመግዛት ሲል የሚያደርጉት የለበጣ የድርድር ህሳቤ ካለ፣ በሚሰቃየውና በሚፈናቀለው ሕዝብ አምላክ ስም አትሳለቁብን እንላለን።

 

ከተዘራ አሰጉ

ከምድረ-እንግሊዝ።

1 Comment

  1. ተዘራ አሰጉ ሃሳብህ መልካም ነው፡፡ ከጽሁፍህ እንደተረዳሁት ክተደራዳሪዎቹ አንዱ ወርቅነህ ገበየው የተባለው ወንጀለኛ ነው፡፡ ይህ ሰው እንደ እውነቱ ከሆነ ኢትዮጵያ መልሳ ስትቋቋም ለፍርድ ከሚፈለጉ አንዱ ከመሆኑም በላይ ትህነግ እንደ ዶ/ር አብይ ጭኑ ላይ አስቀምጦ ያሳደገው ሰው ነው፡፡ የቅንጅት ድምጽ መሰረቁን ተከትሎ 300 ያህል የኢትዮጵያ ወጣቶች ሲቀጠፉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ሃላፊ ሁኖ ትእዛዙን ያስተላለፈው እሱ እንደነበረ ትዝ ይለናል፡፡ ዶር አብይ የሹመኛ ምርጫው የሚገርም ነው ክጅምሩ እንደነገረን ካሁን በኋላ ሹመት በችሎታ ሳይሆን በብሄር ተዋጽኦ ነው ብሎናል፡፡ እንደዛማ ባይሆን አብርሃም በላይ መከላከያ ሚኒስቴር ሁኖ ዉሃ ቅዳ ዉሃ መልስ ባልሆነብን ነገሩ፡፡ አብረሃም በላይ ከሙሉ ነጋ በኋላ ትግሬን እንዲያስተዳድር ተልኮ ህወአትን አጠናክሮ ከመውጣቱ ባሻገር ለዚህ ውለታው የመከላከያ ሚኒስቴር ሁኖ ቁጭ ብሏል፡፡ ሙሉ ነጋ ሸሺቷል የሚል ወሬ ይሰማል፡፡ ለማንኛውም አማራ በወረንጦ እየተለቀመ ሲባረር እንደዚህ አይነት እንኩቶዎች እያበላሹ የስራ ልምድ እንዲያገኙ በጠቅላያችን ተሹመዋል ከዚህ አያያይዘህ እነ (ታከለ ኡማን፤አርከበ እቁባይን፤አዳነች አቤቤን፤አረጋዊ በርሄን፤ሱሌማን ደደፎን፤ሽመልስ አብዲሳን ._ ፟ ) እያልክ ወደ ታች ስትወርድ ብዙ ጉድ ታያለህ፡፡

    እንደ አባቱ እንደ ኡመር ሰመተር አፍቃሪ ኢትዮጵያ የሆነው ወንድማችን ሙስጠፌ ብዙም የኦነጋውያንን ቀልብ አይስብም፡፡ አንድ ትንሽ ስብስብ መጣሁልህ እያለ በየጊዜው ሲያምሰው አፍንጫውን ይዞ በፈለገው መንገድ ውይይቱን ሲመራው ማየት ገዥዎቻችን ምን አይነት እንኩቶ መሆናቸውን ያሳየናል፡፡ በእርግጥ ለችግሩ ሁሉ ተጠያቂው ጠቅላዩ ነው፡፡ በመሰረቱ ኢትዮጵያ የብዙ ሃገር ድምር እንድትሆን የአብይ ህገ መንግስት ያዛል ድርድርም አለ ከተባለ ተደራዳሪዎቹ የወልቃይትና ጠገዴ ኮሚቴ፤የራያ ኮሚቴና የአማራ ማህበር እንጅ ሌላው ምን አገባው፡፡ ደመቀ መኮንን አለበት የሚል ነጠላ ዜማ ሲለቀቅ ተሰምቷል ደመቀ መኮንን፤አገኘሁ ተሻገር በሂደት ትግሬ የሆኑ ሰዎች በመሆናቸው ለዚህ ድርድር በፍጹም ብቃቱ አይኖራችውም፡፡ እነ ገዱ አንዳርጋቸው፤ዮሃንስ ቧ ያለው፤ጄነራል ተፈራን ፤ፋኖዎችን እንጅ ሌላው ምን አገባው? አሁን እንደማየው አማራ የተባለውን ማህበረስብ በየቦታው እረፍት በመንሳት ደካማና ተምበርካኪ ለማድረግ የአብይ የቆየ ትልሙ በመሆኑ አድር ባይ ሆዳም የአማራ ሹመኞችን በቃችሁ ብሎ አማራው እንደ ዳይኖሰር ከመጥፋቱ በፊት የእስራኤሉን አይነት የነጻነት ትግል በሃገርም ከሃገር ውጭም መጧጧፍ አለበት የሚል ግምት አለኝ፡፡ ለዚህም የአይዲዮሎጅ ምልከታ የሚሰጡ ፕሮፊሰር መስፍን አረጋ፤አቻምየለህ ታምሩና ሌሎችም በመኖራቸው በታሪክ ከተጠያቂነት ለመዳን በርትቶ መስራት ግድ ይላል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share