በዚህ ጽሑፍ አይጠመጐጥ ማለት ሌላ ትርጉም ካልተሰጠው በስተቀር ችግር ክፋት ምቀኝነት ከሐዽያን የሚል ፍቺ ተሰጥቶታል
ድሮ ነው በዕውሮች አገር ባለ አንድ ዓይን ሰው ንጉስ ይባል ነበር (In the country of blinds one eyed man is a king) በአሁኑ ጊዜ ሁሉም ታውሮ ንጉሥም ገለመሌ ምየለም
እንደሚታሰበው ዩኒርሲቲዎች የማስተማር የመራመር ቴክኖሎጂ ማፍለቅ እንዲሁም ለሠላም ለስልጣኔ ለከባቢአየር ለሰውልጅ ምቾት ለስራ ዕድል ፈጠራ ግንባር ቀደም ተልእኮ ያላቸው ተቋማት ናቸው ነገርግን በ ኢትዮጵያ ሙሉ በምሉ አቅጣጫቸውን ስቷል
ዳግማዊ አፄምንሊክ በ 1903 ለመጀመርያ ጊዜ አንደኛ ዸረጃ ትምህርት ቤት አቋቋሙ በጊዜው የጣልያን ቅኝገዥዎች በኤርትራ ምድር ትምህርት ይፈቀድ የነበረው እስከ ሥድሥተኛ ክፍል ድረስ ብቻ ነበር በኢትዮጵያ ከዚህ ወቅት እስከ አፄ ኃይለ ለስላሴ ንግስና ማንበብ እና መፃፍ በተጨማሪ የውጭ ቋንቋ ያወቀ እንደ ፒኤችዺ (PhD) ይቆጠር ነበር በርግጥ የበሰሉ ነበሩ ምክንያቱ አብዛኞቹ ባሕላዊውን የሐይማኖት ትምህርት ያጠናቀቁ ነበሩ
ነገር ዓለሙ የተበላሸው ከጅምሩ በ1956 አፄ ኃይለ ለስላሴ ቤተመንግሥታቸውን በመስጠት የመጀመርያው ዩኒቨርሲቲ የያኔው ቀዻማዊ ኃይለ ለስላሴ የአሁኑ አዺስ አበባ ወይም ዘመዶዳችን ደሥ እንዲላቸው “ፍንፍኔ ዩኒቨርሲቲ” አቋቋሙ ዓላማቸው ከልብ ከመነጨ ኢትዮጵያን ወደፊት ያራምዻል በሚል ራዕይ ነበር
በተፃራሪ ግርማዊ ቀዻማዊ ኃይለ ለሥላሴ ያሰቡት ሳይሆን የዓይጠመጐጥ ማምረቻ ሆነ ይኸውላችሁ አገር አፍራሽ የሆኑ EPLF, TPLF, OLF EPRP , EPRDF ወዘተ የሚባሉ ድርጅቶች እና ኢሣያስ መለሥ ብርሃነ መስቀል ወዘተ የተባሉ ግለሰቦች ከውጭ አገር በመጡ ዩኒቨርሲቲ አስተማሪዎች አገር የማፍረስ ሴራ ተክነው አሁን ለተፈጠረው ምስቅልቅል እና ፍጅት ጠንሳሾች ከዚሁ ዩኒቨርሲቲ የተመረቱ ናቸው
በደርግ ጊዜ ከመሠረተ ትምህርት በስተቀር ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምንም አልተለወጡም የውጭ አገር አስተማሪዎች ጥለው ሲሄሴዹ በኢትዮጵያውያን ቢተኩም የነበረው ፈላጭ ቆራጭ አሥተዳደር በመሸሽ ብዝዎች የተካኑ አስተማሪዎች አገር ጥለው ኮበለሉ እንዺሁም ብዙ ብርቅየ ተማሪዎች በቀይሽብር ተጨፈጨፉ ደርግ የዩኒቨርሲቲው አመራር ከችሎታ ይልቅ ደማቅ ሰመያዊ በለበሱ ሰዎች ተተካ (ኢሰፓአኮ) የመምህራን ማሕበርንም አፈረሰ
በ ወያኔ ማግስት ከዩመጀመርያ ቀን ጀምሮ ዒላማው ዩኒቨርሲቲዎች ማፍረስ እና መቆጣጠር ያለመ ነበር ይህም በሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች ነው አንደኛው ዩኒቨርሲቲዎች አመፅ ሊያስነሱብኝ ይችላሉ ብሎ ስለ ስጋ ሁለተኛው ደግሞ ቂም በቀል ነው ቂም በቀል የኃላቀርነት እና ያለመሰልጠን መለክያ ነው ወያኔ ከተመሠረበት ዋና ዋና መርሆዎች ብቀላ ነው ሺ ዓመታት ወደኋላ ተመልሶ የዟጌን መንግሥት ይበቀላል! ከብቀላዎቹ ሁሉ በትምህርት ላይ የሰራው የትውልዽ የመደምሰስ ወንጀል ውደር የለውም ይህም ከበታችነት ስሜት የመነጨ ነው በ 1960 ዓም ተማሪዎች በገና ወራት (Christmas ) ፈተና ያላለፈ ይባረር ነበር ሲባረር ደግሞ ከጫካ በስተቀር መሄጃ አልነበረም ምንም እንኳን አሁን ጐበዝ ተማሪ ነበርን ብለው የወያኔ ባለስልጣናት ቢደነፉ የተማሩ እና ጭንቅላት ቢኖራቸው እዚህ አያደርሱንም ነበር በኔ በኩል በዓለም ላይ ካሉ ሰዎች ዝቅተኛ IQ ይገባቸዋል
