“የትግራይ ሕዝብ፤ ሕዝብን እንደ ሕዝብ ጠላት አድርጎ ፈርጆ አያውቅም” ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል

debre

“የትግራይን መሬትን ወረው የያዙ ኃይሎች በአስቸኳይ ይውጡ ካልሆነ ግን ባለፉት ስምንት ወራት እንዳደረግነው ሁሉ ታግለን መብታችንን እናስከብራለን” ሲሉ የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረሚካኤል ተናገሩ።

“የትግራይ ሕዝብ፤ ሕዝብን እንደ ሕዝብ ጠላት አድርጎ ፈርጆ አያውቅም” ያሉት ዶ/ር ደብረጽዮን “የትግራይ ሕዝብ ትላንት የአማራ ጠላት አልነበረም፣ ዛሬም የአማራ ጠላት አይደለም ነገም የአማራ ሕዝብ ጠላት አይሆንም” ብለዋል።

በተያያዘም የክልሉ መንግሥት ባወጣው መግለጫ፤ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የትግራይ ተወላጆች በግፍ እየተገደሉ፣ እየታሰሩ፣ ከሥራቸውም እየተባረሩ ንብረታቸውም እየተዘረፈ ነው ሲል ከሷል።

(የአዲስ አበባውን ዘጋቢያችንን ኬኔዲ አባተ፣ የመቀሌው ዘጋቢያችን ሙሉጌታ አጽብሐና የባህርዷሯ ዘጋቢያችን አስቴር ምስጋናውን ያጠናቀሩትን ሁሉንም ያካተተ ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

ተጨማሪ ያንብቡ:  የኢትዮጵያ ልክ ከግቢ እስከ ሀገር (የአብይ ቪደኦ)

3 Comments

  1. ቪኦኤ አዳነች ፍስሀዬና ሄኖክ ሰማ እግዚአብሄር አሁንም በርትተው አገር እያፈረሱ ነው ማለት ነው? ለምን ትግሬዎች አዲስ አበባ በየጭፈራ ቤት የሚያቃጥሉትን የኢትዮጵያ ባንዲራ አትመዘግቡም? ለምን የእባብ ስራ ትሰራላችሁ? የጠ/ሚኒስትሩ አማካሪ ትግሬ የጤና ጥበቃ ሚኒስተር ትግሬ ከዚህ በላይ ምን እናድርጋችሁ ተገንጠሉና የምትሆኑትን ሁኑ አትምጡብን።

  2. ይህ ሰው የዛ እባብ ሰው አብረሀ ደስታ አጎት ነው ማለት ነው? በግብርም በመልክም ተመሳሳይ ናቸው።

  3. የሃበሻ ፓለቲካ የመነካከስ ፓለቲካ ነው የምለው ለዚህ ነው። የትግራይ ህዝብ አማራን አይጠላም። ወያኔ እያለ የትግራይ ህዝብ በራሱ አስቦ መኖር አይቻለውም። ለመጥላትም ለመውደድም ምርጫ የለውም። እኛ የሚበጅህን እናውቅልሃለን እየተባለ ያላመነበትን ነገር በግድ በወያኔ ሲጋት እንሆ 50 ዓመት እየተጠጋ ነው። ይህ እጅ በደም የተነከረ የወያኔ ቁንጮ የሚናገረው ሁሉ የሚጣረስ፤ ከሰላም ይልቅ ጦርነትን የሚመርጥ፤ ያው በለመደው መንገድ አሁንም ተነሱ አማራ መጣባችሁ፤ መሬታችሁን ተቀማችሁ፤ ኤርትራ ልትወርህ ነው በማለት ወንድምና እህት እንዲላተሙ የሚያደርግ ልብ አልባ ፍጡር ነው። ችግሩ ወያኔ እንጂ የትግራይ ህዝብ መቼ ፋታ አግኝቶ ማሰብ ይፈቀድለታል? ከዚህም አልፎ በሌሎች የሃገሪቱ ክፍል የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ግፍ ተፈጸመባቸው፤ ታሰሩ፤ ከሥራ ተባረሩ ብሎ ማላዘን በ 27 ዓመት ወያኔ በሃገሪቱ ውስጥ የፈጸመውን የሰቆቃ ጊዜ አለማሰብ ነው። አዲስ አበባ ላይ ተቀምጠው የሃገሪቱን ባንዲራ አቃጥለው የወያኔን ባንዲራ ያውለበለቡ ወደ ትግራይ ቢላኩና ከወያኔ ጎን ሆነው ቢፋለሙ መልካም ነበር። ግን ይህን የሚያደርጉት እየገደሉና እያታለሉ ለዘመናት በሰበሰቡት የግፍ ገንዘብ ከተማ ላይ ተቀምጠው ውስኪ እየተጎነጩ መሆኑ የከተማ አውደልዳዪች ያረጋቸዋል። በመሰረቱ በኢትዮጵያ የዘር ፓለቲካ ተሰልፎ የሚሞትና የሚገል እኩይ ፍጡር ነው። ሰው መመዘን የነበረበት በሰውነቱና በባህሪው ነው። ያ ግን ከቀረ ቆይተናል። የዚህ ሁሉ ግፍ ፈጣሪ ደግሞ የወያኔ የክልል ፓለቲካ ነው።
    ደ/ጽዪን ካለፈው የማይማር፤ አሁንም አዛውንቶችን፤ ህጻናትን፤ ሴቶችን ለጦርነት የሚማገድ የፓለቲካ ሾተል ነው። ባለፉት 8 ወራት እንዳደረግነው ሁሉ አሁንም እንደቁሳቸዋለን። ግን ይታየው ይሆን ይህ ሁሉ የመከራ በረዶ በምድሪቱ ላይ ሲወርድ በአየር ንበረት ላይ፤ በህዝብ ላይ፤ በላዕላይና በታህታት የትግራይ የኢኮኖሚ አውታር ላይ የሚያደርሰው ጉዳት? ሰው ያለ ጦርነት ልዪነቶችን መፍታት እንዴት አይሞክርም። በዚህም በለው በዚያም በለው መቼ ነው የሚያቆመው?
    ወያኔና ደጋፊዎቻቸው ግን ጅሎች ናቸው። የተወረረብንን መሬት ካስመለስን በህዋላ ይላሉ። አሁን ማን ይሙት ተወሰደ የሚሉትን መሬት ሁሉ እንካንችሁ ቢባሉ ወያኔ ጦርነት ያቆማል ብሎ ሰው ያምናሉ? የማይሆን ነገር ለሚስትህ አትንገር ይላሉ። ለወያኔ መኖር ህዝብን ከህዝብ ጋር ማተራመስ ዋናው ምሰሶ ነው። ያለ ጦርነት ነጋሪት ወያኔ በሰላም መኖርን አያውቃትም። የእብድ ገላጋዪቹ አሜሪካና የአውሮፓ ህብረት ለጥቁሩ ህዝብ ምንም አይገዳቸውም። መስሎን እንጂ ያለፈ ታሪካቸውና የአሁን ተግባራቸው የሚያሳየው ይህኑ ነው። ትላንት ሁለቱ ሃያላን መንግስታት (አሜሪካና ራሽያ) በእይታ ካምፕ ከፋፍለው ሲያጫርሱን አይተናል። አሁን ደግሞ ቻይናም፤ ቱርክም፤ ኢራንም ሌሎችም ታክለውበታል። ድሮስ ቢሆን እሳት የሚያቀብለን መቼ አጣን። የፈረሰ ድልድይ እንደንጠግን አይዞአችሁ የሚለን እንጂ። ተምሬአለሁ የሚል ሰው እንዴት ይህን ማየት አይቻለውም? እጅግ ያሳዝናል። አሜሪካኖች በላቢ ክፍያ የሰከሩ፤ ባላመኑበት ነገር ጡርንባ የሚነፉ፤ እኛ ብቻ ቆመናል የሚሉ፤ በሃገራቸውም ሆን ከሃገር ውጭ ለጥቁር ህዝብ የማያስቡ ለመሆናቸው የየጊዜው ትንኮሳና ግድያው ያመላክታል። የዶ/ር አብይ መንግስት አሜሪካን ደስ አሰኛለሁ ብሎ ነገሮችን ያለ ልቡ መቀየሩ ለማንም አይጠቅምም። ሥራቸው ዛሬም ነገም ሃገር ማፈራረስ ነው። የወያኔን ጥሩንባ የሚነፉትም ኢትዮጵያን ለመናድ ነው። በይፋ የሚናገሩትና ከሥር ሥር የሚሰሩት ክፋት ጥልቅ ነው። ብዙ ማለት ይቻላል። ይህ ግን ስፍራው አይደለም። የወያኔው ቁንጮ ድንፋታ ግን እጅግ ያሳዝናል። ታዲያ ጦርነትን እየጫሩና ህዝብ እያፈናቀሉ እንዴት ነው እርሻ የሚታረሰው? እንዴት ነው የትግራይ ህዝብ ጽሞና የሚያገኘው? ያው እንደ ቀልደኞቹ የፓለቲካ አክቲቪስቶች “ጾመ ትግራይ” እንዳሉን አይነት። የተራበና በችግር ውስጥ ያለን ህዝብ ሱባኤ እንዲገባ መጋበዝ። የሚበላው አጥቶ ሲገኝ ቀምሶ ሲያጣ ባዶ ሆድን የሚያድርን ህዝብ ባህር ማዶ ተቀምጠን ጾም የምናውጅ እብዶች። የሃበሻው ፓለቲካ ሰከን ብሎ ዘርና ቋንቋውን ወደ ኋላ በመተው ማሰብ እስካልቻለ ድረስ ሊመጣ ያለው የጨለማ ጊዜ አሁን ከምናየው የባሰ ይሆናል። ዋ በህዋላ ተራፊም አትራፊም አይኖርም። የሰው መኖር የሚለካው እድሜ ቆጠራ ከሆነ የሃበሻው ህይወት እኮ ያፍታ ነው። ዛሬ ታይቶ ነገ የለም። አይበቃም ይህ እብደታችን? በቃኝ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share