July 15, 2022
11 mins read

“ጥቃት እና ሞት በቃ” ! “ሞት ለገዳይ”

ሁላችንም ኢትዮጵያዉያን ለራሳችን እና ለአገራችን በጎ የሚያስቡትን ፤የሚያስቡትንም በመሬት ለሚዘሩት ኢትዮጵያዉያን ታላቅ አክብሮት አለን ፡፡

በዚህ ረገድ አብን ለህዝብ እና ለአገር ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ ስልጣን ኮርቻ ላይ ሆነዉ እንደሚሽራዋ ከታዘልኩ አልወርድም ብለዉ የስልጣን ቁራኛ ለሆኑት ፖለቲከኞች  የስልጣን ሽግግር ማድረግ የአብን አመራሮች አይነተኛ አብነት ናቸዉ ፡፡

ለዚህም ዓብን በህዝብ ልብ መሆኑ እና ኢትዮጵያዊ ቁመና ያለዉ መሆኑ የማይካድ ቢሆንም ከሰሞኑ የአብን ከፍተኛ አመራር ክቡር ክርስቲያን ታደለ  በኢትዮጵያ ለደረሰዉ እና እየደረሰ ላለዉ ዕልቂት ማስተዛዘኛ እና የኃዘን ቀን መጠየቁን ሰምተናል ፡፡

ሆኖም ኢትዮጵያ ስትፈርስ  እና የህዝብ ዕንባ እና ደም ሲፈስ ለምን ከማይል አስተዛዛኝ እና የዕልቂት ቀን እንዲፈቀድ መጠየቅ “በጎቹን የበላ  ቀበሮ  ሀዘን ይቀመጥ ” እንደማለት እና ህዝባዊ የነፃነት እና የህልዉና ዕንቅስቃሴ ግለቱን  መግታት  ካልሆነ  በዳይ የሚያዝንበት ህሊና የለዉም ፡፡

በኢትዮጵያ ምድር የዘረኝነት  እና የበታችነት ልክፍት የወለደዉ የጥላቻ ፖለቲካ ጉዞ ትንቅንቅ ነባር ባለቤት የአገሩ ዕንግዳ  እና ባዕዳ በማድረግ በፀረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች ደባ ሠዎች ሠዉ በመሆናቸዉ ብቻ ኢትዮጵያዊነት ጠላትነት ሆኖ በማንነታቸዉ ሲዋረዱ ፣ሲሳደዱ እና በግፍ በተፈጥሮ የመኖር ሠባዊ ክብራቸዉን ሲነፈጉ ማየት ላለፉት ሶስት አስርተ ዓመታት የቀጠለ   የክህደት እና ዉርደት  ዶፍ ያስተናገዱበት  ታሪክ ነዉ ፡፡

በብሄር ጭቆና ስም አገርን እና ህዝብን በጠላትነት ፈርጆ የግፍ  የስልጣን ዕድሜ ማራዘሚያ ጠላት አገር እና ህዝብ ሆኖ ኢትዮጵያ ከማለት ክልል ፤ ህዝብ እና ሠዉ ከማለት ብሄር ያለ አገር  ፤አገርም ያለሠዉ እና ህዝብ ምንም እንዳይደለ እየታወቀ በነበረዉ  የበታችነት እና የጥላቻ ፖለቲካ ተርክት ኢትዮጵያዊነት እና ዓማራ በጠላትነት ተፈርጂዉ ብዙ የመከራ እና የሰቆቃ ጊዜ አሳልፈዋል ፡፡

አሁንም የጭቆና ቀንበር በላዩ ተሸክሞ ያለዉ ኢትዮጵያዊ ህዝብ እንደትናንቱ ዛሬም በማንነቱ እና ኢትዮጵያዊነቱ ብቻ ጥቃት ፣ ሞት ፣ዉርደት እና ስደት እያስተናገደ  ይገኛል ፡፡

