April 8, 2013
5 mins read

በቤንች ማጂ ከ350 በላይ አማርኛ ተናጋሪ ዜጎች ከቦታቸው ዳግም ተፈናቀሉ፤ ሕዝቡ ጫካ ውስጥ ተጠልሏል

ከዚህ ቀደም ከጉራ ፈረዳ የተባረሩ አማሮች (ፎቶ ፋይል)
በቤንች ማጂ ከ350 በላይ አማርኛ ተናጋሪ ዜጎች ከቦታቸው ዳግም ተፈናቀሉ፤ ሕዝቡ ጫካ ውስጥ ተጠልሏል 1
በደቡብ ክልል ቤንች ማጂ ዞን በሚገኘው ሜኒት ወልድያ ወረዳ በተለይም ዘንባብናአርፋጅ ቀበሌ ነዋሪዎች በካከል ከ350 በላይ የአማርኛ ተናጋሪ ዜጎች ተፈናቅለው በወረዳው አካባቢ በሚገኝ ጫካ ውስጥ ተጠልለው እንደሚገኙ አስታውቀዋል፡፡
ማን እንዳደራጃቸው በማይታወቁ ግለሰቦች ከመኖሪያ አካባቢያቸው 61 ከብቶችና ግምቱ ያልታወቀ እህል ተዘርፈው አካባቢያቸውን ጥለው ለመውጣት የተገደዱት አማርኛ ተናጋሪ ተፈናቃዮቹ ተሸሽገው ባሉበት ጫካ ለከፍተኛ ርሃብና ውሃ ጥም መዳረጋቸውን ለፍኖተ ነፃነት ጨምረው ገልፀዋል፡፡
ከተፈናቃዮች መካከልም 4 በግፍ መገደላቸውንና የወረዳው አስተዳደር አካላት “እናጣራለን” ከማለት ውጭ ምንም መልስ ባለመስጠታቸው ጉዳዩ እየባሰ በመሄዱ ንብረቶቻቸው ተዘርፈው በአሁን ወቅት ለዓመታት የኖሩበትን አካባቢ ጥለው በጫካ መጠለልን መምረጣቸውን ተፈናቃዮቹ በተለይ ለፍኖተ ነፃነት ገልፀዋል፡፡
እንደተፈናቃዮቹ ገለፃ ከሆነ በአሁን ወቅት ከወረዳው ፖሊሶች ውጭ የአስተዳደሩ አካላት በግፍ መፈናቀላችንን በተመለከተ ያላቸውን ውሳኔ እንዲያሣውቁን ብንጠይቅም ምላሽ የሰጠን ባለመኖሩ አሁንም ለከፍተኛ ችግር በመጋለጣችን የሚመለከተው የመንግስት አካል ምላሽ እንዲሰጠን እንፈልጋለን ብለዋል፡፡
በተለይ ጉዳዩ ላይ የደቡብ ክልላዊ መንግስት የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ የሆኑት አቶ ሁሴን በበኩላቸው “በአሁን ወቅት በክልሉ ምንም ዓይነት የአማርኛ ተናጋሪ ዜጎችን ማፈናቀል ስራ አልተካሄደም፤ የተላለፈ መመሪያም የለም፤ እንደውም በተለያየ ምክንያት ከተለያየ ቦታ ወደ ክልሉ የመጡትን እንኳ እየተንከባከብን ነው” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
ከተፈናቃዮቹ ጋር በተያያዘ የአማራ ክልላዊ መንግስት ያለውን አቋም ለማረጋገጥ የክልሉ ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ ወደ ሆኑት አቶ ንጉሴ ጋር ደውለን ጉዳዩን ስናነሳላቸው ስልካቸውን የጋዜጠኛው ጆሮ ላይ በመዝጋታቸው የክልሉን መንግስት አቋም ልናረጋግጥ አልቻልንም፡፡
በተለያየ የሀገሪቱ ክፍል ዜጎችን የማፈናቀሉ ጉዳይ እየቀጠለ በመሆኑና ዜጎች በሀገራቸው የመኖር ነፃነታቸውን የማክበርና የማስከበር ኃላፊነት ምን ያህል እየተተገበረ ነው የሚለውንና የዜጎችን ከነበሩበት ቦታ ቋንቋን መሰረት በማድረግ ብቻ ማፈናቀል መንግስት የሚከተለው ፖሊሲ ትግበራ መሆኑን ለማረጋገጥ የፌደራሉ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት
ምክትል ሚኒስትር አቶ ሽመልስ ከማልን ጠይቀናቸው “አሁን ከሰው ጋር ነኝ ትንሽ ቆይተህ ደውል(ሰዓት ቀጥረው) ቢሉም ባሉት ሰዓት ሲደወልላቸው ስልካቸውን ሊያነሱ አልቻለም፡፡ ከዚህ በፊት በዚሁ ቤንች ማጂ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ የሚኖሩ አማርኛ ተናጋሪዎች በክልሉ መንግስት ፕሬዘዳንት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ልዩ ትዕዛዝ ፤ በቅርቡ ደግሞ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያሶ ወረዳ ያሉ አማርኛ ተናጋሪ ዜጎች ያፈሩትን ሀብትና ንብረታቸውን ጥለው እንዲፈናቀሉ መደረጉ ይታወቃል፡፡

