የትግራይ ህዝብ ነጻ አዉጭ ድርጅት ( ት.ህ.ነ.ድ) የካቲት ወር 1968 ዓ.ም. ያወጣዉን የትግል መመሪያ ትግራይን ነጻ ማዉጣት እና የግዛት አስተዳደር ጥያቄ ዛሬ ከ45 ዓመት በኋላ እንደ አዲስ ወይም ድንገተኛ ጉዳይ ማድረግ ስህተትም ማዘናጋትም ነዉ ፡፡
ይኸዉም ት.ህ.ነ.ድ በትግል መድበል (manifesto) ስለ ትግራይ ግዛት እና የመደብ ጠላቶች የሚላቸዉን በገለፀበት እና ይህንም ወደ ስልጣን መንበር ከወጣበት አስከአሁን ምን ዓይነት ማስተካከያ ባላደረገበት ሰሞኑን ወደ ከገጠር ቀበሌ ወደ መቀሌ በገባ ማግስት የትጥቅ ትግሉን በማጠናከር የግዛት ማስፋፋት ጥረቱን እንደሚገፋበት መዛቱን ማስተጋባት ጊዜ እና ኃይል ማባከን ነዉ ፡፡
እንዲያዉም አሁን ላይ ስለሚዛት ወረራ መገንዘብም ሆነ መረባረብ የነበረብን ይህ አገር የማፍረስ እና ሉዓላዊነት የመግሰስ ሴራ ከተመከረበት 1968 ዓ.ም. ማግስት እንደነበር እና ይህም በዘመኑ ለተገነዘቡ በሳል ኢትዮጵያዉያን አማካኝነት ከዚያ አስከ ዛሬ ብዙ ዋጋ እንዲከፈል ተደርጓል፡፡
ኢትዮጵያዉያን ከዚያ አስከዛሬ ያልከፈሉት ዋጋ የለም ፤ዛሬም ንቁ ፤ዕወቁ ፤ታጠቁ የሚባሉት የነዚያ በጎ ያገር ባለዉለታ ልጆች ናቸዉ ፡፡
ለዚህም ነበር ፤ነዉ ኢትዮጵያን የሚሉ ኢትዮጵያዉያን በብሄር እና ኃይማኖት ማለትም በጨቋኝ ብሄር/ማህበረሰብ እና ዕምነት ወይም ኃይማኖታዊ አቋም ሽፋን ያልሆነ ኢሰባዊ እና ኢተፈተፈጥሯዊ ግፍ ከ ፪ (ሁለት) አስርተ ዓመታት በላይ የተፈፀመ ፣እየተፈፀመ እና እየተዛተ ያለዉ ፡፡
ይህ ላለመቀጠል ወይም ባለበት ቆሞ ተጠያቂ ባለቤት እንዲኖረዉ ለማድረግ አሁንም ህብረት ፣አንድነት እና ዝግጅት አያስፈልግም ማለት ሳይሆን ከመሰረታዊ የታሪክ ዳራ መነሳት እና የኋላ ማንነትን አለመርሳት ግድ መሆን አለበት ፡፡
ይህም ካለፈ መከራ እና ስቃይ በተጨማሪ ቀሪ እና የማይገባ ዋጋ ላለመክፈል ከመከራ መማር እና መመርመር ግን የዞትር የተዚህ ትዉልድ ጉዳይ ሊሆን ይገባል ፡፡
ራስን አለመከላከል ተያይዞ መጥፋት ከዚህ ትዉልድ እና ዓለም አልፎ መጭዉን ትዉልድ እና ዓለም ይዞ የሚጠፋ መሆኑን መዘንጋት የለበትም ፡፡
የዚያን ዘመን ት.ህ.ነ.ድ እና የዛሬዉ ህ.ወ.ሀ.ት. የትግል መመሪያ የመሬት ግዛትን በሚመለከት በመቅድም ላይ እንደሚያትተዉ በምእራብ ትግራይ ወልቃይት እና ጠለምት ….ይላል፡፡
የህብረተሰቡ ወደ ኋላ መቅረት እና ዕረፍት ማጣት (ለ) “ጨቋኟ አማራ ” የኢኮኖሚ ብዝበዛ እና የፖለቲካ ጭቆና ማድረጓን…….ይነግረናል ፡፡
ወረድ ሲል የነጻነት ትግል “ዓለማማ እና ሥራዉ (ሀ) ” የትግራይ ህዝብ ብሄራዊ ትግል ፀረ ዓማራ ፣ ኢምፔራሊዝም …… ነዉ ይላል ፡፡
ለዚህ ነዉ አዲስ ነገር ወይም የተለየ ነገር ባለመኖሩ ዛሬ ሂሳብ እንዝጋ ከዓማራ እና ከአስመራ ጋር……ወዘተ የቋንቋ ለዉጥ ካልሆነ በቀር “ሆድ ያበዉን ጌሾ ያወጠዋል ”እንዲሉ እንጅ የዓማራ ክልል ካልሆነ በቀር ኤርትራ እና መንግስቷ ድሮም ስለሚያዉቋቸዉ ከጠላት ዛቻ አገራቸዉን ለመከላከል ዝግጅታቸዉን ያሳረጉት ህ.ወ.ሀ.ት. በተፈጠረ ማግስት እንደሆነ ከታሪክም እና ከሁነትም መገመት እና መረዳት ይቻላል ፡፡
በእኛ በኢትዮጵያ በተለይም በዓማራ ማህበረሰብ ግን እንኳን የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ( ጎንደር እና ወሎን…) ለማስከበር ሰርገኛ መጣ በርበሬ ከማለት በፊት ት.ህ.ነ.ግ. “ጨቋኗ ዓማራ በዝባዥ እና ጨቋኝ” ሲል የየትኛዉን የትግራይ ሀብት እና ንብረት ነበር…..ብሎ የጠየቀ አለመኖር በራሱ አስካሁንም የሚያስተዛዝብ እና አሁንም ይህን እንዲተፉ አለማድረግ በራሱ ክልሉን ብቻ አይደለም መላ ኢትዮጵያን ለመከላከል እና ለማዳን የሚደረገዉን ትግል መራር እና ዉስብስብ ያደርገዋል፡፡
ሌላዉ የግዛት አስተዳደር በምዕራብ ወልቃይት እና ጠለምት በጊዜዉም ሆነ አሁን የትግራይ ክ/ሀገር መሬት አካል አለመሆኑን እነርሱ ራሳቸዉ በመመሪያቸዉ በዘወርዋራ ዓምነዉ እያለ በእኛ በኩል የወልቃይት…. ጉዳይ የአማራ ጉዳይ ብቻ አድርጎ ማሰብ የኢትዮጵያን እና ህዝቧን ሉዓላዊ ግዛት እና አንድነት ነጥሎ ከማየት የሚለይ አይመስለኝም ፡፡
የሀረር ጉዳይ የኢትዮጵያ በመሆኑ በሶማሊያ ወረራ ….ኢትዮጵያዉያን የህይወት እና የደም ዋጋ ከፍለዉ ሀረር ላይ ህያዉ ምስክር ናቸዉ ፡፡
አደዋ ላይ ጀግኖች ቅድመ አያቶቻችን ብቻ ሳይሆኑ ዕምነታቸዉ እና የጫኑት ፈረስ ሳይቀር በትግል በዛ ከፍለዉ የዛሬዋን አገር አቆይተዉናል ፡፡
በኢትዮ አርትራ ጦርነት የአንበሳዉን ደርሻ የነበረዉ ኢትዮጵያዊ እንጅ የብሄር እና የአካባቢ ህዝብ አልነበረም እኮ ለምን ይሆን የጥፋት ኃይል ያዙኝ ልቀቁኝ ባለ ቁጥር ዛሬ ዐማራ ተነስ ማለት ፡፡
የኢትዮጵያ ጉዳይ በልዩነት በመከራ እና በጭንቅ ጊዜ ለጀግኖች እና አይበገሬዎች ድረሱ ማለት ድሮም የነበር እና ያለ ዓለም የሚመሰክረዉ ቢሆንም ሲጨልም እና መከራ ሲያብት ድረሱልን ሲነጋ ጠላት ከማድረግ ርቀን በጎ ለሚሰሩት ዕዉቅና እና ዋጋ እንስጥ፡፡