ግንቦት ፳፣ የክልል አወቃቀር እና የህገ -ኢኃአዴግ   አግላይ  የኢትዮጵያዊነት ማዳከሚያ ስልቶች ስራ ላይ እንዲዉሉ ሆኖ በኢትዮጵያ እና ህዝቦች ላይ የተጫኑት  የጭቆና  ቀንበሮች ኢትዮጵያን እንደ አገር  የነበረ ገናና አቃሟን  በማንገዳደገድ ፤ ህዝቡን  በኢትዮጵያዊነቱ እና በሠዉነቱ እንዳይተማመን  እጂ ከወርች  በመቀፍደድ አሁን ካለበት አድርሰዉታል ፡፡

ይህ ብቻ አይደለም ሳይፈልግ በኢትዮጵያ ምድር ተፈጥሮ  ኢትዮጵያዊ ሆኖ ፣ ለኢትዮጵያ እንደ አገር እንድትቆም በሁሉም የአገሪቷ ግዛቶች በአደም እና በአጥንት የመሰረታትን አገር እንዳይኖርባት ቢኖርባትም በስጋት እና በዉርደት እንዲኖር የተፈረደበት ህዝብ -ዓማራ  በኢትዮጵያ ያልተጫነበት የፖለቲካ ግፍ እና ጉድፍ አልነበረም ፤የለም ፡፡

በሁሉም የአገሪቷ ክፍሎች ለዘመናት ጥቃት ፣ ሞት ፣ዉርደት እና ስደት የሚያስተናግደዉ ሠዉ እና ኢትዮጵያዊ ከመሆኑ ዉጭ ሌላ ምንም ምክነያት አለመኖሩን የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች በጥፋት ስምምነት ሠነዳቸዉ ያመኑበት እና እየተገበሩት ያለ ነዉ ፡፡

ይህ ብቻ አይደለም  ኢትዮጵያዉያን ስሜቱ ላቅ ያለ ነዉ በሚባልበት የኢትዮጵያ ክፍሎች ከጎንድር  ወልቃይትን እና አካባቢዉን ፣ከጎጃም በተከል ፣ ከሸዋ በዙዉን ፣ ከወሎ ራያ እና በወሎ የሚገኝ ልዩ ዞን…. የኢትዮጵያዊ አብነትን እና ተፈጥሯዊ ማንነትን የማዛባት  ኢትዮጵያን የማዳከም ሴራ መሆኑ የክህደት ስምምነት የጠላት የ1968 ዓ.ም .መመሪያ ምስክር ሲሆን በድርጊት የሚገለፅ ነዉ ፡፡

የኢትዮጵያዊ ህዝብ በተለይም  ዓማራ  በፀረ ኢትዮጵያዉያን የዉስጥ እና የዉጭ ጠላቶች ለዓመታት ለደረሰባቸዉ ጥቃት ፣ፍጂት እና ስደት ጠያቂም ሆነ ተጠያቂ ባልነበረበት ዛሬ አስተዛዠኝ መጠበቅ  ገዳይን  ዕጉም ከማለት አይለይም ፡፡

ከግንቦት ሀያ አስራ ዘጠኝ መቶ ሠማንያ ሶስት ዓ.ም. ጀምሮ  በኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊ -ዓማራ ላይ  የደረሰዉ የመድሎ አሰራር  ፣የማግለል እና የማስገደል  ሴራ ኢትዮጵያን የማጥፋት ርምጃ መሆኑ በጥዋት የሚታወቅ ሆኖ በዜጎች ማንነት ተኮር ጭፍጨፋ  በአፋኝነት ፣ በዘረኝነት እና በቀለኝነት ስሜት መሆኑ እየታወቀ  በጊዜዉ የነበረዉ   አግላይ እና በዳይ ስርዓት፣ የስርዓቱ ዘዋሪ ፣ የስርዓቱ ተባባሪ ተጠያቂ አለመሆን፣ በግፍ በማንነታቸዉ ለተጨፈጨፉት ዕዉቅና አለመስጠት  እና መታሰቢያ አለመኖር   እና ለዚህም ኃላፊነት የሚወስድ አካል በሌለበት አስተዛዛኝ ማለት ከሞኝነት ዉጭ ሌላ ሊሆን አይችልም ፡፡

