ከአማራ ሕዝባዊ ኃይል (ፋኖ) የተሰጠ መግለጫ!

እንደ ሀገር ኢትዮጵያ እጅግ አደገኛ ምስቅልቅል ውስጥ ትገኛለች፤ እንደ ህዝብ አማራ የእልቂት አዋጅ ታውጆበት ራሱን ከፈጽሞ ጥፋት ለማዳን በእያንዳንዷ ሰከንድ በእልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ ውስጥ ነው። በዚህ ምክንያት ወቅቱን በዋጀ የጠላትን እንቅስቃሴ በሚመጥን አኳኋን፣ ጠላትን ለመመከትና ለመደምሰስ ህዝባዊ ትግል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የአማራ ህዝባዊ ሃይልን ፈጥረን ላለፉት ሶስት ወራት በሞት ጫካ ውስጥ እየተሽሎከሎክን ህዝቡን ስናነቃ፣ ስናደራጅና ስናሰለጥን ቆይተናል። በአጭር ጊዜም ሽዎችን ማንቃት ማደራጀትና ማሰልጠን ተችሏል።

በዚህ ሁሉ ሂደት ውስጥ እያለን የሰሞኑን መንግስት የክተት ጥሪ ተከትሎ ለውጊያ ቅድመ-ዝግጅት እንዲያግዘን የመርጡለማርያም ግብርና ኮሌጅን እንደ ጊዚያዊ መሰባሰቢያ ካምፕ እንድንጠቀም ተነገረን። ከዚህም በተጨማሪ የመንግስት ሰራተኛ አባሎቻችንን ጭምር ማዝመት እንደምንችል እና ደሞዛቸው ለቤተሰብ እንደሚደርስ፣ የቡድን መሳሪያና ተተኳሽ በበቂ እንደሚቀርብልን፣ ምግብ በአንድ ትልቅ ተቋም በኩል እንደሚቀርብ… ወዘተ ተስማማን።

በኛም በኩል የመንግስትን ውሳኔ አድንቀን መላው የአማራ ሕዝባዊ ኃይል አባላት (ፋኖ) ወደ ጊዜያዊ ካምፑ እንዲከት ጥሪ አስተላለፍን፤ በሰባ ሁለት ሰአት ውስጥ አንድ ሽህ አንድ መቶ አስራ ስምንት (1118) የሰለጠነ ፋኖ ወደ ካምፕ ከተተ። ከዚህ ውስጥ ከ ሰላሳ በላይ የኮማንዶ አሰልጣኞች፣ ከአስራ አምስት በላይ ሃኪሞች፣ የመከላከያ ሰራዊት አባላትና መሪዎች የነበሩ፣ የልዩ ሃይል መሪዎችና አባላት የነበሩ የሚገኙበት ሲሆን ብዙ ሺወች ከየቀያቸው ተነቃንቀው ህዝባዊ ሃይሉን ለመቀላቀል መጠራራት ጀመሩ።

ይሁንና ሰባ ሁለት ሰአቱ በቅጡ ሳይጠናቀቅ የመንግስት የተለመደ አመል ማገርሸት ጀመረ። ምግብ ያቀርባል የተባለው ተቋም አንድ ረፋድ ላይ ደረቅ እንጀራ፣ ሽሮና በርበሬ አድርሶ ጠፋ፤ ካምፑን ለቀን እንድንሄድ እዚህም እዚያም ጫናዎች መታየት ጀመሩ፤ “ደመወዛቸው አይቋረጥም ችግር የለም ይዝመቱ” የተባሉ የመንግስት ሰራተኛ አባሎቻችን ላይ ባልተለመደ ሁኔታ ላንድ ቀን እንኳን ካምፑ ውስጥ ውለው ሳያድሩ መስሪያ ቤታቸው ደብዳቤ እንዲጽፍ ማድረግ ተጀመረ፤ ፋኖዎች ከአካባቢያቸው እንዳይንቀሳቀሱ መኪና መከልከልና ማስከልከል ተጀመረ፤ “ከሰላሳ እስከ አምሳ ሰው ብቻ ነው ማዝመት የምትችሉት ከዛ ውጭ አትችሉም” ይሉን ገቡ፤ “በመከላከያ እዝ ስር ከተው ሊያስጨርሷችሁ ነው ተመለሱና ልዩ ሃይሉንና መከላከያን ብቻ ተቀላቀላችሁ ሰልጥኑ”…ወዘተ የሚሉ የውስጥ ለውስጥ ቅስቀሳዎች ጦፉ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአባይ ቦንድ ሽያጭ በጉተምበርግ ከሸፈ፤ ድብድብ ተነሳ (Video)