ወያኔ በትምህርት ላይ ከሰራቸው ወንሎች ከዚህ በታች ልዘርዝር
ሀ. በስመ ዼሞክራሲ ጥራት የሌላቸው ትምህርት ቤቶች ማብዛት በአፍ መፍቻ ቋንቋ ሰበብ ማንነት ላይ ያተኮረ ትምህርት መንዛት ዕውቀትን መገደብ እና አንዽ ላይ ይኖሩ የነበሩ ሕረተብ እንዳይግባቡ ማድረግ አማርኛ ቋንቋ ማጥላላት ፊደላትን መቀየር የጋራ እሴት ተረስቶ የውሸት ስነ ዜጋ ማስተማር ሥራ የማይፈጥር ካሪኩለም ማባዛት የማይረባ ለብ ለብ ኮንስትራክሽን መገንባት
ለ. ወያኔን የማይደግፍ አስተማሪ ማባረር አስተማሪን ማደኸየት የአንድ ፕሮፌሠር ደሞዝ በ ኢትዮጵያ $200 ሲሆን ነርግን በኡጋንዳ $4000 ይኸ ወያኔን ትምህርት ላይ ያለው ትኩረት በጣም አናሳ መሆኑ ያሳያል ለአባላቶቹ መኖርያ ቤት ሲሰጥ ሌላው በየኩሺናው ኪራይ ተወሽቋል
ሐ. መቀሌ እንደ መካ ከሆነች ሰነባብታለች መቀሌ ካልተደረሰ የዩኒቨርሲቲ ፕረዚዳንት ወይም ስልጣን ማግኘት አይቻልም በኢትዮጵያ ከፍተኛው ባጀት የሚበጀተው ለትምህርት ሚኒስቴር ሲሆን የላቀ ድርሻ ለከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚመደብ ነው ቦርድ የተባለ የአንድ ብሔር ስብስብ ከመሬት ሽያጭ ቀጥሎ ከፍተኛ የሙስና ገንዘብ ማግበስበሻ ሥርዓት በማበጀት ባጀቱ ይዘርፋሉ
መ. ዩኒቨርሲቲዎች የፌደራል መንግስት ናቸው ይባሉ እንጂ የሚተዳደሩት እና የሚመሩት በክልል ፓርቲዎች ከሆነ ውሎ አድሯል በነገራችን ሲቪል ሠርቪስ የተባለ ዩኒቨርሲቲ ሥራው ጡንቻ ራስ የሆኑ ሰዎች አገሪቱ እንዲመሩ መልምሎ የሚያመርት ነው በአዲስ አበባ ነዋሪዎች ድንጋይ ማምረቻ ተብሎ ይጠራል
- በ ዩኒቨርሲቲ የክልሉ የገዢ ፓርቲ አባል ካልሆኑ አስተማሪዎች አይቀጠሩም
- የክልሉ የገዢ ፓርቲ አባል ካልሆኑ የትምህርት ዕድል ወይም የምርምር ገንዘብ ወይም እድገት አይሰጥም
- የደህንነት አባላት ዩኒቨርሲቲ ቅጥርግቢ እንዲሁም ማስተማርያ ክፍል ገብተው አስተማሪዎችን ይሰልላሉ በተለይ ከመቀሌ የድህረ ምረቃ ተማሪዎች ተብሎ የሚመጡ ተማሪዎች
ሠ. የውሸት ዲግሪዎች እስከ ከፍተኛ ባለሥልጣን ይታደላል ባጠቃላይ ማጭበርበር ጨመረ የውሸት የዶክትሬት ዲግሪዲ ከተቀበሉ ባለስልጣናት መካከል አቦይ ሥብሒ ነጋ አቦይ ዱላ ገመዳ አቦይ ሐድሽ ለገሰ አቦይ ሺፈራሂ ሽጉጤ ይገኙበታል ለልጆቻቸው እና ለሚስቶቻቸው ጭምር ዲግሪ እንዲሰጥላቸው ወረፋ ይዘው ነበር ይኸ የውሸት ዲግሪ ከውጭ አገርም ይገኛል ራሳቸው ለቅኝ ገዢዎች የሸጡ ምሁራን ዲግሪ ካስፈለገም ፓብሊኬሽን ሽልማት (እስከ ኖብል ፕራይዝ የሚደርስ) ዳጐስ ያለ ደሞዝ እንዲሁም በ ሚድያ እውቅና ያለምንም ጥረት ይቸራቸዋል ከዛ ተልእኳቸው በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር መሠለል እና ይችን አገር ገደል መክተት ነው