ይህን ኢትዮጵያን ከጥፋት ለመታደግ በግንባር ቀደም ዕግሩን ለጠጠር ፤ደረቱን ለጦር ላለ ማህበረሰብ ፤ክፍል እና ኃይል ትናንት ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም. ከተለኮሰዉ የጥፋት ዕሳት ኢትዮጵያን አሁን ካለችበት እንድትገኝ ለማድረጉ አሁንም ዕዉቅና እና ምስጋና ሊቸር ይገባል ፡፡ አሁንም ኩሉም ወገን ማለት ከኢትዮጵያ እና ከትግራይ የምንሰማዉ የኢትዮጵያን ጉዳይ የአንድ አካባቢ( ዓማራ ክልል) እና ማህበረሰብ ( ዓማራ) እንዲሁም ወልቃይት፣ጠለምት፣ ራያ…ከማለት ይልቅ ጉዳዩ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት የማስቀጠል እንዲሁም በሰፈር፣በወረዳ….ከማቅለል ጎንደር እና ወሎ የኢትዮጵያ የግዛት አስተዳደር አካሎች መሆናቸዉን ለጠላት እና ወዳጅ በግልፅ እና አጭር መልዕክት ማርዳት እና መስረዳት ያስፈልጋል፡፡
ዞትር“ ሠርገኛ መጣ በርበሬ ቅንጠሳ” የዚህችን አገር እና ህዝብ ወደር የለሽ ዋጋ እያስከፈለ በመሆኑ “ሰሞነኛ አዘነጎችን” ከመቸዉም በላይ አንመን ፤ገለል እንበል ፡፡
የትኛዉም አገር እና ህዝብ ቋሚ ወዳጅም ሆነ ጠላት የለዉም ፤እንዲያዉም ጊዜ እያየ ወዳጅ ከሚመስል ጠላት እንጠበቅ ፡፡
ለዚህ ማስረጃ ጠላት ዛሬ የሚመካባት አሜሪካ በትግል መመሪያዉ ላይ ፀረ ትግራይ ተደርጋ ፀረ-ኢምፔራሊስት ትግል ሲያደርግ ነበር ፡፡ ኋላ ግን ህ.ወ.ሃ.ት. በትግል ዘመኑ ላካሄዳቸዉ ኢሰባዊ እና ሽብር ተግባራት ሲከሰስ እንደዛሬዉ ህ.ወ.ሀ.ት.ን የታደጋቸዉ አሜሪካ ናት ፡፡
ዉሻ በበላበት ይሉሀል ይኸዉ ነዉ ፡፡
እናም ራስን ያዳነ ዓለምን ያድናል እና ዞትር ዝግጁ መሆን ጠላት ጦር በሰበቀ ፤ ዘገር በነቀነቀ ቁጥር በማሳለስ እና በማድበስበስ ሳይሆን ለራስ እና ላገር ከሚኖር ክብር እና ፍቅር መሆኑን ሊታወቅ ይገባል፡፡
የምናምን እና የመንደር (የአንድ አካባቢ ) ጉዳይ ከማለት እና የኢትዮጵያዉያንን የህይወት መስዋዕትነት ከማሳነስ ወጥተን የኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዉን በሚል ከፍ ባለ አንድነት እና ህብረት የሁሉም ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵ ዘብ የመቆም ጉዳይ ነዉ ፡፡
ኢትዮጵያ ባነሰች ቁጥር ከፍ የሚል የሚመስለዉ የስልጣን እና የከንቱ ዉዳሴ ደዌ የተጠናወተዉ ብቻ እንደሆነም ደጋግመን ልናጠይቅ ይገባል ፡፡
“የሳሎን ክፍል ሲቃጠል መኝታ ክፍል ገብቶ ከሚደበቅ ምንም አንጠበቅ ” ፡፡
“ዞትር ዝግጅት መደረግ ያለበት ጠላት ስላለ ሳይሆን ፤ወዳጅ እና ጠላት ላለመሆን ነዉ ”
አንድነት ኃይል ነዉ
ማላጂ