/

“የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች” አማራ ወጣቶች ማህበር

በትግራይ ክልል የተማሪዎችንና የሊቪል ዜጎችን ደህንነት መንግስት የማስጠበቅ ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል

Amhara Youth Association 1

ህወሀት ትልቋን ትግራይ በአማራዎች መሬትና መቃብር እፈጥራለሁ በማለት ምናባዊ ካርታ ተቆጣጥራቸው በነበሩ የአገሪቱ ሚዲያዎች ሁሉ ማስተዋወቅ ጀምራ ነበር።ለዚህ አላማ መሳካት ያዘጋጀቻቸውን ሀይሎችና አጋሮች በመተከልና በሽዋ በማስነሳት ሀገር የማፍረስና ትልቋን ትግራይ የመመስረት ህልሟን ለማሳካት ጥረት አድርጋለች።

በመጨረሻም ነገሮች ሁሉ ከፕሮፖጋንዳ ወደ ፊትለፊት ጦርነት አምርተው በአማራ ልዩ ሃይል፣በአማራ ፋኖና ሚሊሻ ተጋድሎ ወልቃይት እና ራያን ወደ ቀድሞ ይዞታቸው ማስመለስ ተቻለ፡፡ የህወሀት እብሪት አስመራም ዘልቆ በሮኬት እስከ መደብደብ ደርሶ ስለነበር ዛላንበሳን እና ባድመንም አስነጠቃት።በጦርነቱ ህወሀት በእብሪቷ ከነ አባይ ፀሀየ፣ከነደብረፅዮን፣ከነስዩም መስፍን ጋር ጉድጓድ ውስጥ በተደበቀችበት ግንባሯን ተመትታ በረሀ ላይ ከሰመች። የትግራይ ነገር የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ሆነ።

የነገሩ አጀማመር እንዲህ ነበር።ህወሃት አማራው ጠላቴ ነው ብላ ከተነሳችበት 1967ና 1968 ዓ/ም ጀምሮ ተዘርዝሮ የማያልቅ ዘርፈ ብዙ በደል በአማራ ላይ እንዲደርስ ማኔፌስቶ አዘጋጀች።በ1980ዎቹ መጀመሪያ በአማራው ጫንቃ መንበረ ስልጣኑን ከተቆጣጠረች በኋላ መንግስታዊ መዋቅርን በመጠቀም በአማራው ላይ ከመሬት ወረራ እስከ ዘር ማጥፋት ዘመቻዎችን አካሄደች።በጊዜዋ አማራውን በቁጥር አሳንሳ ውክልናውን ነስታለች።እነ ሸዋንና መተከልን ለሌላ ወገን አስረክባለች።

ይህ ሁሉ ግፍ ጫፍ ሲደርስ የህዝብ እቢተኝነቶች በአማራ ወጣቶች አማካኝነት በአደባባይ ተጀመረ።ርዕሰ መዲናችን ባህር ዳርም ከ50 በላይ ወጣቶቿን በጠላት ህወሀት ተነጠቀች።ከነሐሴ 2,2008 ዓ/ም በኋላ አማራው ህወሀት በቃን በጎበዝ አለቃነው የምንተዳደረው አለ።ጀግናው የአማራ ፋኖም የትጥቅ ትግል ለማድረግ በየቦታው ተንቀሳቀሰ።ሁኔታው ህወሀት መራሹን መንግስት አሸበረ።ብዙ ሳይቆይ ትግሉ የለውጥ ፍንጭ አሳይቶ የህወሀትን አቅም ፈተነ።ሁኔታውን የታዘበው ከህወሀት ኢሕአዴግ ውስጥ የለውጡ አካል ነን ብሎ የወጣው ሃይል ህውሓትን ከፌደራል ሥልጣኗ ነቅሎ ወደ መቀሌ ሸኛት።

ተስፋ ያልቆረጠችው ሀወሀት ወደ አራት ኪሎ ለመመለስ ሌላ ስልት ቀየሰች። እብሪትና ሽብር መፍጠሯን አጠናከረች።የሰሜን እዝን ደፈረች።በዚህ ምክንያት አገር ከሚመራው ሀይል ጋር ተጋጨች። እብሪቷ የእዮቤልዮ ቤተመንግስትን ከርቀት እያስጎመጀ መቀሌንም አስትቶ ቆላ ተንቤን አስገባት፡፡

ህወሀት ጠላቴነው ባለችው የአማራ ህዝብ ከተሞች በጎንደርና በባህር ዳር ላይ ከሀገር የተዘረፉ ሮኬቶችን ወነጨፈች።ብዙ ሳትቆይ በአማራ ልዩ ሀይል፣ በመከላከያ፣ በፋኖና በአማራ ሚሊሻ ከነመሪዎቿ ተደመሠሠች።በወረራ የወሰደቻቸውን ወልቃይትን፣ሁመራን፣ጠለምትንና ራያን ተሸንፋ ለቀቀች።ባድመንና ዛላንበሳንም ተሰናበተች።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በውጭ ከለላ የተረፈው ጌታቸው ብዙ የአልሞት ባይ ድራማወችና ከጦርነት በፊት የነበረን ግዛት ይከበርልን እያለ አቧራ እያስነሳ ነው።ምን እንደታሰበ ባይታወቅም ከትላንት ጀምሮ ከፍተኛ የመከላከያ ሀይል …።

ውድ የአማራ ወጣቶች በቀጣይ ጊዚያት የምንሰማው ፣የምናየው እና የሚሆነው መጥፎም ሊሆን ይችላል።
በአሁኑ ሰዓት የአገረ መንግሰቱ የፓለቲካ አቅጣጫ በተለይ ከምርጫ በኃላ በጣም አስቸጋሪ ፤ከምንጊዜም በላይ የማይጨበት እየሆነ መጥቷል።
በአራቱም ማዕዘን ያለው አማራም ተደራጅቶ የማይበገር አንድ አካል መሆኑን ይቀጥል።ሁላችንም በንቃት በየ ድንበሩ በተጠንቀቅ እንቁም!!! ምንም ይሁን ምን በጦርነት ባስመለስናቸው ቦታዎች መደራደር አይታሰብም።የሚያስብም ካለ ጠላታችን ነው!!

ከአማራ ወጣቶች ማህበር ባህር ዳር ገጽ

2 Comments

 1. Well, all what you are saying is self-evidently and loudly clear not today but a long period of time back !!! No one with his or her right mind doubts this fact of our political sickness !

  Yes, you are absolutely right that TPLF must not be allowed to come back and try to disturb let alone to retake the very legitimate lands and properties of the Amhara Ethiopians !!! Never and never and never !!!
  Yes, you are absolutely right that the Amharas must stay alert or standby until those tugs of TPLF who are allergic to the very value of living together in a democratic Ethiopia would either be convinced and choose the right way of Dinh politics or to be defeated and eliminated !

  Here is my serious concern!
  with all due respect to what you are saying , I strongly argue and believe one very hard fact to deal with Is missing from your statement of reaffirming your commitment to legitimately challenge and defeat the long time deadly notorious political entity called TPLF! Believe or not or like it or dislike it, the noble commitment you are talking about will never be sufficiently effective and long lasting without going back to the very fundamental question of the political movement by all freedom and justice – loving people of Ethiopia to the extent of paying their irreplaceable lives three years ago ?was it not to bring about a fundamental democratic change of a political system and to make the very dream of living in freedom, justice, unity, peace and shared prosperity a reality ??? Absolutely it was and still is !!! So, I hate to say but I have to say that until you do answer this fundamentally critical question , all what you are talking about will never take you anywhere in the real sense of the term ! It would be very foolish if not stupid way of political thinking to simply blame and try to get rid of only one faction of the same deadly political system of EPRDF , but giving legitimacy to the other faction which controls the palace politics and which of course directly or indirectly committed and continued committing unprecedented crimes of politically motivated. I have to add that the very politics of doing things without a firm and long lasting principles and objectives will always remain emotion- driven and short -live that makes those ruthless political gangsters of EPRDF or Prosperity very glad . I am genuinely and reasonably afraid that the way you are doing politics will never make a meaningful difference as long as you keep jumping around the bush or around the central question of engaging in the struggle for fundamental democratic change of a political system instead of directly and straightforwardly dealing with the very hot spot of changing the very backward and deadly politics of ethnocentrism !

  Good luck !

