July 16, 2022
14 mins read

አሳሳች አምባገነናዊ ሥርዓት ምን ዓይነት የህዝብ እንቅስቃሴ ስልት መከተል ይበጃል?

ከገብረ አማኑእል፣

meles and Abiy

በቅርቡ የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ሥልጣናቸውን ለቀዋል። ለዚህም ዋናው ምክንያት ለኮቪድ 19 የወጣውን የመሰባሰብ ህግ፣ በተለያየ ጊዜ ጥሰዋል የሚልና፣ በቅርቡ አንድ የካቢኔያቸው ተሿሚ የሆነ ግለሰብ በመጠጥ መንፈስ ያደረገውን ወሲባዊ ትንኮሳ እያወቁ በሚኒስትርነት በመሾማቸው ነው። በነዚህ ጉዳዮች ላይ ማጣራት በየወቅቱ ተደርጓል፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ይቅርታ በተደጋጋሚ ጠይቀው ራሣቸውንም የወከሉትንም ፓርቲ ለማዳን ብዙ ጥረት አድርገዋል። ሆኖም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሁኔታዎች እየተባባሱ በመምጣታቸው ሥልጣናቸውን ሊለቁ ችለዋል።

ይህ ሁኔታ በዓለማችን ያለውን የህዝብ መብት አያያዝን ሠፊ ልዩነት ፍንትው አድርጎ ያሳየናል። ባለፈው ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓ.ም. በወለጋ የደረሰውን ዘር ማጥፋትን ዓላማ ያደረገ የሰው ልጆች ጭፍጨፋ፣ ግድያና ደም ማፍሰስ፣ በሺዎች ለሚቆጠሩ የሰው ልጆች ሞት ሥቃይና ስደት ምክንያት ሆኖዋል። ነገር ግን ከዚህ ሁሉ እልቂት በኋላ ባለሥልጣናቱ እንደመሪ እጅግ ሊያፍሩበት የሚገባ መግለጫዎችና ምላሾችን ሰጥተው ሲያበቁ፣ የተደረገውን ሁሉ አንድ በምናብ የተፈጠረ ለሚመስል ስውር እጅ አሸክመው፣ በሥልጣናቸው ላይ በፈላጭ ቆራጭነት ቀጥለዋል፣ ላለቀውም ህዝብ ባግባቡ የሃዘን ሥነ-ሥርዓትም አልተደረገለትም። ለተፈጠረውም እጅግ ከፍተኛ ውድመትና ሞት ትኩረት በመንፈግ ወደተለመደው ‘’የልማት’’ ሥራ ተመልሰው ችግኝ በመትከል፣ ህንፃዎችን በመመረቅና በሌሎች ሥራዎች ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ። እልቂቱንም አንደወትሮው ለማረሳሳት ሌሎች ተራ ጉዳዮችን በማራገብ ላይ ይገኛል።

በዓለማችን ብዙ ኣምባ ገነኖች በተለያየ ጊዜ ተከስተዋል። ከነዚህም ወስጥ ሂትለር፣ ስታሊን፣ የጀርመኑ ሞሶሎኒ፣ ሌሎችም በምሳሌነት ታሪክ ያስታውሳቸዋል። እነዚህ በየዘመናቱ የተፈጸሙ ጭፍጨፋዎች የየራሳቸው ምክንያቶች ነበሯቸው።

ሂትለር እ.ኣ.ኣ. 1930 በሰው ልጅ ታሪክ ለተደረገው ከፍተኛውን የሰው ልጆች ዕልቂት ተጠያቂ ሰው ነው። ሂትለር ዘርን ማዕከል ያደረገ የ11ሚሊዮን ሰዎችን ዕልቂት ያዘዘ ነበር። ከነዚህ መካከል 6ሚሊዮኖቹ አይሁድ ነበሩ። በተጨማሪም ሁለተኛውን የዓለም ጦርነት የቀሰቀሰ ሰው ነበር። በመጨረሻም በ1945 ዓ.ም. ራሱን አጥፍቷል።

በጆርጂያ የተወለደው የሶቬት መሪ ለኒን ከሞተ በኋላ ነበር ስታሊን በ1924 ወደ ሥልጣን የመጣው። እጅግ ተጠራጣሪና፣ የፖለቲካ ተገዳዳሪዎቹን በጭካኔ የሚያጠፋ፣ ሰው ነበር። ከ14 – 20 ሚሊዮን የሚገመቱ ሰዎች ጎላጎስ በሚባለው የማሰቃያ ስፍራ በሱ አገዛዝ ዘመን ተገለዋል፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ደግሞ ካገር ተባርረዋል።

