“ለአማራ ድል፣ ብአዴን መወገድ አለበት!!!! – አቻምየለህ ታምሩ

ለፋሽስት ወያኔ የውስጥ መረጃ በማቅረብ አማራን እያስጠቃ ያለው “ብአዴን” ነው!!!!!
የአብኑ የሱፍ ኢብራሒም በተወለደበት ደሴ ከተማ ውስጥ ባረፉበት ሆቴልና በሚጓዙበት መኪና ላይ ከትግራይ የመጡ ወራሪዎች ሶስት ጊዜ መድፍ ተኩሰው እንደሳቷቸው ነግሮናል። ይህ የሚያሳየው የፋሽስት ወያኔ አንበጣ ሠራዊት የአገር መከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይልና ፋኖ የሚያደርገውን ስምሪት ብቻ ሳይሆን ግለሰቦች የት ቦታ እንደሚያርፉና ምን አይነት መኪና እንደሚያሽከረክሩ ሳይቀር ያውቃሉ፤ መረጃው አላቸው ማለት ነው። ፋሽስት ወያኔ ይህን ሁሉ ሚስጥራዊ መረጃ ከተራና ከተርታ ግለሰቦች ሊያገኝ አይችልም። በኔ እምነት የፋሽስት ወያኔ ታማኝ የመረጃ ምንጮችና አስተኳሾች የአማራ ርግማኖች የሆኑት ነውረኞቹ ብአዴኖች ናቸው። ፋሽስት ወያኔን ደብረ ታቦር ድረስ እየመራ የወሰዳቸው የብአዴኑ ሹም፤ የምዕራብ ደንብያው የደኅንነት ኃላፊ መሆኑን መዘንጋት አያስፈልግም። ፋሽስት ወያኔ ከኮረም እስከ ደሴ ድረስ የግፍ ወረራ ያካሄደው በዋናነት ከእንደምዕራብ ደንብያው የደኅንነት ኃላፊ አይነት የብአዴን ሰዎች በሚያገኘው ሚስጥራዊ መረጃና ሴራ እየታገዘ ነው። ስለዚህ የፋሽስት ወያኔ አስተኳሽ የሆኑ ብአዴኖች ከጥቅም ውጭ ሆነው ጸረ ፋሽስት ወያኔ ተጋድሎው እስካሄደ ድረስ በብአዴን አዝማችነት የሚካሄደው ጸረ ፋሽስት ወያኔ ተጋድሎ ከጠላት ጋር ተሰልፎ ጠላትን ለማሸነፍ እንደመሞከር አይነት ጅልነት ነው። ባጭሩ የብአዴን የሆነው ነገር ሁሉ የኅልውና ዘመቻው በድል እስኪጠናቀቅ ድረስ ታግዶ ጸረ ፋሽስት ወያኔ ተጋድሎው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጆ በመከላከያው፣ በልዩ ኃይሉ፣ በሚሊሻውና በፋኖው የተቀናጀ ስምሪት ይመራ።
ተጨማሪ ያንብቡ:  የአማራና አፋር ተጎራባች ወንድማማቾች የሰላም መድረክ በቀወት ወረዳ ኩሬ በረት ቀበሌ በመካሄድ ላይ ነው!

4 Comments

  1. አቻምየለህ፦ ትክክል ብለሀል፡፡ የብአደኖች( የአማራ ብልጽግናወች) ዘወር መደረጋቸው ብቻውን መፍትሄ አያመጣም፡፤ እስከወረዳ ደረጃ በሀለፊነት ያሉት ብአደኖች በሙሉ ተለቅመው እስር ቤት መግባት አለባቸው፡፤ በአማራ ላይ ስፍር ቁትር የሌለው ክህደቶችን እየሰሩ አማራውን ለዚህ ውርደትና ምስቅልቅል አድርሰውታል፡፤ ታዲያ እስሩ መጀመር ያለበት ከላይ ነው፡፤ ከደመቀ መኮንን ጀምሮ ገዱ አንዳርጋቸውን፣ አገኘሁ ተሻገርን፣ ተመስገን ጥሩነህንና ……ወዘተ እያለ ወደታች መውረድ አለበት፡፤ ይህ ጊዜያዊ መፍትሄን ለጊዜው(ለጦርነቱ) ያመጣል እንጅ አማራ ተገቢውን ቦታ በአገሪቱ ፖለቲካና እኮኖሚ ስሪትና አመራር ውስጥ እንድያገኝ ለማድረግ አሁን አማራውን ከገባበት አሮንቃ ለማውጣት እንደብቸኛ መፍትሄ የተጀመረው የአማራ ህዝባዊ ሀይል ንቅናቄ በሂደቱ የሚወልዳቸው ጀግኖችና ምሁሮች አመራሩን መያዝ የግድ ይላል፡፡

  2. አምበሳው ቆፍጣናዉ አቻምየለህ ታምሩ ኢትዮጵያና አማራው ነጻ ሲወጡ በእርግጠኝነት ወገን በላይ ዘለቀ ጎን በህይወት እያለህ ሀዉልት ያቆምልሀል ብዬ አምናለሁ። ዉሀ ልክ ነህ።

