July 15, 2021
3 mins read

እምቢ በል! (በላይነህ አባተ)

ለሰላሳ ዓመታት ያየኸው ሰቆቃ፣
እስከ ዘላለሙ ዳግም እንዳይመጣ፣
እንደ ድር አብረህ አምቢ በል አማራ!

የፈጠሙብህ ግፍ ቢሰፈር ቢቆጠር፣
እንኳን ቆሞ ኻጅን ሙትን ያሸፍታል፡፡

መታገስ ማባበል ላንተ ያተረፈው፣
አገር አልባ መሆን አንገት መታረድ ነው፡፡

እንደ ቅድመ አያትህ እንደ ዱር አርበኛው፣
ፋኖ ሁን አማራ ሸልል ኧረ ጎራው!

ቀረርቶ ፉከራን ቁርስ ምሳ አድርገው፣
የጀግና መፍለቂያ ባህር ውቂያኖስ ነው!

የምትኖር ተአገር ውስጥ ተውጪም ተሰደህ፣
ተባዕድ ተሻርከው ዘርህን ሲያጠፉህ፣
ልክ እንደ አያቶችህ ዋሽንት አንቆርቁረህ፣
እንደ አምስቱ ዘመን ፋኖ በል ፎክረህ፡፡

ወገንህ ሲታረድ አድፍጠህ የተኛህ፣
ሆድህን እንደ ኬሻ በእህል እየሞላህ፣
እንኳን ትውልድ ታሪክ እግዜርም አይምርህ፡፡

ወራሪ አንበርክኮ ድንበር በጠበቀ፣
አገርን መስርቶ ኑሩበት ስላለ፣
ባጎረሳቸው እጅ አንገቱ ታረደ፣
አማራ በባትሪ እየተፈለገ፡፡

መነኮሰ ሞተን ተራስህ ላይ ደፍተህ፣
ምእመናን ሲሰው ታርጁ ጋር ቆመህ፣
አትግደል ለማለት ሥጋ እንቅ ታረገህ፣
የጨበጥከው መስቀል እሳት ሆኖ ይፍጅህ፡፡

ዶክተር ፕሮፌሰር ምሁር ሊቅ ነኝ እያልክ፣
በጭራቅ ሲታረድ በመደዳ ሕዝብህ፣
የአማራን ዘር ፍጅት ሙልጭ አርገህ ክደህ፣
የእናቴ መቀነት አደናቅፎኝ እያልክ፣
ድምጥህን አጥፍተህ ቁርጥ መዛቅ የቀጠልክ፣
ተላንቃህ ተጣብቆ እረፍት እንቅልፍ ይንሳህ፡፡

ተአምስቱ ዘመን ጅብ ተሮም የከረፋ፣
ተቱርክ ተላላኪ ተግራኝ የከፋ፣
በባትሪ ፈልግ ዘርህን የሚያጠፋ፣
ጭራቅ መጥቶብሃል ልብ በል አማራ፣
በአገር በውጩ ዓለም ፋኖ ተሰማራ!

በጉርሻ አትንሸንገል እንደ ውሻ ባንዳ፣
አርበኛ ፋኖ ሁን ተዳር ዳር አማራ!

ሺህ አመት ላትኖር ነገ አፈር ልትሆን፣
ለሆድህ ለከርስህ አትሺጥ ክብርህን፣
ሱሪህን ከፍ አርገህ አጥብቅ ቀበቶህን፣
እንደ ቅደም አያትህ አማራ ፋኖ ሁን፡፡

ተዚህ ሁሉ ችግር ትዕግስት በኋላ1
ፍርድ ባንተ የለም ምድር ብትፈነዳ፣
ክንድህን አንስተህ እምቢ በል አማራ!

በላይነህ አባተ (Abatebelai@ yahoo.co

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop

Don't Miss

Ejeta

እጀታ! – በላይነህ አባተ

በሰዶም ኃጥያት ተጠምቀህ በይሁዳ እጆች ተጣመህ፣ ግንድ ቅርንጫፍ በመክዳት ተምሳር