ረ. ዩኒቨርሲቲዎች የዘር እና የግዛት ምልክት (Territorial Demarcation) ሆኑ ለምሳሌ ወልቃይት እና ራያ ዩቨርሲቲ የተባሉ የትግሬ ክልል የማስፋፋት ዕቅድ ለማሳካት የተቋቋሙ ናቸው
ሸ. ተማሪዎች ከራሳቸው አከባቢ ርቀው መማር ትርፉ ጥቃት እና ግድያ ሆነ ከርሟል የባለሥልጣን ልጆች ውጭ አገር አልያም በቀጭን የስልክ ትእዛዝ በፈለጉት ዮኒቨርሲቲ ዘመዶዳቸው ማስመደብ ችላሉ
ቀ. ብሔራዊ ፈተናዎች ተአማኒነት የላቸውም የድሀ ልጅ በኩራዝ ሲያጠና የወያኔ ልጅ ግን ሠርተፊኬት ይሠራለታል በክልሎች እርስበስ ውድድር ስላለ በዛ ያለ ተማሪ ለማሳለፍ ማኮራረጅ የተለመደ ነው ፈተና የወደቁ የ15 እና16 ዓመት ወጣቶች ደግመው መማር ስለማይፈቀድላቸው ለክድምና እና ለልመና በየአገሩ ይሰደዳሉ እንደምንም ብሎ ሁሉንም ችሎ የገዢው አባል ያልሆነ ዶክተር ወይም ኢንጂነር ሥራው ኮብል ስቶን ወይም ቡና ማፍላት ብቻ ነው
በ. ወያኔ ጭንቅላት የለውም የቅል ራስ ነው ግን እንደሮቦት መላላክ ይችላል ለዚህም የድሮ ብርቅ የየኢትዮጵያ ምሁራን ለማጥፋት ሌት ተቀን ይሰራል ከተለያዩ መንሥታት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ድጋፍ ያገኛል ከዚህ ስትራቴጂ አንዱ የኢትዮጵያ ምሁራን በማባረር ዩኒቨርሲቲዎቹ ኒውደልሂ እስክያስብላቸው ድረስ ህንዶችን መቅጠር ሲሆን ሌላው ደግሞ በውጭ አገር በብዛት ራሱልሒቃን ማሰልጠን ነው ለዚህም 95% ( በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ) ሊሒቃኑ የተማሩት በኔዘርላድ በልጅየም እና በኖርዌ ይሲሆን አንድ ወዳጄ እንደነገረኝ የኖርዌይ ዮኒቨርሲቲ በትግሬዎች ብዛት መቀሌ ዮኒቨርሲቲ መስሎ ነበር
ከላይ በተዘሩት ምክንያቶች የኢትዮጵያ ዩቨርሲቲዎች እና የምህርት ሥርዓት አይጠመጐጥ ማምረቻ ሆኗል
ከመሰናበቴ በፊት ትንሽ ሰለወቅታዊ ሁኔታ ዘና ላድጋችሁ
- ዾ/ር ደብረፅዮን የያዘው ቡዳ አልታወቀም በድንገት ካለፉት ሦሥት ወራት ጀምሮ አማርኛ አልናገር ብሎ ከ ዾ/ር ዓብይ ጋር በልሣን (tongues) መነጋገርምሯል ተባለ
- ቪኦኤ (VOA) እና ቢቢሲ (BBC) በ ሦሥት የኢትዮጵያ ቋንቋዎች በሬዽዮ የሚያሠራጩት በማወቅም ሆነ ባለለ ማወቅ ኢትዮጵያ በ ቋንቋ እንድትከፋፈል እና ዩዘር ግጭት እንዺካሄድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው ተረጋግጧል!
- ብሔራዊ ትያትር ራስ ትያትር ሀገር ፍቅር ትያትር ከስመው በምትካቸው የቤተመንግሥት ቲያትር የፓርላማ ቲያትር የአክቲቪስች ቲያትር የፓርቲዎች ቲያትር የዘወትር ማዝናኛ ፕሮግራሞችኗል
- መንግስት በ COVID 19 ሠበብ ትምህርትቤቶች በተሎ ላይከፍት ይችላል ምክንያቱም ተማሪዎች ተመርቀው ሥራ ስለማያገኙ
ሕልም እልም አልኩኝ ተነስቸ ኢትጵያየ ስትፈርስ አይቸ!
የፍፃሜው ጦርነት ነው ሁሉም ዘብ ይቁም በቦታው!
ኢትዮጵያ ለዘልዓለም ትኖራለች!
ሊጋባው በየነ