 2. መንግስት በትግራይ ክልል የሲቪልና የተማሪዎችን ደህንነት ማስጠበቅ አለበት? ምን አይነት ቀልድ ነው። ከኋላና ከፊት እየተተኮሰበት በገጠርና በከተማ ሲቪል ለብሰው ለውጡን ተቀብለናል ባሉ ሰዎች ስንት ወታደሩን አራግፎ የወጣን መንግስት የሰዎችን ደህንነት እንዲያስጠብቅ መጠየቁ ቧልት ነው። መንግስትም ሆነ ወያኔ የሚነግሩን የላይ የላዪን ብቻ ነው። ብዙ ሰው አልቋል። ብዙዎች ከቀያቸው ተፋልሰዋል። የችግሮች ሁሉ ምንጭ የሆነው ወያኔ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል በማለቱ ድሃ አደግ የትግራይ ልጆች የት እንደሚሄድ ሳይገባቸው እሳት ውስጥ ተከተዋል። ይህን የፈጸሙትን የወያኔ የሃገር ውጭና የሃገር ውስጥ የሙታን ፓለቲከኞች አሸንፍን ገለ መሌ ቢሉ ነገሩ ሁሉ እንኩሮ ነው። የሆነው የአህያ ውደቆሽ ነው። የፌደራልና የወያኔ ሃይሎች ተቀጣቅጠው የሞተው ሞቶ፤ የቆሰለው ቆስሎ የሸሸው ነፍሴ አውጭኝ ብሎ ከስምንት ወራት በህዋላ የሁለቱም ሃይሎች ቁስላቸውና መከራቸው ስለበረታ የፌደራሉ መንግስት “ብርሌ ከነቃ አይሆንም እቃ እንዲሉ” ከወያኔ ቀንበር ነጻ አወጣኋችሁ ያላውን የትግራይ ህዝብ ጥሎ ፈርጥጧል። የማያዛልቅ ጸልቶ ለቅስፈት ይሉሃል እንዲህ አይነቱ ነው። ውስልትና እና መቀላመድ ስራቸው የሆነው የወያኔ ቡችሎች ደግሞ ድል አድርገናል እያሉ ለውጭ ሃገር ጋዜጠኞች የእስረኛ ክምር ማሳየት ጀምረዋል። ሲጀመር የትግራይ ህዝብ በወያኔ ክፋትና የዘመናት የጥላቻና የመከፋፈል መርዝ የተለከፈ በመሆኑ ፌዴራላዊውን ሃይል ምንም በጎ ነገር ቢያደርግለት አይፈልገውም። ቢፈልግም ድጋፉን ማሳየት አይችልም። ሌላው ወያኔ ያርደዋል። ቤቱን ያቃጥልበታል። ስንቶች የትግራይ ልጆች ናቸው በወያኔ ሴራ በእነዚህ ስምንት ወራት ያለቁት? ቤቱ ይቁጠረው። ስለዚህ አሸንፍን ተሸነፍን ለትግራይ ህዝብና ገበሬ ስንል ነው የወጣነው የሚለው ዜና ሁሉ ውሸት ነው። ወያኔ የሩቅ ጊዜ አላማውን ለመፈጸም አሁን ምቹ ጊዜ አግኝቷል። በጦር መሳሪያ ሃይል የአማራን ህዝብ በግልጽ ለመጨፍጨፍና የኤርትራን ሰራዊት ለመፋለም። ግን ሁለቱም ህልሞች ናቸው። የማይሆኑ። በዓለም ላይ ካሉ መሪዎች ውስጥ የምዕራባዊንን አሻጥር አበጥረው ከሚረድት መካከል ቀዳሚው አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ ናቸው። አሁን ደግሞ ጠ/ሚ አብይ የነጩ ሴራ ቁልጭ ብሎ የታያቸው ይመስለኛል። ስለሆነም ጠራርጎ ከትግራይ መውጣቱ ማለፊያ ነው። ግን አወጣጡ ያስረሽ ምቺው በመሆኑ በመንገድ ላይ ብዙዎች ሞተዋል፤ ተማሪዎች እዚያው ቀርተዋል። በቅንነት ለትግራይ ህዝብ ያገለገሉ የትግራይ ተወላጆች ወያኔ እንዲያርዳቸው በዚያው ተረስተው ቀርተዋል።
