ታጥቦ ጭቃ፣ አድሮ ቃሪያ – በድሉ ዋቅጅራ

ኢትዮጵያ ውስጥ የማያጋጭን፣ የማያዋጋን፣ የተቀበልነው ልዩነት ግለሰባዊ መጠሪያ ስማችን ብቻ ይመስለኛል፡፡ ዛሬ የፖለቲካ አመለካከት ልዩነት፣ የማንነት ልዩነት፣ የሀይማኖት ልዩነት፣ ሰንደቅ አላማና ህገመንግስት ላይ ያለን ልዩነት፣ ወዘተ. በሙሉ ህይወት የሚጠፋበት ግጭት ውስጥ ይከተናል፡
ልዩነታችን ሲሻል መበሻሸቂያ፣ ሲከፋ መጋጫ ነው፡፡ ከወያኔ አገዛዝ ጀምሮ እስካሁን እንደሚታየው ደግሞ፣ አብዛኞቹ በየደረጃው ያሉ የመንግስት አካላት/ተቋማት፣ የሀይማኖት ተቋማት፣ በተመሳሳይ ፖለቲካዊ አመለካከት ስር የተደራጁ ቡድኖች፣ . . የመበሻሸቁና የግጭቱ መሪ ተዋንያን ናቸው፡፡
ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ከበቂው በላይ ፈተና ላይ ነን፡፡ በጦርነቱ ምክንያት የሞተው፣ የወደመው የትየለሌ ነው፡፡ ኢኮኖሚው እየተንገታገተ የኑሮ ውድነቱ ፈተና ሆኗል፡፡ የመንግስት አካላትና የሀይማኖት ተቋማት በዚህ ወቅት የሚጠበቅባቸው የዜጎችን ፈተና ማቅለል እንጂ ማክበድ አይደለም፡፡ ባለፈው ሳምንት በመስቀል አደባባይ በሀይማኖት ጉባኤ ስም የተፈጠረው ሁከት፣ በጥምቀት በአል የሰንደቅ አላማ አጠቃቀም ላይ የተነሳው ውዝግብና በጸጥታ ሀይሎች ‹‹አረንጓዴ÷ቢጫና ቀይ የለበሰ ታቦት አጃቢ አናሳልፍም›› ሰው መሞቱና መቁሰሉ፣ ካለንበት ሁኔታ አንጻር የማይጠበቅ፣ ለዜጎችና ለሀገር አለማሰብና አፍራሽ ተግባር ነው፡፡
በመንግስት የሚታዘዝ የጸጥታ ሀይል፣ እንኳን የሀገራቸውን የጠላትንም ባንዲራ ቢለብሱ፣ ታቦት አጅበው በሚሄዱ ምእመናን ላይ አስለቃሽ ጭስና ጥይት እንደምን ሊተኩስ እንደሚችል ሊገባኝ አይችልም፡፡ የጸጥታ ሀይል የማንን ጸጥታ ነው የሚጠብቀው? ታቦት ያጀበ ምእመን ላይ የሚተኩስ (በምንም ምክንያት ይሁን) የጸጥታ ሀይል፣ መስጊድና ቤተክርስቲያን በመድፍ ከደበደበው ትህነግ የከፋ ነው፤ ትህነግ ሽብርን አውጆ የተነሳ ሲሆን፣ የጸጥታ ሀይሉ ሰላምህን እጠብቃለሁ ባለው ህዝብ ላይ ነው ይህን የሚፈጽመው፡፡ ‹ታጥቦ ጭቃ፣ አድሮ ቃሪያ› እንዳይሆን ይህ ጊዜ ሳይሰጠው መታረም አለበት፡፡
በድሉ ዋቅጅራ

 

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሰውእየው(አንድ ሁለት) (አጭርልብወለድ) - በመኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

