1- ህውሃት አሁን የደረሰችበት ሁኔታ ለመድረስ ያላትን ጠቅላላ አቅሟን ተጠቅማለች ፡ሆኖም ጠቅላላ አቅሟን ስትጠቀም አራት ወር ሙሉ ወሎ ውስጥ የከፈለችው ኪሳራ ቤዟን ያሟጠጠ አቅሟን ያደቀቀ ነው። በዚህ አይነት ብቻዋን በመሞት እና በመግደል የምታጠፋው ህይወት በራሷ ህዝብ ላይ ማለቂያ የሌለው መጨረሻው ዋጋቢስ የሆነ አጉል እልቂት መሆኑን ልብ ሊባል ይገባል።
2- አማራ ደግሞ ህውሃት እያደረሰችበት ያለውን እልቂት እየመከተ ያለው፡ አማራ ሊኖረው ከሚችለው ሁለንተናዊ አቅም አንፃር ፡አስራ አምስት ፐርሰንቱን እንኳን መልክ አሲይዞ ሳይጠቀም ፡ሊያደርግ የሚገባውን እና የሚችለውን ያህል ሳይሞክር ነው ይህ ሁሉ ግፍ እየተፈፀመበት ያለው፡፡ጦርነቱንም በሆነ መንገድ መንግስት ያስቆመዋል ህውሃትን ይደመስስልኛል በሚል የህልም ምኞት ብቻ ዘግናኝ ፍጅት እየተፈፀመበት ይገኛል።
3- መንግስት በግልፅ አማራን በርታ ያለአንተ አሁን ህውሃትን ለመዋጋት ቁርጠኛ የሆነ ሃይል የለም መከላከያ ሊዋጋው የማይችለው የህዝባዊ ጦርነት ስለሆነ እንካ ያለኝን ብሎ ለአማራ አስፈላጊውን ትጥቅ እና ሃቅ ባለማስረከቡ፡አማራን ይበልጥ መንታ መንገድ ላይ ጥሎታል።
እነዚህ ሃቆች ማናችንም በአይናችን የምናያቸው ጥሬ ሃቆች ናቸው።
አሁን መዳኛው አንድ እና አንድ ብቻ ነው፡፡የአማራ ልጅ ሁሉንም ጉዳይህን ትተህ ጦርነቱ ብቸኛው ስራህ ሊሆን ይገባል። ንግድ ትምህርት የመንግስት ስራ ማህበራዊ ኑሮ የሚባል ነገር ትግራይ ውስጥ የለም።አማራም ይህንኑ ባስቸኳይ አድርግ፡፡ህውሃቶች ጠላታቸውን ለማጥፋት እቤቱ መጥተዋል።አማራም የመጣበትን ጠላት በሙሉ ሃይሉ ሊገጥመው ግድ ይለዋል፡፡
ይህ ጦርነት ፈፅሞ የስልጣን ጦርነት አደለም ፡፡ጦርነቱ አማራን ማጥፋት ነው።እንግዲህ ውሳኔው የአማራ ህዝብ ነው፡፡ “
–ተዋርዶ መሞት ወይም ተከብሮ መኖር።
— ባገኙት ገጥመውሃል ባገኝህው ግጠማቸው።
— መሳሪያ ቀምተዋል
— መሳሪያ ቀማ ፡
— በጅምላ ገጥመውሃል
— በጅምላ ግጠማቸው፡
— ያላቸውን ሁሉ አዝምተዋል ያለህን ሁሉ አዝምት ፡
— መሪ ፈጥረዋል ይታዘዙታል፡መሪ ፍጠር ታዘዘውም።
እንደዚህ አይነት ግልፅ ጦርነት አይቼ አላውቅም። መልሱም አማራ እጅ ላይ ነው ፡፡
ነገ ሳይሆን ዛሬ።
አበበ በለው