March 12, 2022
3 mins read

በመርካቶ የ32 ቀበሌ ወጣቶች በብዛት ታሰሩ፣ ሰፈራቸውን ለቀው እየጠፉ ናቸው

275693327 539117197779540 6499245695507069949 nበአዲስ አበባ ክፍለ ከተማ በተለምዶ “32 ቀበሌ” ተብሎ በሚጠራው አካባቢ /ከፋሲል ፋርማሲ ገባ ብሎ/ እስካሁን ለጊዜው ቁጥራቸው በትክክል የማይታወቅ ወጣቶች የታሰሩ ሲሆን፣ ፍርድ ቤት ቀርበው ለመጋቢት 9/2014 ዓ.ም የተቀጠሩና ምርመራ ያልጨረሱ ቢሆንም፣ እንደ ድንገት ከተማ ዳር ወዳለው አባ ሳሙኤል ተጭነዋል፡፡ እዚያም ትላንት በድንገት ወደ አባ ሳሙኤል ከተወሰዱት 46 የባልደራስና የአዲስ አበባ ወጣቶች ጋር ተቀላቅለዋል፡፡
የ32 ቀበሌ ወጣቶችም፣ በአድዋ ክብረ በዓል ወቅት “ባለሥልጣናትን አዋርዳችኋል፣ ህገወጥ ሰንደቅ አላማ ይዛችኋል” ተብለው ተከሰዋል፡፡ ከተያዙት መካከል በክብረ በዓሉ ላይ ጭራሽኑ ያልተገኙ የተካተቱበት በመሆኑ፣ የጅምላ እስሩ ዓላማ የአዲስ አበባ ወጣቶችን ቅስም ለመስበር ታስቦ እየተፈፀመ ስለመሆኑ ማሳያ ሆኗል፡፡
በ32 ቀበሌ ያለው አፈሳና የፖሊስ ወከባ በእጅጉ በመጠናከሩ፣ በርካታ ወጣቶች ሰፈሩን እየለቀቁ ወደ ሌላ ሰፈር እየተሰደዱ ናቸው፡፡ ቤተሰብም በጭንቀት ላይ ይገኛል፡፡ 32 ቀበሌ በምርጫ 97 በርካታ ወጣቶች የተገደሉበት፣ የታሰሩበትና የአካል ጉዳት የደረሰበት ሲሆን፣ አሁን በሰፈሩ ያለው ድባብ ከዚያን ጊዜ ከነበረው የጭንቀት መንፈስ ጋር እንደሚመሳሰል የአካባቢው ነዋሪዎች ለባልደራስ ተናግረዋል፡፡ ከታሰሩት ወጣቶች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡-
1. አብዲሳ ቦሩ
2. ቴዎድሮስ ንጉሴ
3. ሮቤል ጫላ
4. አልአዛር ትዕግሥቱ
5. ደሳለኝ ጥላሁን
6. ስንታየሁ አበባው
7. ኃይሉ መሀመድ
8. እንዳለው አስራት
9. እንቁ ስለሺ
10. ሱራፌል ሞላ
11. ዳግም መንግስቱ
12. ይድነቃቸው ገብሬ
13. ዮናስ ደሳለኝ
14. ሳምሶን ግርማ
15. አቤል ሰለሞን /ሱማሌ ተራ/
ማሳሰቢያ፡- የአያት ስም ስላልተጠቀ፣ ካልተያዙ ሰዎች ጋር የስም መመሳሰል ሊኖር እንደሚችል ግምት ውስጥ ይግባ።

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop