“አረመኔውና ጨፍጫፊው ትህነግ በሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ ጭና ተክለኃይማኖት ቀበሌ ከ100 በላይ ንፁሃንን ጨፍጭፏል” አቶ ግዛቸው ሙሉነህ September 7, 2021 ሰብአዊ መብት Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ያስተላለፉት መልዕክት። “የጀግኖቻችንን የተቀናጄ ጥቃት ሲቀምስ፣ በየጫካው እየተፋለሙት ያሉትን ጀግኖችን መቋቋም ያልቻለው ወራሪ በየቤታቸው የነበሩ አዛውንቶችን፣ ህፃናትንና እናቶችን በያሉበት መንደርና ሰፈር በመግባት፣ ቀሳውስትን ቤተ ክርስትያን ውስጥ ገብቶ የፍጥኝ በማሰር ከ100 በላይ ንጹሃንን ጨፍጭፏል። የትግራይ ወራሪ ቡድን ቀደም ሲል በሰሜን ወሎ፣ በአፋር ክልል የፈፀመውን አይነት ዘግናኝ ጭፍጨፋ በሰሜን ጎንደር በዳባት ወረዳ በጭና ተክለኃይማኖት ቀበሌ በድጋሜ ፈፅሟል። ይህ ሰይጣናዊ ቡድን ከወረራቸው አካባቢዎች በአፋጣኝ ግብዓተ መሬቱ እስካልተፈፀመ ድረስ ሌሎች ጭፍጨፋዎችን እንደሚፈፅም ግልፅ ነው። በጥላቻ የናወዘውና ጭፈጨፋን የዕለት ተዕልት ተግባሩ ካደረገው የትግራይ ወራሪ አድማስ የነካ በደል፣ ሰቆቃና የግፍ ፅዋ ሕዝባችንን ለመታደገ ፍጥነታችንን ጨምረን ማርሻችንን ቀይረን ከያለበት ግብዓተ መሬረቱን በመፈፀም ሕዝባችን ልንታደግ ይገባል። ሚዲያዎቻችንም ይሄንን እውነት ዓለም እንዲያውቀውና ከወራሪውና ጨፍጫፊው ጋር በምናደርገው ትግል አብረውን እንዲቆሙና ድርጊቱንም እንዲያወግዙት በፍጥነት መዘገብና ቦታው ድረስ በመሄድም ሁኔታውን ማስረዳት ይገባናል። በንፁሃን ወገኖቻችን ላይ የደረሰው አሰቃቂ ጭፍጨፋ የትግራይን ወራሪ ቡድን ግብዓተ መሬቱን በማፋጠንና ለሕዝባችን ዳግም ስጋት እንዳይሆን በማድረግ ደማቸውን እንደምንመልስ ጥርጥር የለውም። የትግራይን ወራሪ ኃይል ከየገባበት እየመታን ባለንበት ወቅት የቤተሰብና የወገንን ሀዘን የምንጠግነው በትግራይ ወራሪ ኃይል መቃብር ላይ ይሆናል!!!! አሚኮ Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email Leave a Reply Cancel replyYour email address will not be published. Δ Previous Story ማሩኝ! – በላይነህ አባተ Next Story ኢትዮጵያ ዚምባብዌን ባለቀ ሰአት በተገኘ ፍጹም ቅጣት ምት1 ለ0 አሸነፈች