April 8, 2013
3 mins read

ምርጫ እስኪያልፍ ድረስ ሙዚቃ ቤቶች ሃገር ፍቅር ቀስቃሽ ዘፈኖችን እንዳይከፍቱ ተከለከሉ፤ የቴዲ አፍሮና ጸጋዬ እሸቱ ይገኙበታል

በአዲስ አበባ የተለያዩ ስፍራዎች በሚገኙ መዝናኛዎችና ሙዚቃ ቤቶች በሚያዝያ መጀመሪያ የሚደረገው የአካባቢ ምርጫ ሳያልፍ ሀገር ፍቅር ስሜት የሚቀሰቅሱ ዘፈኖችን እንዳይከፍቱ ክልከላ ተደረገ፡፡ ከጥቂት ቀናት በኋላ በሚደረገው የከተማ መስተዳድርና የአካባቢ ምርጫ ብቻውን የሚወዳደረው ኢህአዴግ በካድሬዎቹ አስገራሚ ትዕዛዞችን እየሰጠ እንደሚገኝ
የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ጠቆሙ፡፡
በአዲሱ ትዕዛዝ መሰረት ምርጫው እስኪያልቅ ድረስ ሙዚቃ ከፍ አድርገው የሚያጫውቱ ሙዚቃ ቤቶችና የመዝናኛ ስፍራዎች የሀገር ፍቅር ስሜት የሚቀሰቅሱና ስለባንዲራ የተዜሙ ዘፈኖችን መክፈት ተከልክለዋል፡፡ በትዕዛዙ በተለይ የተከለከሉት የቴዲ አፍሮና የፀጋዬ እሸቱ አዲሱ አልበም ላይ የተካተቱት ዜማዎች ይጠቀሳሉ፡፡ ነጋዴዎቹ “ክልከላው ከምርጫው ጋር ምን እንዳያያዘው አልገባንም፣ሆኖም ከመንግስት የመጣ ትዕዛዝ ስለሆነ ላለፉት ሁለት ሳምንታት ዘፈኖቹን ማጫወት አቁመናል” ብለዋል፡፡
ነጋዴዎቹ ጨምረው ለፍኖተ ነፃነት እንደገለፁት በተለያየ ጊዜ ለቁጥጥር የሚመጡት የወረዳ ካድሬዎች የተከለከሉትን ዘፈኖች ተከፍቶ ከሰሙ ዛቻና ማስፈራሪያ እንደሚያደርሱባቸው ፡፡ “የቴዲን ዘፈን በተለያዩ ወቅቶች አትክፈቱ ተብለን እናውቃለን” የሚሉት ነጋዴዎቹ የፀጋዬ እሸቱ አዲሱ አልበም ውስጥ ያሉት ሀገርንና ባንዲራን የሚመለከቱ ዘፈኖች
በሬዲዮ እየተለቀቁ እነሱ እንዳይከፍቱ መደረጋቸው እንዳስገረማቸው ገለፀዋል፡፡ ምንጮቻችን ተዘዋውረው ያነጋገሯቸው ነጋዴዎች እንደገለፁት ይህ ክልከላ ጎልቶ የታየው በመርካቶና በፒያሳ አካባቢ ነው፡፡

ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ 2ኛ ዓመት ቅጽ 2 ቁ 71

ምንጭ፡ ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ የሰኞ ኤፕሪል 8 ዕትም።
ሙዚቃ ቤቶች ምርጫ እስከሚያልፍ ድረስ እንዳይከፍቱ፤ በራድዮም ሆነ በቲቪ እንዳይሰሙ ከተከለከሉ ሙዚቃዎች መካከል የሚከተለው ይገኝበታል።

 

Latest from Blog

ከሰሞኑ ታዛቢዎች በተገኙበት ከመንግስት ጋር ውይይት እንዳደረገ እና ለድርድር ዝግጁ እንደሆነ የገለፀው በእስክንድር ነጋ የሚመራው የፋኖ ክንፍ ድርድሩ በውጭ ሀገራት እንዲሆን እየጠየቀ መሆኑ ታውቋል። የመሠረት ሚድያ ምንጮች እንደተናገሩት ታጣቂ ክንፉ ድርድሩ በአውሮፓ

በእሰክንድር ነጋ የሚመራው ፋኖ’ ከመንግስት ጋር ለመደራደር ተዘጋጅቷል

January 26, 2025
የኦህዴድ መራሹ ብልፅግና  መንግስት  በአማራ እና በኦሮሚያ ክልል በንጹሀን  ዜጎች ላይ እየወሰዳቸው ያሉ የነፃ እርምጃ  ግድያዎች  መንግስት ያሰበውን የፖለቲካ ግብ ያሳካለታል  ወይ ? በኔ አመለካከት እነዚህ የንፁሃን ዜጎች  የጅምላ ግድያዎች  በሁለት በኩል እንደተሳለ ቢላዎ (double edge sword) ናቸው:: ፩- መንግስት እያሰላው

 የኦህዴድ መራሹ ጅምላ ግድያዎች ስሌት (ሸንቁጥ- ከምዕራብ ካናዳ)

January 24, 2025
እነዶ/ር ደብረፅዮን እና በጠ/ሚ ዐብይ አህመድ በተሾሙት የትግራይ ጊዜያዊ መንግሥት መሪዎች እነጌታቸው ረዳ መካከል የነበረው አለመግባባት ተካርሮ ሰራዊቱን ወደውግንና አስገብቷል። የትግራይ ሐይል አዛዦች ትላንት ባወጡት መግለጫ ውግንናቸው ከእነዶ/ር ደብረፅዮን ጋር መኾኑን አስታውቀዋል።

በትግራይ የተፈጠረው ምንድነው?

January 23, 2025
የድሮ መሪዎች ያላደረጉትን ምሁር ጳጳሳቱ ያላስተዋሉትን ከፈረሰች ጎጆ ከባልቴት ቤት ገብቶ ክብሩን ዝቅ አድርጎ ውሀዋን ጠጥቶ ምግቧንም ተጋርቶ ያላለቀሰ ሰው ያንን ትይንት አይቶ ማን ይኖራል ከቶ? በዉሸት ፈገግታ ፊቱን አስመስሎ ፀሀይ የበራበት

ሰው በሰውነቱ – ከ ይቆየኝ ስሜ

Go toTop