ባገራችንም እየተወለደ ያለው ይህ ዓይነቱ የአምባገነንነት ሥራዓት ነው። በመጀመሪያ የታየው ሁሉንም ወደራስ የመውሰድና ሃላፊነትን የመቀበል የሚመስል ነገር ግን ሥልጣንን ለመሰብሰብ የሚያመች አካሄድ ነበር። ለዚህ ብዙ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል። ሁኔታው ይሄ ሆኖ ሳለ ይህ አስተዋይ ህዝብ ድክመቱ ፖለቲከኞችን ማመኑ በመሆኑ፣ ምናልባት የተወሰኑ ሰዎች ካልሆኑ በስተቀር አብዛኛው ግፍ፣ ድህነት፣ መፈናቀልና ውርደት በተሰለቸበት ዘመን፣ ብዙ ህዝብ ምሁራንንም ጭምር ከጀርባ ማሰለፍ የቻለ ሃሰተኛ የፖለቲካ አመራር ነው። ውሎ ሲያድር፣ ሰላማዊ ታጋዮችን በሃሳብ ልዩነታቸውና በተቃውሟቸው ብቻ ‘’በክላሽም ቢሆን አንዋጋችኋለን.. ‘’ ወደሚል ማስፈራሪያ አደገ። ከሁሉም በላይ መጽሃፉ ‘’ ከፍሪያቸው ታውቋቸዋላችሁ…’’ አንዲል፣ የሚሰሩት ስራዎች በተግባር ኣምባገነንትንና ብቻ ሳይሆን አሳሳች አምባገነንነትን፣ የህዝብ ዕልቂት (genocide) የሚያረጋግጥ ሆኖ መታየቱን ቀጥሏል።

የየትኛው ዕምነት ተከታይ እንደሆናችሁ የማናውቅ ቢሆንም፣ መሪዎቻችን የሰውን ልጅ ክብር ምንኛ እንደሚረዱትና እውቅና እንደሚሰጡት ለመረዳት የከበደ ደረጃ ላይ ደርሰናል። በድሆች፣ ስለፖለቲካ በማያውቁ፣ በፈቃዳቸው ባልተፈጠሩበትና ባልሠፈሩበት ስፍራ ለምን ተገኛችሁ በመባል ለሚፈሰው ደም ፖለቲከኞቻችን ግድ ያላቸው አይመስሉም። በአንድ ሰው የመብት መጉደል ምክንያት መንግስት የሚናጥባቸው አገሮች ባሉበት ዓለም፣ የሺዎች በኢሰባዊነት መሞት ህጻን ከሽማግሌ፣ አዛውንት ከወጣት፣ ነፍሰጡር ሳትቀር በየቀኑ በሚገደሉበት በኢትዮጵያ የህሊና ጸሎት አንኳን ማድረግ የማይቻልባት አገር መሆኗን ስናስብ በሃዘን እንዋጣለን። የመንግስትን ለህዝብ እልቂት ተጠያቂ መሆን እግረ-መንገራችንን አናረጋግጣለን። መጨረሻችንንም ለመገመት ኢጅግ አስቸጋሪ ሆኗል።

ይህ ሁሉ ሲሆን እያየን፣ ፍርድና በቀል የፈጣሪ መሆኑን አያመንን፣ እኛስ ከፈጣሪ በታች ምን ናደርግ ይገባናል? የሚለውን ጥያቄ ማንሳት የግድ ይሆናል። አብዛኛው ህዝብ ይህንን ጥያቄ አንደሚጠይቅ እገምታለሁ።

እንደኔ ሃሳብ የደረስንበት ደረጃ የሚጠይቀው የተቀናጀ መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴ ነው። ፍልሚያው ከታጠቀና በዘረኝነት ፖለቲካ ከሰከረ ወገን ጋር ስለሆነ እጅግ የታሰበበትና አንደ ደቡብ አፍሪካው ANC የበሰለ ዘርፈ-ብዙ ትግል ማካሄድ ያስፈልጋል፡ በዚህ ዓይነቱ ጥልቀት ባለውና ዘመኑን በሚመጥን ስልት የሚመራ ትግል ውጤት ያመጣል ‘’እርዱኝ እረዳችኋለሁ።’’ ለሚለውም ቃል ምላሽ ይሆናል ብዬ አምናለሁ። በዚህ ሃሳብ ከታመነ፣ ከየት እንጀምር ወይም የቱን እንቀጥል ለሚለው ጥያቄ ማመላከቻ ሃሳብ ሊኖረን ይገባል።