በቀይ ሽብር ሰማዕት ለሆኑት ሞት  ምክነያት  በፖለቲካ ዓመለካከት  እንደሆነ እና ለዚህም ተጠያቂ በከተማ ላይ ጥጥቅ ትግል የጀመሩት የዛሬ ነፃ አዉጭዎች መሆናቸዉ ለዚህ ተጠያቂ ሳይሆኑ ምንም ዓይነት የፖለቲክም ሆነ የሌላ ወገንተኝነት የሌለዉን ለፍቶ አዳሪ  ኢትዮጵያዊ በማንነቱ ለደረሰበት ዕልቂት ኃላፊነት ባልወሰደበት ሁኔታ  አስተዛዘኝ  መፈለግ ሳይሆን በህብረት እና በአንድነት “ኃዘን በቃን ” “ ሞት ለጠላት ” ማለት  ይገባል ፡፡ ካልሆነ ጉንፋን ሲያስታምሙት ወረርሽኝ ይሆናል ፡፡

ተጎጂዉ ኢትዮጵያዊዉ ሆነ ዓማራ  ላለፉት ረጂም ዓመታት  በግፍ እና በጭካኔ በደል እና ግፍ ለደረሰባቸዉ ወገኞች አንድነቱን እና ኅብረቱን በማጠናከር ፡-

  • ለሞቱት መታሰቢያ በማድረግ መዘከር ፣
  • መታሰቢያነቱ በዋና ከተማ እና በሞቱበት አካባቢ
  • ርዳታ እና ዕገዛ ለሚያስፈልጋቸዉ ዜጎች ሁለንተናዊ እና ተደራሽ  ትብብር ማድረግ ፣
  • “ግንቦት ሀያ  የጥልመት እና ሞት ዕለት  ”  ሆኖ ብሄራዊ በዓል ሆኖ እንዲከበር ለዚህ ኢትዮጵያዉያዊ ሁሉ የሚተገብረዉ እንዲሆን ፣
  • በምንም ዓይነት በግፈኞች የአድሎ እና መድሎ አስተዳደር ዘመን ለሆነዉ ማንኛዉም ዓይነት  የአገዛዝ ችግር ምክነያት ለደረሰ ጥፋት ሁሉ ተቋማዊ(ድርጅታዊ) እና ግለሰባዊ ተጠያቂ እንዲኖር መስራት እና ብሄራዊ እና ዓለማቀፋዊ ፍትህ እንዲገኝ ማድረግ ፣

ሲቻል ያኔ የኢትዮጵያ ጠላቶች ዛሬ በኢትዮጵያ ና ህዝቦች መከራ እንደሚደሰቱ  ሁሉ ዋጋ የሚከፍሉበትን ኃይል በመፍጠር ሁሉም ዓለም ከተበደሉት እና ከተገፉት ጎን ይቆማል፡፡

ከዚህ ዉጭ ገዳይን  ለኃዘን አፅናኝ እንዲሆን መማፀን ሳይሆን ጥቃት እና ሞት በቃ ብሎ  ዕምቢ ለአገሬ ፣ ለዳር ድንበሬ ፣ለማንነቴ ለእኔነት ክብሬ ማለት ብቻ ነዉ

ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት የአምስት ትዉልድ የሚሆን በጎ እና አርቆ አሳቢ የህዝብ አመራር/ ፖለቲካ  እንጂ  ስቆ አጥልቅ አዛኝ የአምስት ዓመት ዉል ለማደስ በየአምስት ዓመቱ  መደባደጃ ለፖለቲካ ንግድ የሚመላለስ መሆን የለበትም፡፡

“በኢትዮጵያ ጥቃት እና ሞት በቃ ! ”

“ሞት ለገዳይ ”

 

NEILLOSS Amber

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
Go toTop