ምንጭ፡ ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ የሰኞ ኤፕሪል 8 ዕትም

Latest from Blog

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

ትላንት አንድ ወዳጀ ደውሎ “አሳየ ደርቤን” ታውቀዋለህ ወይ” አለኝ፡፡ እኔም አላውቀውም አልኩት፡፡ ኢንጅኔር “ኡሉፍ” የተባለ ሰው የዛሬ ሰባት ዓመት ያሰራረውን ጥልቀትና ስፋት ያለውን ዘገብ አቅርቦታልና አዳምጠው አለኝ፡፡ እኔም “ጉድሺን ስሚ ኢትዮጵያ–ከባድ አደጋ

ተቆርቋሪ የሌላት ኢትዮጵያ – አክሎግ ቢራራ (ዶር)

ወገኖቸ፤ ለጊዜው ትችቱን እናቁምና ለወገኖቻችን እንድረስላቸው፡፡፡ በቤተ አማራ ወሎ ቡግና የተከሰተው ርሃብ ጉዳት ቀላል አይደለም፡፡ ለወገን ደራXኡ ወገን ስለሆነ እባካችሁ ህሻናትን እናድን፤ ለግሱ፡፡ ጦርነት ያመክናል፤ ተከታታይ ጦርነት አረመኒያዊነት ነው፡፡ ጦርነት ካልቆመ የረሃቡ

እግዚኣብሔር ግን ወዴት አለ?

ልዩ ቆይታ ከገዱ አንዳርጋቸው ጋር ! – “ዐብይ ቂም የያዘ የነጣቂ መንግስት መሪ ነው”/ “አማራ እየተዋጋ ያለው ሰላምን ፍለጋ ነው” – ክፍል አንድ ልዩ ቆይታ ከገዱ አንዳርጋቸው ጋር ! –

“ፋኖ የበለጠ ይደራጃል ወደ ኋላ አይልም!”/ “የትግራይን ህዝብን ይቅርታ ጠይቂያለሁ” “ፋኖ በናፍቆት እየተጠበቀ ነው” ገዱ አንዳርጋቸው (ዶ/ር)

December 28, 2024
ፈቃዱ በቀለ (ዶ/ር) (ታህሳስ 19፣ 2017) December 28, 2024 መግቢያ እንደተነገርን ኢትዮጵያን “ከዕዝ ወይም ከሶሻሊስታዊ” ኢኮኖሚ አላቆ ወደ “ ነፃ ገበያ ኢኮኖሚ” እንድትሸጋገር ከተደረገ ይኸው ከ31 ዓመት በላይ ሊያስቆጥር ነው። በጊዜው ስልጣንን የተቆናጠጠው የህወሃት አገዛዝ

ሁለ-ገብ ለሆነ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ዕድገት መሰረት የሚጥል ህግ፣ ወይስ የኢትዮጵያን ሀብት የሚያዘርፍና ህዝብን አቅመ-ቢስ የሚያደርግ አዲስ የባንክ ህግ- ከኒዎ-ሊበራሊዝም ወደ ባሰ ኒዎ-ሊበራሊዝም የዝቅጠት ጉዞ!

ልዩ ቆይታ ከገዱ አንዳርጋቸው ጋር ! – “ዐብይ ቂም የያዘ የነጣቂ መንግስት መሪ ነው”/ “አማራ እየተዋጋ ያለው ሰላምን ፍለጋ ነው” – ክፍል አንድ

ልዩ ቆይታ ከገዱ አንዳርጋቸው ጋር ! – “ዐብይ ቂም የያዘ የነጣቂ መንግስት መሪ ነው”/ “አማራ እየተዋጋ ያለው ሰላምን ፍለጋ ነው” – ክፍል አንድ

December 27, 2024
የሲቪል ማህበረስብ ድርጅቶች ባለስልጣን፤ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) እና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከልን (EHRDC) “ገለልተኛ ባለመሆን ከተቋቋሙበት ዓላማ ውጭ ተንቀሳቅሰዋል” በሚል ምክንያት ማገዱ ገለጸ። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል (EHRDC)

መንግስት ኢሰመጉ እና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከልን አገደ፤ የታገዱ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቁጥር አራት ደረሷል

December 26, 2024
Go toTop