ባሳለፍናቸው ጥቂት ዘመናት ይህንን ሥርዓት ለመታገል የተጀመሩ የትግል አቅጣጫዎች እንደነበሩ ይታወቃል። አሁንም ብቅብቅ ያሉ ስልቶች እናያለን። በርግጥ ይህ ትግል አንድ ተአማኒ በሆነ የተቀናጀ ሃይል የሚመራ ቢሆን ውጤታማና ዘላቂ ውጤት ያመጣል ብዬ እገምታለሁ። በመሆኑም ለመወያያ ኢንዲሆን የሚከተሉትን ለመጠቆም አፈልጋለሁ፡

  • ካለፈው በተለየ ዘመናዊና በአነስተኛ መስዋዕትነት ውጤት ሊያመጣ የሚችል የትግል ስልት መመርመርና መከተል፣
  • ተንሰራፍቶ ያለውን የዘረኝነት ፖለቲካ በዓለም መድረክ ማጋለጥና እንዲወገዝ ማድረግ፣
  • በስራ ላይ ያሉ የሰብዓዊ መብቶችና ሌሎች ዓለማቀፋዊ ህጎች በኢትዮጵያ እየተጣሱ መሆናቸውን፣ ይልቁንም የሰው ልጅ የመኖር መብት በኢትዮጵያው የዘረኝነት ሥርዓት በአደባባይ የተጣሰ መሆኑንና ሰዎች በየዕለቱ በመንግስት እውቅና እየተገደሉ መሆኑን በማያወላዳ ማስረጃ አስደግፎ በማቅረብ ለዓለም አቀፍ ድርጅቶች የኢትዮጵያን መንግስት በይፋ መክሰስ፣ ከዚህ ቀደም የተጀመሩ ዓለማቀፍ ክሶችን ማጠንከርና መቀጠል፣
  • በተቻለ መጠን ይህ መንግስት የሚያገኛቸውን ርዳታዎችና ብድሮች ለማስቆም ያላሰለሰ ትግል ማድረግ በኢኮኖሚ፣ ያለውን ሥርዓት ማዳከምና ለዘረፋና ለስርቆት የሚውለውን ሃብት ማሳጣት፣
  • በአገር ውስጥ በሚገባ የጠራ የጸረ-ዘረኝነት ሃሳብና አስተምህሮ በተጠናና ለሁሉ ሊዳረስ በሚችል መልክ ማስፋፋት ለዚህም የላቀ ተዓማኒነት ያላቸው የራዲዮ ጣቢያዎችንና የቴሌቪዥን ጣቢያዎችን መጠቀም (በ gofundme የህዝብ ኪስ ሳይራቆት ያሉትን እውነተኛ ሚዲያዎች በማስተባበር ሊካሄድ የሚችል ይመስለኛል።)፣
  • በአገር ውስጥ የሚካሄደው ትግል በሁሉም የኣገራችን ክፍሎች የሚራመድ፣ በተቻለ መጠን የሚሰጠው ትምህርት የወቅቱን የፖለቲካ ቃላት የማይጠቀም፣ ህዝባዊ ይዘት ያለው፣ ሆኖ በተለያዩ ቋንቋዎች አንዲሰጥ ማድረግ፤
  • እውነተኛውን የኢትዮጵያን ማንነት የሚያከብሩና የሚያራምዱ ታዋቂ አንጋፋ ሰዎችን ከአፍሪካ፣ ከአውሮፓና አሜሪካ ወዘተ. በማስተባበር የትግሉ አጋርና ጠበቃ አንዲሆኑ ማድረግ፣
  • በዘመኑ ፖለቲካ፣ ትግልን መጥለፍ አሁን ያለው ሥርዓት ስልት በመሆኑ ትግሉ እንዳይጠለፍ የላቀ ስልታዊ በሆነ መንገድ መከላለከልና ጠንካራ መሠረት አንዲይዝ ማድረግ፣ ወዘተ.

እነዚህ በተቀናጀ መንገድ ከተካሄዱ ሃይል ያላቸው የሰላማዊ ትግል ስልቶች ሊሆኑ ይችላሉና እንወያይባቸው እንተግብራቸው። ያገሬ ሰው ሆይ ቁጭ ብለን ሰው በሚበላው ሥርዓት ተበልተን ሳናልቅ፣ ፈጣን ውጤት ሊያመጣ የሚችል ዘመናዊና ሥልታዊ የሆነ ሠላማዊ እንቅስቃሴ ተጠናክረን ቆመን በማካሄድ ፈጣሪአያችንን አንርዳ!

https://youtu.be/SMVpLbQZ3PY

ዕውነት ያሸንፋል!

የንጹሃን ደም ይደርቃል!

ፈጣሪ ኢትዮጵያን ያድን!

https://youtu.be/mX2IajF0PvY

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
Go toTop