1 Comment

  1. ወንድሜ በድሉ ይህ ሆን ተብሎ በኦሮሞ ጠባብ ብሄርተኞች የተፈጸመ ተግባር ነው። ሰው ዝም ብሎ በባንዲራ በዚህም በዚያም ይላል እንጂ ጉዳዪ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ የቆመችለትን የአንድነትና የሃገር ፍቅር ከመጥላት የፈለቀ የዘር ጥላቻ ነው። የኦሮሞ ጠባቦች ከወያኔ ቢከፉ እንጂ አይሻሉም። ለዚያም ነው የወያኔ ጉዳይ አስፈጻሚ የሆኑት። ተኳሽና አስተኳሽ እንዲሁም የቄሮ ቆመጥ አንጋቾችን ወደ ህግ እስካላመጣ ድረስ የጠ/ሚሩ በየአደባባዪ መደስኮር ዋጋ ቢስ ነው። ግፈኞችን ወደ ፍርድ ማቅረብ አስፈላጊ ነው። ሞተና ቆሰለ ብሎ ፋይል የሚዘጋባት የእብድ ሃገር ኢትዮጵያ ብቻ ናት። ለነገሩ የኦሮሞ ፍርድ ቤት የኦሮሞን አጥፊ እንዴት ባለ ሂሳብ ነው በደለኛ ናችሁ ብሎ የሚፈርደው? ይህ መንጋ እኮ በአርሲ፤ በሃረር፤ በሰበታ፤ በሻሸመኔና በሌሎች ከተሞች አንገት ከሚቀሉት፤ ቤት ዘግተው ሰው በእሳት ከሚያጋዪት፤ የእህል ክምር ማገዶ አርገው ከሚሞቁት ጭራቆች ሥራና ተግባር ጋር የተገናኘ ነው። ሰውን ባልሰራው ሥራ ዘቅዝቆ የሚሰቅል ስብስብ ነው።
    ስለዚህ ጉዳዪ ግብታዊ እንደሆነና በክልል ፓሊሱ ብቻ እንደማይደገፍ አድርጎ መውሰድ ስህተት ነው። በመንግስት መዋቅር ውስጥ ዛሬም ቋንጭራ ያነገቱ አሉ። ይህ የእነርሱ ሥራ ነው። ከንቲባ አዳነችን እንዲህ አርጋ ያን ሰርታ የሚሉት ሁሉ ስተዋል። ሴራው ውስጥ እሷ የለችበትም። ከእርሷም ከፍ ባለ ሁኔታ የተቀናበረ የድርቡሽ ተግባር ነው። ይህ የሰውና የአራዊት ክምችት ስትዘፍን የሚያለቅስ፤ ስታለቅስ የሚስቅ በዘሩና በቋንቋው የሰከረ ጥርቅም ነው። እንደ እንቁራሪት አንድ ሲጮህ ሌላው አብሮ የሚንጫጫ የራሴ የሚለውን የማያውቅ፤ ሰርቶ ሳይሆን ቀምቶ መኖርን የሚመርጥ ቡድን ነው። ገና ብዙ ገመና ሃገሪቷን ይጠብቃታል። የዘርና የቋንቋ የአፓርታይድ ፓለቲካ ሆን ተብሎ የተጠመደ ፈንጂ ነው። በዚህ የፓለቲካ ስሌት ግን አንድም ሰው አያተርፍም። ያተረፈ ቢመስለው እንኳን ውሃ መዝገን ነው የሚሆነው። ከያኒ ካሣ ተሰማ በዘፈኑ ላይ እንደሚለን ” የጫረው እሳት ሲፈጀው ታዬ” ነው። ጊዜ ይሸረሸራል። ዛሬ የቆመው ነገ ይጎብጣል። የራሳቸውን ሸፋፋና አሳፋሪ ባህሪ ሳይገቱ እጃቸውን አንስተው “ተፈጥሮን እንቆጣጠራለን” ብለው ያፋከሩት እንደ ጉም ተነዋል። የአሁኑም ሽርጉድ ገልቱነት ነው። አብሮ መኖር ነበር ሰውን ሰው መሆኑን የሚለየው። ያ እድሜ ለወያኔ ተንዷል። አትራፊ በሌለበት የፓለቲካ ንግድ ላይ ለተሰማሩ ሰዎች ግን መጥኔ ለእናተ እላለሁ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share