እረኝነት …
ትልቅ ኃላፊነት …
መሆኑንን አውቃለሁ ።
ግን እኔ
ለወንድሜ መልካም እረኛ ሆኛለሁ ?
ወይስ እኩይ ቅናት ስላደረብኝ
የመጥፊያውን ጉድጎድ እቆፍራለሁ ?
” ከእኔ ቀድሞ በሞተ ! ” ቢዬ እፀልያለሁ ።
………………………………..
ግን ፣ ግን ፣ መቼ ነው ?
ሰው ለሰው መልካም እረኛ የሚሆነው ?
አንዱ ለሌላው ሥኬት ፣ እንቅፋት የማይሆነው ?
መቼ ነው ?
ከጠብ መንጃ አጥር ወጥቶ …
ህይወትን የሚኖራት በጋራ ተስማምቶ ?
መቼ ነው ፤ ሰው አለማወቁን የሚየውቀው ?
ሰው ከአፈር ተፈጥሮ ፤ አፈር እንደሚሆን የሚረዳው ?
……………………………………………………………………..?
ሰው አፈር እስከሚሆን በተራ ፤ በተራ …?
የፈጠረውን ፈጣሪውን ካልፈራ …?
” የክርስቶስ ነኝ ፡፡ ” እያለ በገዳይነት ከተሰማራ…?
” አላህ ! ክበር ! ” እያለ ፣ በአላህ ካልተመራ …?
እግዚአብሔር …
ከእመ አልቦ ሁሉን እንደፈጠረ ካለወቀ …?
ፈጣሪውን በመፍራት ሰው፣ለሰው ካልተጨነቀ ?
ፈጣሪን የመፍራት ጥበብ በውሰጡ ካልደመቀ
ሰው በተግባሩ ገሃነም አይሆንም ወይ ፤ ከፍቅር ከራቀ ?