አገራችን ኢትዮጵያ እንደ አገር ከተመሰረተች ጀምሮ በቀስተ ደመና መልክ (ቀለም) የሚታወቀዉ አረንጓዴ ፣ ቢጫ እና ቀይ ቀለም የህዝብ እና የአገር መገለጫ የማንነት እና የሉዓላዊነት አሻራ እና ምልክት ነዉ፡፡
ይህ የኢትዮጵያ እና ህዝቦች ሰንደቅ ዓላማ ታሪካዊ ፣ጥንታዊ እና ሁለመናዊ ህብረ ቀለም ኢትዮጵያዊ ከመሆኑ ባሻገር ተፈጥሯዊ ፣ ኃይማኖታዊ እና ባህላዊ ይዘት እና ዕዉነት ያለዉ ነዉ ፡፡
ይህ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጥቁር ህዝብ የነፃነት እና የኩራት መለያ የሆነዉ ሰንደቅ ዓላማ ከኢትዮጵያዊነት በላይ ለአፍሪካ ጥቁር ህዝቦች የነፃነት እና የድል ተምሳሌት በመሆኑ ወንድም የአፍሪካ ህዝቦች ባንዲራ የኢትዮጵያን ሠንደቅ ዓላማ የሚጠቀሙ ስለመሆኑ ማሳያ ቤኒን፣ ጋና፣ጉኒያ…… በቂ ምሳሌ ነበር ነዉ ፡፡
ይህ የኢትዮጵያን የነፃነት እና አንድነት መገለጫ ባንዲራ ስርዓት መጥቶ በሄደ ቁጥር የድርጅት መልክት/ ዓርማ በመቀየር እና በመለዋወጥ የኢትዮጵያን ሠንደቅ ዓላማ አንይ ማለት ጤናማ ኢትዮጵያዊነት እና ህዝባዊነት አለመሆኑን ለዘመናት ከእኛ በላይ ዓለም ጠግቦታል፡፡
ከፖለቲካ ተቋማት እና ድርጅት ፅ/ቤት ዉጭ ለሚደረግ የሠንደቅ ዓላማ መኖር የጶለቲካ ድርጅት እና የመንግስት አስተዳደር በተለዋወጠ ቁጥር ይህን ያዙ ፤ ያን አዉግዙ ማለት ቢቆም ዘላቂ መተማመን እና ብሄራዊ መስተጋብር ሊኖር የሚያስችል ነዉ ፡፡
የኢትዮጵያ ህዝብ የህይወት እና የደም ዋጋ የተከፈለበትን የ ፭ ሽ ዘመናት የነፃነት እና ሉዓላዊነት ሠንደቅ ዓላማ ቢሸከም ቀርቶ ጠቅሎ ቢጎርሰዉ ማንንም ሊያስደስት እና ሊያኮራ እንጂ ሊያሳፍር አይገባዉም ፡፡
በህይወት እና ደም የተገኘን ማንነት ማክበር እና ማስከበር የኢትዮጵያዊነት ኩራት እንጂ ስጋት ሆኖ አያዉቅም፡፡ በኢትዮጵያ ላይ የራሳቸዉን ከተግባር የተጣላ ታሪክ ለማንበር በቁማቸዉ ሀዉልት የሚያሰኛቸዉ የኢትዮጵያዊነት መገለጫ የቆየ የማንነት አሻራ የሚያቅለሸልሻቸዉ የጥላቻ እና ክህደት ጅምር ሀሁ….ዛሬ አልተጀመረም ፡፡
ባንዲራ ጨርቅ ነዉ……..የቤተክረስቲያን……..የነገስታት…………እያሉ የዋረዱ፣የወረዱ ፣ የረገጡ፣ ያቃጠሉ……..ለምን ይሆን አዉድ ዓመት ባባተ ቁጥር ጣሉ የሚሉት አታንሱት የሚሉት፡፡ መቸ ነዉ እኛ አገር በምክነያት እና በዕዉነት የምንቀሳቀሰዉ ፡፡
እኛን ብቻ ተከተሉ ክፉ የጥላቻ እና የምቀኝነት ዘመቻ መጋኛ የምንላቀቀዉ መቸ ነዉ ፡፡
ለመሆኑ የአንድ አገር ብሄራዊ ሠንደቅ ዓላማ ከፖለቲካ አስተሳሰብ እና ከግል መሳሪያ አልፎ በነፃነት ዜጎች የእኛ ብለዉ አስከተቀበሉት በነፃነት የሚኖሩበት ፡፡
ዛሬ በአንድም ተቋም በክብር ወጥቶ እና ወርዶ በማይከበር ሠንደቅ ዓላማ ዜጎች በግል፣ በጋራ እና በዕምነት ተቋማት በአዉድ ዓመት ቀርቶ በዕለት ቢያከብሩት ሊያስመሰግን እና ሊያኮራ እንጂ ሊያሳስብ አይገባም፡፡
የዕምነት ተቋማት የቆሙባትን አገር እና የሚከተላቸዉን ህዝበ አማኝ የማንነት እና የነጻነት ዓርማ ከፍ ማድረግ የሚያስከብር እንጂ የሚያስነዉር አይደለም ፡፡
ስርዓተ መንግስት ሆነ ድርጂት ቀሪ ሲሆን አገር ፣ህዝብ እና ትዉልድ ዘላለማዊ ናቸዉ ለዚህም አብሮ የሚኖረዉ ከኢትዮጵያ ጋር የኢትዮጵያ ህዝብ ብሎም የአፍሪካ የነፃነት ምልክት የኢትዮጵያችን ዓርማ ( አረንጓዴ ፣ቢጫ ፤ቀይ ) ነዉ ፡፡
ኢትዮጵያዊነት ከታሪክ በመማር ከጥላቻ እና ከበታችነት ጉዳጓድ መዉጣት እንጂ በክፋት እና ምቀኝነት መነታረክ አይደለም ፡፡
አንድነት ኃይል ነዉ