  አማራንና ኤርትራን እናጠቃለን የሚለው አቶ ጌታቸው ረዳ የተንኮል ማሰሮ እንደሆነ ሰው ሊያውቅ ይገባል። ግን ሁለቱንም ሃይሎች በጭራሽ የማጥቃት ጉልበት ወያኔ እንኳን አሁን የዛሬ 10 ዓመትም አይኖረውም። ሻቢያ ቢፈልግ በአንድ ቀን መቀሌ መግባት ይችላል። አማራውም ልብ አግኝቶ እየተሰባሰበ ራሱን መከላከል ስለሚፈልግ ወያኔ በአፉ ጉራ እንደሚነዛው ነገሮች ቀላል አይሆኑም። ዝም ብሎ የትግራይንም ህዝብ ሆነ ሌላውን ወገን ለመከራ ለመዳረግ እንጂ የዚህም የዚያኛውም ወገን ፉከራ ጅልነት ነው። የጦርነት መልካምነት የለውም። ሰው ከማስጨረስ ያለፈ።
  ግን የፌዴራል መንግስትም ሆነ የክልል መንግስት ከለላ ይሆነኛል ማለት በራስ ህይወት ማሾፍ ነው። ወያኔ አማራን ለማረድ እንደሚቋምጥ ከሚሰጣቸው መግለጫዎች መረዳት ይቻላል። ታዲያ መግለጫ በመግለጫ ከመሆን ይልቅ የጠላትን ቁመናና አመጣጥ፤ የትጥቅና ዝግጅት አይነት ተምኖ ራስን ለማይቀረው ፍዳ ማዘጋጀት ነው። መደንፋቱ፤ መግለጫ ማውጣቱ፤ የአለም ህበረተሰብ ወይም የኢትዮጵያ መንግስት ይደግፈኛል ማለቱ መረሳት ያለበት ነገር ነው። የውጭው ዓለም እኛ እንድንገዳደል ይፈልጋል። ሰው ቅነሳ ነው። የአረቡ አለም ደግሞ ሁሉም ባይሆኑ የነጭ ተቀጥላዎች ናቸው። እሳት ከማቀበል ወደ ኋላ አይሉም። ያኔ ለወያኔና ለሻቢያ በገፍ እሳት ያቀብሉ የነበሩ የአረብና የነጭ ሃገሮች ኤርትራ ሃገር ስትሆን በዚህ መንገድ እንርዳችሁ አላሉም። እኛ ስንጋደል ግን እርዳታው ይጎርፋል። ለዘመናት የሆነው ይህ ነው።
  የትግራይ ህዝብ በወያኔ አይጠቀምም። እኔ አፍቃሪ ብልጽግና አይደለሁም። ግን የጠ/ሚሩ መንግስት ለትግራይ ህዝብ ጥሩ ልብ ነበረው። የሆነው ግን ባጎረስኩ እጄን ተነከስኩ ነው። ያልተነገሩ ብዙ ጉዶች በትግራይ መሬት ተፈጽመዋል። አሸነፍን ብለው አዲስ አበባ ላይ ጥሩንባ ሲነፉ ስለሞተው ወገን የነገሩን የለም። ለመሆኑ ጄ/ አበባው የት አለ? ለምን ተሰወረ? ሌሎችስ የት ገቡ? ሄሊኮፕተርና ሌላ ከአሜሪካ የተቀለተውን የማጓጓዣ አውሮፕላን የገበረው መንግስት ከምን አንጻር ነው። አዎን የቴክኒክ ጉዳይ ይባላል። ግን ጉዳዪ ሌላ ነው። ብቻ ወያኔ አሁን መቀሌ ላይ መፏለሉ የመከራውን ምንጭ ያበዛዋል እንጂ አያነጥፈውም። የሚሆነው ግን እንዲህ ነው። እርስ በእርሳቸው ይበላላሉ። የቆሰለ አውሬ መጨረሻው እንደዛ ነው። ምድሪቱን አፈር መሬት አስግጠው እነርሱና መሰሎቻቸው ወደ ምዕራብና አረብ ሃገሮች ይፈረጥጣሉ። እስከዚያው አፈርናና ግድያው በትግራይ መሬት በራሱ በወያኔ ይቀጥላል። የፓለቲካ እብደት እንደዚህ ነው። መብረቃዊው ጥቃት ራሱን ሲያጋየው። ቃሌን ቆይተን ከጊዜ ጋር እንፈትሽ ለዛሬ ግን ይብቃኝ። ወያኔ ይምረኛል ብሎ የሚያምን አማራ ግን ልበ ቢስና አንገቱን ለስለት የሰጠ ነው። በማይካድራ የተፈጸመውን፤ በስልጣን ዘመናቸው በአማራህ ህዝብ ላይ ያደረሱትን ግፍ፤ አልፎ ተርፎም እንደ ቀን ሰራተኛ ሲላላካቸው የነበረውን የሰሜን እዝ የፈጸሙበት በደል ለቋሚ ትምህርት ይሆናል። ሞት አይቀርም። እየተጎተቱ እንደ ከብት ተወስዶ መገደል ግን የሞት ሞት ነው። ቀን ሳለ መዘጋጀት ነው። በቃኝ!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.