ዓለማየሁ ገላጋይ ሚያዝያ 5 /1960 ዓ.ም በ አራት ኪሎ አካባቢ ተወለደ። በዳግማዊ ምኒልክ ፩ኛ ፪ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተምሯል። በ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ስኩል ኦፍ ጆርናሊዝም ተምሮ ተመርቋል።
=ዓለማየሁ ገላጋይ “ኔሽን” ፣ ” አዲስ አድማስ ” ፣ “ፍትሕ” ፣ “አዲስ ታይምስ” ፣ እና “ፋክት”ን ጨምሮ በተለያዩ ጋዜጦችና መጽሔቶች ላይ በሚያቀርባቸው መጣጥፎች ይታወቃል።
=ሥራዎች
– ስብሐት ገብረእግዚአብሔር ሕይወትና ክህሎት፣ ቅበላ፣ የብርሃን ፈለጎች፣ ኢህአዴግን እከሳለሁ፣ኩርቢት፣ ወሪሳ፣ አጥቢያ፣የፍልስፍና አፅናፍ ፣በፍቅር ስም ፣ መለያየት ሞት ነው ፣በእውነት ስም(ታለ) ፣ውልብታ፣በእምነት ሥም (ሐሰተኛው) የተሰኙ ልቦለድ ና ኢልቦለድ መፃሕፍት ለአንባቢያን አበርክቷል።
ከዚህ በተጨማሪም “መልክዓ–ስብሐት ” በተሰኘው መጽሐፍ 27 ጸሐፊያን፣ያን ደራሲያን፣ገጣሚያንና ሰዓሊያን አሳትፎ በማሰናዳት ለአንባብያን አድርሷል።
ዓለማየሁ ገላጋይ በሃያሲነትም ስም ያተረፈ የብዕር ሰው ነው። ገና ለሕትመት
ያልበቁ በርካታ ሥራዎችም አሉት።
ምንጭ፦Wikipedia