  3. አሁን በዚህ በጭንቅ ሰዓት ስለ አማራ አመራሮች መወገድ ታወራለህ? ይገርማል። የሚናፈሰው ወሬ ኮምቦልቻና ደሴ በወያኔ እጅ እንደተያዙ ነው። አልፎ ተርፎም የወያኔው ወታደራዊ መሪ ጻድቃን ለድርድር እንዲቀመጡ ለቀረበለት ጥያቄ መልስ ሲሰጥ “ጦርነቱ አልቋል። ማንንም ከምንም ጋር የሚያደራድር ነገር የለም” በማለት ነበር የመለሰው። እኔ ጭራሽ የማይገባኝ ሃገርን የረድ እየመሰላቸው በየድህረ ገጽ ትኩረት የሚሰጠውን ነገር ትተው የወታደሩ አመራር መቀየር አለበት፤ የክልል መሪዎች ይውረድ፤ እዚህ ጋ ይህ ይሁን እዚያ ጋ ያ ይፍረስ የሚሉት የቀኑንና የጊዜውን መወሳሰብ የማያዪ የወሬ አናፋሾች ናቸው። ግን ለዚህ ሁሉ ጥያቄ ጊዜ ይኖረዋል። አሁን ግን በጭራሽ ጊዜው አይደለም። መንግስት በዚህም በዚያም ኮምቦልቻና ደሴ አልተያዙም ይበል እንጂ አመላካቹ ነገር የሚናገረው ሌላ ነው። ከላይ በአየር ወቀጥናቸው፡ ከሥር ሰራዊቱና ሚሊሻው ቀጠቀጣቸው እየተባልን በእርግጥ እነዚህ ስፍራዎች ተይዘው ከሆነ የድንቁርናችን ጣራ ላይ መድረስ ያሳያል። ወያኔ ከመቀሌ ተንቀሳቅሶ ወሎ ከገባ አዲስ አበባ እንደገባ ይቆጠራል። የሚያሰለቸኝ የመንግስትም ሆነ የአማራው ክልል ጡሩንባ መግለጫው ነው። ከህጻናት እስከ ሽማግሌ፤ ከእናቶች እስከ ነፍሰ ጡር አሰልፎ ወያኔ እያሉ ማቅራራት ምን ይባላል። ይህ የሚያሳየው ቁርጠኝነታቸውን ነው። አረገዘች፤ ህጻን ሆን ሁሉም ለዝርፊያና ለግድያ እየተዋደቁ ነው። ትክክል ነው በዚህ ፍትጊያ፤ ከወያኔ ጋር በሚደረገው ትንቅንቅ የሚወለድ ጀግኖች ይኖራሉ። የተወለድም ሞልተዋል። ይህ በሂደት የሚሆን የባቡር ጉዞ ነው። አንድ ሲወርድ ሌላው ይሳፈራል። የለውጡና የመለዋወጡ ሂደት ግብታዊ የሚያደርገው ጊዜና ሁኔታዎች ናቸው። ግን ወያኔን ማጥፋት ተስኖን እንደገና የሃገር መሪ ከሆኑ ወዮ ለሃገሪቱ ወዪ ለህዝባችን። በቃኝ!
    አሁን የአማራ ህዝብ ለራሱ ህልውና ትንቅንቅ ላይ ነው። የአመራሩ የጅምላ ለውጥ መከራ እንጂ ወታደራዊ ድል አያስገኝም። ሆን ተብሎ አመራሩ ከጦርነቱ በፊት የተመነጠረው ለዚሁ አላማ ነበር። ነጋ ጠባ ክተት እያስባለ የሚያስጮኸው የአማራው አመራርና ፌዴራል መንግስቱ የወያኔን ወረራ መቀልበስ ካልቻለ ሃገራችን እንደገና ለሰቆቃ ይዳርጋታል።

  4. ተስፋ ቀደም ብሎ ስለተገነዘበው ሊደርስ የሚችለውን አመላከተን ታዲያ የሆነው ምን ነበር? የብአዴን ሹማምንት ገንዘብ በኬሻ መከፋፈል ፤ጄነራል ተፈራ ማሞን ተከታትሎ መጠቆም ነበር፡፡ ብአዴን እዚህ ጦርነት ላይ 5ኛ ረድፍ ላይ የተሰለፈ የጠላት ሃይል እንጅ የክልሉ መሪ አይመስልም ነበር አልነበረምም፡፡ አሁንም እንዳየኸው ነው ትግሉን በድል ለመወጣት ብአዴንን ከማስወገድ ውጭ ምርጫ የለም፡፡ አቻምየለህ ቀደም ብሎ ተረድቶት ስለነበር ጥቆማ ሰጠ፡፡ የሱዳኑ መሪ የፈጥኖ ደራሽ ሃይሉን አጥፍተው ሊበሉት ሲሉ ቀድሞ በላቸው የአማራ ፋኖ ልዩ ሃይል ሚሊሽያም እጣው መበላት ስለሆን አሻፈረኝ ከማለት ውጭ ምርጫ አይኖረውም፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share