ከጉዟችን ላለመናጠብ ሲባል ብቻ ችግሮችን ባላየ እያለፍን በትዕግስት ይዘን ትኩረታችንን ዋናው ጠላት ላይ ለማድረግ አቅደን ፋኖውን ለቀጣይ ግዳጅ ማዘጋጀቱ ላይ ብቻ አተኩረን ነበር። ይህ ትዕግስት ግን የረባ ውጤት ሳያመጣ የተገባልን ቃል ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ከመታጠፉ በተጨማሪ ሰኞ እኩለ ቀን የገባንበትን ካምፕ ረቡዕ እለት ለቀነው እንድንወጣ፤ ኃይላችንም እንድንበተን ግፊት መደረግ ተጀመረ። አልፎም “ሁኔታዎች እየተካረሩ ከሄዱ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደምንገባ” ‘ይመክሩን’ ገቡ።

በእኛ በኩልም መንግስት በገባው ቃል መሰረት ተገቢዉን ይፈፅማል በሚል እምነት ወደ አንድ ካምፕ የተሰባሰበ በርካታ የአማራ ፋኖ ህይወት አደጋ ውስጥ ላለመጣል እና የውስጥ ችግር ላለመፍጠር ስንል ከህዝባዊ ኃይሉ አባላት ጋር መክረን የህዝባዊ ኃይሉን ህልውናና ቀጣይ እንቅስቃሴ በማይነካ አኳኋን ፋኖው ወደ ቀየው ተመልሶ ከነ ሙሉ መዋቅሩ ትግሉን እንዲቀጥል አቅጣጫ በማስቀመጥ ከካምፕ ወጥተን በቁጭት እምባ እየታጠብን ወደየቀያችን ተመልሰናል። ፍርዱን ለአማራ ህዝብ፣ ለኢትዮጲያ ህዝብ እና ለታሪክ ትተነዋል።

በመሆኑም:-

1/ አባሎቻችን ቀጣይ ተልዕኮ እስኪሰጥ ድረስ በየመጣችሁበት ወረዳ ተመልሳችሁ ህዝብ የማንቃት እና የማደራጀት ስራችሁን እንድትቀጥሉ እናሳስባለን።

2/ የመንግስት አመራሮች ቃላችሁን ለማክበር ፈቃዱ ካላችሁ እኛም ማንኛውንም ስምሪት ለመቀበል ዝግጁ መሆናችንን በህዝብ ፊት ቃል እንገባለን።

3/ መላው የአማራ ህዝብ እና የገባንበት የህልውና አደጋ ያሳሰባችሁ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ህዝባዊ ኃይሉ ለትግል ዝግጁ መሆኑን አውቃችሁ እንድትደግፉት እና በየሚመቻችሁ አደረጃጀት ትግሉ ላይ አስተዋፅኦ እንድታደርጉ ጥሪ እናስተላልፋለን።

4/ ጥሪያችንን ባለመቀበል፤ አንድም የአማራ ጉልበት እንዳይባክን አበክረን የገለፅነውን ወርቃማ ሃሳብ በመግፋት ለሚደርሰው ታሪካዊ ኪሳራ ገዥወች ኃላፊነቱን እንደሚወስዱ እናሳውቃለን።

ተጨማሪ ያንብቡ:  አሸባሪው፣ የአማራ ቄስ ብልጽግና ነው በሚል ካህናቱን ማረዱን የደብረጸሐይ ሐሙሲት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርቲያን ካህናት ገለጹ

አማራ ሕዝባዊ ኃይል (ፋኖ)

7 Comments

  1. ከዚህ በላይ ብአዴንን አጥቦ የሚያሰጣው ነውር ከየት ይመጣል እናንተ እስኪ ጠጡ እኛ ወጣቶች ሂደን እንሙት ሲሉ አይሆንም ማለትን ምን ይሉታል? አገኘሁ ተሻገር ቢባረርም ብአዴን ታጥቦ ጭቃ ሆነ ማለት ነው?

  2. ከውጪ ሴረኞች በሚሰጥ ድጋፍ እና በውስጥ ባንዳች ተልዕኮ ፈፃሚነት አገርን ለማድከም፣ ለመበጣጠስ እና ለመገነጣጠል የሚደረግ ሻጥር በተለይ በአመራር ላይ ያሉ አካላት ተጠያቂ ሊያደርጋቸው እንደሚችል በደንብ ልብ ሊሉት ይገባል፡፡ ያለው የእሳት ወላፈን እንሱንም ሰይነካ ሊበርድ እንደማይችል ሊገነዘቡት ይገባል፡፡ ይልቅስ እንታገል የሚሉትን በአግባቡ ቢደግፉና ቢያግዙ ነገ ከእሳቱ ወላፈኑ ሊድኑም ይችሉ ይሆናል፡፡ ይታሰብበት፡፡
    ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!! ጠላቶቿው ይጥፉ!!

  3. በነመለሰ ዜናዊ ክልል በማለት ሀገሪቱ ከተሸነሸነችበት በኋላ ይመስለኛል የአማራ መሬታችን ተወሰደ ማስመለስ አለብን በማለት ፋኖ የተመሰረተ ይመስለኛል። ከዚያን ወቅት ጀምሮ ሲዋግም ነበር። በአሁን ወቅት ደግሞ ፋኖ፤ ከመክላከያ ሠራዊት፤ከልዩ ሃይል እና ከሚሊሺያ ጋር በመሆን እየተዋጋ ነው። መንግሥትም ፈቃደኛ የሆነ ሁሉ በማእከላዊ መሰልጠኛ ካምፕ ወስጥ ገብቶ በመከላከያ ሰራዊት መሠልጠን እንደሚችል ጥሪ ካደረገ ውሎ አድሮአል።ታዲይ ይህ ከላይ በመርጦ ለማርያም ኮሌጅ በራሱ ሃይል ለመሰልጠን ፋኖ ነኝ ብሎ የመጣው ክፍል ሌላ ሁለተኛ የፍኖ ክፍል ነውን? ወይንስ ምንድን ነው? እየተዋጋ ያለው ፋኖ ከሆነ ደግሞ ከሀገሪቱ መከላከያ እና ልዩ ሃይል ጋር በመጣመር እየሰለጠነ እና እየተዋጋ በመሆኑ መግለጫ ማውጣትም አያስፈልግ። በመሆኑ ከመግለጫው እንደተረዳሁት ከሰላስ በላይ የኮማንዶ አሰልጣኞች፤ ከአስራ አምስት በላይ ሃኪሞች፤የመከላከያ ሰራዊት አባላት የነበሩ እና የልዩ ሃይል አባለትን የነበሩትንም ይጨምራል ይላል።ይህ ሁሉ የሰለጠነ አና አስልጣኝ ካለ፤ለብቻችን አንሰልጥን፤መንግሥት ይክፈለን ብሎ መግለጫ ማውጣቱ ምን ይባላል ? መነግሥት ባወጣው መመሪያ መሰረት መጓዙ አይቀልምን? ይስመሰኛል መልክቱ ሌላ ይመስለኛል።

  4. መንግስት ይመግበኝ፣ ደመወዝ ይክፈለኝ የሚል ፋኖ ተብየ የሰማነው ይህን የመርጡለማሪያሙን ብቻ ይመስለኛል። የተጠቀሰውን ጥቅማጥቅም የሚሻ ሃይል ደመወዝና ስንቅ በመደበኛነት የሚያቀርበውን መከላከያ ወይም ልዩ ሃይል መስፈርቱን አሟልቶ ቢቀላቀል ሳይሻል አይቀርም።

    እነዚህን ፋኖ ብሎ መጥራትም አስፈላጊ አይደለም።

  5. Bebekule manim yihun man ethiopiawi yehone Ethiopia tiketil yemil banda woyanen ke amara kilil endiwota mefked yelebetim please ye poletica liyunet hager sitnor new lela banda mehon ayasfeligim hulum neger wodetor ginbar shikucha yikir mewonejajel yikir mekefafel yikir amara ende afar metagel yasfeligal tigilu degmo le amara bicha yemintew aydelem Ethiopia hagerachinn enafersalen bilo yw tigray ye chew mekoteriya cherk eyawulebelebe hagerachinin mewurer anfekdim woyane malet ke taliyan yebelete worari nw Ethiopian ethipiawinetin kalfelegu lemin wodelelaw Ethiopia gizat yigebalu ? Woyanen keguya yizo tigil lemashenef ayabekam so tenegnawum bihon enesu ertitrawin 1991 lay endabareru wodemekele melak alebachew or detention camp megbat torinetu eskiyalk? Tigray tashenifalech bilo Ethiopian masanes min yemilut new ?

  6. ከዚህ በኋላ ምን እስኪመጣ ይጠበቅ ፣የአህያ ባል ከጅብ አያሰጥም ፣!አሉ አባቶቻችን ሲናገሩ መንግሥትደጋግሞ ክዶናል አለቀ ከዚህ በኋላ ተስፋችን አምላካችን እግዚአብሔር እና የሚይሰበረው ማንነታችን ነዉ መንግሥት ከዚህ በላይ ፈርሷል ምንም አንጠብቅም መጀመሪያ ትግል የሚሆነዉ በዙሪያችን ተጠምጥሞ አስሮ አላራምድ ካለን የእግር ብረታችን መፈታት ነዉ ዘመኑን ሙሉ ከአሽከርነት የማይላቅ የማህይማን ስብስብ ነፃ እርምጃ በመውሰድ ከእስራታችን መፈታት ነዉ አለቀ ባገኘህበት ይህንን እንደግብር የህዝብ ሞት አለማምዶ ሲያጠፋን ሲያስጠፋን የኖረ ባንዳ የባንዳ ስብስብ ነፃ እርምጃ በመውሰድ ከእስራታችን እንፈታ ሌላው እዳዉ ገብስ ነዉ (ከህወሓት )!በላይ ጠላታችን የብልፅግናዉ መንግሥት እና ሎሌዉ ብአዴን !!!ነዉ አከተመ !!!

  7. ከዚህ በኋላ ምን እስኪመጣ ይጠበቅ ፣የአህያ ባል ከጅብ አያሰጥም ፣!አሉ አባቶቻችን ሲናገሩ መንግሥትደጋግሞ ክዶናል አለቀ ከዚህ በኋላ ተስፋችን አምላካችን እግዚአብሔር እና የሚይሰበረው ማንነታችን ነዉ መንግሥት ከዚህ በላይ ፈርሷል ምንም አንጠብቅም መጀመሪያ ትግል የሚሆነዉ በዙሪያችን ተጠምጥሞ አስሮ አላራምድ ካለን የእግር ብረታችን መፈታት ነዉ ዘመኑን ሙሉ ከአሽከርነት የማይላቅ የማህይማን ስብስብ ነፃ እርምጃ በመውሰድ ከእስራታችን መፈታት ነዉ አለቀ ባገኘህበት ይህንን እንደግብር የህዝብ ሞት አለማምዶ ሲያጠፋን ሲያስጠፋን የኖረ ባንዳ የባንዳ ስብስብ ነፃ እርምጃ በመውሰድ ከእስራታችን እንፈታ ሌላው እዳዉ ገብስ ነዉ (ከህወሓት )!በላይ ጠላታችን የብልፅግናዉ መንግሥት እና ሎሌዉ ብአዴን !!!ነዉ አከተመ !!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share