April 18, 2022
3 mins read

“የብልፅግና አመራሮች የእርስ በእርስ ንትርክ ለሃገር ስጋት ሆኗል” – ኢዜማ

Ezema 1 1በመንግስት አካላት መካከል የሚታዩ መፋጠጦች እንዲረግቡ ካልተደረጉ ችግሩ ወደ ህዝቡ በመውረድ አጠቃላይ ሀገራዊ ቀውስ ውስጥ ሊከቱን ይችላሉ ሲል ያስጠነቀቀው ኢዜማ፤ ሃገር እየመራ ያለው የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች የእርስ በእርስ ንትርክና ፀብ ለሃገር ስጋት ሆኗል ብሏል፡፡

 

በብልጽግና ስር ተጠቃለው ክልሎችን ለመምራት በስልጣን ላይ የተቀመጡ የብልጽግና አመራሮች ተናበውና  ተቀናጅተው ሃገሪቱን ከገጠማት ዘርፈ ብዙ ፈተና ለማውጣት በጋራ መስራትና ከህዝቡ አንድ እርምጃ ቀድመው የመፍትሔ ሃሳብ ከማቅረብ ይልቅ በየጊዜው እርስ በእርስ እየተናከሱ አለፍ ሲልም ለፀብ እየተጋበዙ፣ ከኑሮ ውድነቱ  በላይ ራሳቸው አመራሮቹ የሃገር ስጋት ሆነዋል ሲል ጠቅሷል፡፡
“ብልጽግና ውስጥ የሚፈጠርን ችግር የማምለጫ መንገድ ተደርጎ እየተወሰደ ያለው ህዝብን ከህዝብ ማጋጨት ነው” ያለው ኢዜማ፤ የህዝብን አብሮ የመኖር እሴት በቋሚነት በመሸርሸር የመንደራቸው አውራ ለመሆን የሚታትሩ የብልጽግና አመራሮች ከዚህ  አስነዋሪ ድርጊታቸው ሊታቀቡ ይገባል” ሲል አሳስቧል – ፓርቲው።

 

በአሁን ወቅት በሃገሪቱ ላይ የተደቀኑ ኢኮኖሚያዊ፣ማህበራዊና ፖለቲካዊ ችግሮች ጥልቅና ዘርፈ ብዙ መሆናቸውን ያመለከተው ፓርቲው፤ እነዚህ ችግሮች ከግብታዊነትና ከእልህ በወጣ መልኩ በመነጋገርና በመግባባት ብቻ የሚቀረፉ መሆኑን በማመን ሁሉም አካላት ሃገራቸውን አስቀድመው በሰከነ መንገድ ወደ መነጋገሩ መድረክ እንዲመጡ ጥሪ አቅርቧል፡፡
አሁን በሃገሪቱ ባሉ ችግሮች ላይ ተጨማሪ ችግሮችን  መፍጠር መጠፋፋትን  እንደሚያስከትል የተቆመው ኢዜማ፤ በብሔር ዘውግ ጫፍና ጫፍ ሆነው መጓተት ውስጥ የገቡ አካለት ከእለት ወደ እለት ሃገሪቱን ብዙ ዋጋ እያስከፈሏት ነው ብሏል፡፡

 

እነዚህ በሃገሪቱ ላይ የተጋረጡ ስጋቶችንና የተደቀኑ አደጋዎችን አስመልክቶ መፍትሔ ለማበጅት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ለመነጋርና ለመወያየት ዝግጁነቱን የገለፀው ኢዜማ፤ ለሃገሪቱ ሠላምና ለህዝቦች አንድነት፣ የሃይማኖት መሪዎች የሃገር ሽማግሌዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ምሁራን የዚህ ሂደት ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop