August 10, 2020
14 mins read

ሕዝብ ሆይ! እንደማመጥ እንጅ! ጋሰለ አረሩ፤ አዴፓ ብአዴን፤ ብልጽግናም ይህ አድግ ነው!  

በላይነህ አባተ ([email protected])

የጥበብ መጀመርያው እግዚአብሔርን መፍራት እንደ ሆነው ሁሉ አማራን ተመጥፋትና አገር አልባ ተመሆን ለማዳንም የመጀመርያው ጥበብ የተንኮል ቁማር ተጫዋች ይህ አድግንና ጂላንፎው ሁሉ ቁማር የሚጫወትበትን የጆከር ካርታውን ብአዴንን በሚገባ ማወቅ ነው፡፡

የበፊቱ ይህ አድግ አማራን ተገዛ እርስቱ ተወልቃይትና ተራያ እንዳጠፋው የአሁኑ ይህ አድግ ደሞ አማራን ተገዛ እርስቱ ተምስራቅ፤ ተደቡብ፣ ተደቡብ ምዕራብና ተመከካለኛው ኢትዮጵያ ሊያጠፋ ሰይጣን የላከው የወሮ በሎች ቡድን ነው፡፡

በሕዝብ ነፍስና በአገር የተንኮል ቁማር ተሚጫወተው ይህ አድግና ተመጫወቻው ካርታ ተብአዴን የሚጠቅም ነገር መጠበቅ የበሬ ቆለጥ ይወድቅልኛል ብላ ጆሮዋን ቀስራ ስትከተል ተዋለችው ዘልዛላ ቀበሮም ማነስ ነው፡፡

መልከ-ጥፉን በስም ቢደግፉት መልከ-ጥፉነቱ በላፒስ ተፍቆ አይጠፋም፡፡ በንጹሀን ደም እጅና እግሩ የተጨማለቀው፣ የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈጠመውና አገር እስከማስገንጠል ብሄራዊ ክህደት የፈጠመው ይህ አድግ “የብልጥግና ፓርቲ ነኝ!” እያለ ጭራቅ መልኩን በስም ሊደግፍ እየጣረ ነው፡፡ መንዘላለዘልና መጃጃል የማይሰለቸው ስንቱ ዜጋም የይህ አድግን ብልጽግና ሊውጥ አፉን እንደ ሰማይ ከፍቶ እየተጠባበቀ ነው፡፡ በእንዲህ ዓይነት በመርዝ በተለወሰ ከረሚላ ከአንዴም ሁለቴ፤ ተሁለቴም ሶስቴ የሚንዘላዘል ዜጋ ዓይምሮው በላቦራቶሪ መፈተሽ ያለበት ከንቱ ፍጡር ነው፡፡ በራሱ ተስፋ ቆርጦ በሱሰኛ ይህ አድጎች እምነት ጥሎ የሚንዘላዘል አማራ የጅል ጅን ስለሚኖርበት ዲ ኤን ኤ (DNA)ው መጠናት ያለበት አሳዛኝ ፍጡር ነው፡፡

የብአዴን “አዴፓ ነኝ” ማለት የአረሩን “ጋሰለ ነኝ!” ማለት የሆነውን ያህል የይህ አድግ “ብልጥግና ነኝ!’ ማለትም የአረሩንና የጋሰለን ታሪክ እንደገና የሚያስተርክ ነው፡፡ ባደኩበት ሰፈር አቶ አረሩና አያ አዳነ የሚባሉ ሰዎች ይኖሩ ነበር፡፡ አቶ አረሩን ኮስማናዋ እናቱ እማማ ሐብትሽ ምን እያበሉ እንዳሳደጉት አላውቅም ቁመናው የገደል ግማሽ ያኻክል ነበር፡፡ ጥምቡልዝ መልኩም የተወቀጠ ኑግ ይመስል ነበር፡፡ አቶ አረሩ የገደል ግማሽ እንደሚያህል ለመግለጥ የሰፈሩ ሕዝብ ” አረሩ ብቻውን የቤት ጣራ ተሸክሞ መሄድ ይችላል” ይለው ነበር፡፡ አያ አዳነ በተቃራኒው ቁመናዋ እንደ ስንበሌጥ የሰነነች መልኳም በቀይና በቀይዳማ መካከል ያለች ቆፍጣና ጎበዝ ነበረች፡፡ አቶ አዳነ በሰንጢ ንግግሯ እንደ አለቃ ገብረ ሃና የምትታወቅ ጠቢብ ነበረች፡፡ የአያ አዳነን የንግግር ሥስለትነት ለመግለፅ ማህበረሰቡ “የአዳነ ንግግር ያልጋለ ብረት ከመቅፅበት ይቆርጣል” ይላት ነበር፡፡

በዚሁ ሰፈር ካቶ አረሩ በተጨማሪ አረሩ የሚባል ጠብደል ጥቁር አለሌ ይኖር ነበር፡፡ ስለ አህያው አረሩ ባላውቅም አቶ አረሩ የህዝቅኤል ጋቢሳን ያህል ሥሙን ይጠላው ነበር። አቶ አረሩ ከአለሌው ለመለየትና  አረሩ የተባለውም የተቀቀጠ ኑግ በመሰለው ቆዳው ምክንያት ስለመሰለው ባካባቢው ባልተለመደ መንገድ ስሙን ጋሰለ ወደ እሚባል ስም ቀየረና አረፈው፡፡ ይኸንን በአካባቢው ያልተለመደ የሥም ለውጥ  የተረዳ አብዛኛው የአቶ አረሩን ሥም በየቤቱ እያነሳ እየጣለ ሌላውም “ሥሙን መለወጥ መብቱ ነው!” እያለ የአንድ ሰሞን የቡና ቴራቲም ወሬ አደረገው፡፡

ብዙውን ጊዜ ተመንጋው ጋር የማትነዳዋ አያ አዳነ ግን የአቶ አረሩ ድንገተኛ ሥም ቅየራ የአንድ ሰሞን የቡና ወሬ ሆኖ እንዲቀርና እንደዚህ ዓይነት ባህል እንዲለመድም አልፈቀደችም፡፡ አብዛኛው ሰው አቶ አረሩን በአዲሱ ስሙ ጋሰለ እያለ ሲጠራው አያ አዳነ ግን በሥሙ አፍሮና በማንነቱ ተሸማቆ ስም በቀየረው አቶ አረሩ በሽቃ በማያስፈልገው ቦታ ሁሉ “አረሩ” ብላ እየተጣራች አስቸገረችው፡፡ ይኸንን የአያ አዳነን ጥኑ አቋም የተመለከቱ ሽማግሌዎችም አረሩን በፈለገው ስም ጋሰለ ብላ እንድትጠራው  አያ አዳነን ቢለምኗትም “ሥምን የሚያወጣው ወላጅና እግዚአብሔር ነው፡፡ ስለዚህ እናቱ እማማ ሐብትሽ ባወጡለት ሥም እጠራዋለሁ” ስትል በአቋሟ ጠናች፡፡

ባያ አዳነ እምቢተኝነት ያልተደሰተው የድሮው አረሩ ያሁኑ አቶ ጋሰለ በበኩሉ “አዳነ ጋሰለ ብሎ ታልጠራኝ ምላሱን እቆርጠዋለሁ” እያለ በሰፈሩ ማስወራቱን ቀጠለ፡፡ ዳሩ ግን ጋሰለ የሚባል ሥም ከአያ አዳነ አንደበት እንኳን በውኑ በህልሙና በቅዠቱም አልወጣ አለ፡፡ እንዲያውም አያ አዳነ በበነነ በተነነው “አረሩ….” የሚለውን ቃል ከወትሮውም በበለጠ እያነሳች አቶ ጋሰለን ማሳቀቁንና እንደዚህ ዓይነት በራስ ተሸማቆ ሥምን የመቀየር ባህል እዳይለመድ ማስተማሩን ቀጠለች፡፡

አቶ ጋሰለና አያ አዳነ በእንዲህ ዓይነት ውጥረት ውስጥ ሳሉ በአንድ የሰንበት ቀን አያ አዳነ አቶ ጋሰለ ጋቢውን ተከናንቦ ድንኳን መስሎ አህያው አረሩ ሳር ከሚግጥበት መስክ ተቀምጦ አየችው፡፡ አያ አዳነም በአቶ ጋሰለ አጠገብ ስታልፍ “ደህና አደርክ አረሩ” የሚል ሰላምታ አቀረበች፡፡ አቶ ጋሰለ ሰላምታውን እንዳልሰማ ሁሉ “ምን አልክ?” ሲል በንዴት ጠየቀ፡፡ አያ አዳነም በሽመሉ አለሌውን አረሩን እየጠቆመች “ያኛውን አረሩ ነው!” ስትል መለሰች፡፡

እናቱ እማማ ሐብትሽ ያወጡለትን ስም በማንነቱ አፍሮ እንደቀየረው አቶ አረሩ በቀደም ብአዴንም ሥሙን አዴፓ ብሎ ቀየረው፡፡ አሁን ደሞ ይህ አድግ በማንነቱ አፍሮ ፈጣሪው ህወሀት ያወጣችለትን ሥም ብልጽግና በሚል አብለጭላጭ ሥም ቀየረው፡፡ በአለሌው አረሩ ሥም እንደተሰየመው አቶ አረሩ ሁሉ ይህ አድግም ቀላሹ ህወሀት ባወጣችለት ሥምና በባርነት ግብሩ ተሸማቀቀ፡፡ ይህ የተሸማቀቀ ወንጀለኛ ድርጅትም ሥሙን ወደ ብልጥግና ቀየረና አረፈ፡፡

ዳሩ ግን ጋሰለ የሚለው ስም የአቶ አረሩን መልክና ምንነት እንዳልቀየረው ሁሉ ብልጥግና የሚለው ሥም የይህ አድግን መልክና ምንነት አይቀይረውም፡፡ ብልጥግና የሚለው ስም ይህ አድግ ለሰላሳ አመታት በኢትዮጵያ ሕዝብ የፈጠመውን ወንጀልና ክህደት እንደ እንዶድ አያፀዳውም፡፡ ብልጥግና የሚለው ሥም ይህ አድግ የህወሀት የእጅ ስራ መሆኑን፣ ህወህትም የሻብያ ዲቃላ መሆኑን፤ ሻብያም የታሪካዊ ቅኝ ገዥዎችና አረቦች የማደጎ ልጅ መሆኑን አይቀይረውም፡፡

ብልጽግና የሚለው ስም ብአዴንን ተአሽከርነት አያዋጣውም፡፡ ብልጽና የሚለው ስም ብአዴንን ጌቶቹ ሲያዝዙት የአማራን ወጣቶች ተማሰርና ተመግደል አይገታውም፡፡ ብአዴን አጋሰስ ሆኖ እየተጫነ ያዘረፈውን ሐብት አያስመልሰውም፡፡ ብልጽግና የሚለው ሥም ብአዴን የአማራን ዓይን ጨፍኖ ለህወሀት ያስረከባቸውን ራያን፣ ሁመራና ወልቃይትን አይመልስም፡፡

ብልጽግና የሚለው ማታለያ ብአዴን ከቢሮው ጣራ አልሞ ተኳሽ አንጠልጥሎ ባህርዳር ያሰዋቸውን ወጣቶች ነፍስ አይመልስም፡፡ ብልጽግና የሚለው ማጭበርበሪያ ስም ብአዴን በህወሀት አሽከርነት በድብቅ ስፍራዎች ያስቀበራቸውን፣ ያሰለባቸውን፣ ያስገረፋቸውን፣ ያስጠለፋቸውና አካለ ጎደሎ ያስደረጋቸውን ዜጎች አይታደግም፡፡ ብልጽግና የሚለው ሥም ብአዴን በአምባ ጊዮርጊስ፣ በጎንደር፣ ደብረታቦር፣ ዳንግላ፣ ቡሬ፣ ወልዲያ፣ ማጀቴና ሌሎችም ቦታዎች ያስፈጃቸውን ዜጎች አያስረሳንም፡፡

ብልጽግና የሚለው ማታለያ ብአዴን “አያገባኝም” እያለ በበደኖ፣ በአርባ ጉጉ፣ በአርሲ ነገሌ፣ በጉራፈርዳ፣ በጎሬ፣ በወለጋ፣ በመተከል፣ በሀገረ ማርያምና ሌሎችም ሥፍራዎች ያስፈጃቸውንና ያሰደዳቸውን አማሮች ታሪክ አይፍቀውም፡፡

ስለዚህ አቶ ጋሰለ አረሩ ነው፡፡ ግልቡ ብልጽግናም ኢህዴግ ነው፡፡ አዴፓም ብአዴን ነው፡፡ እማማ ሐብትሽ  ለልጃቸው ያወጡለት ሥም አረሩ ነው፡፡ ከአማራ መቃብር ሪፐብሊኳን ለመመስረት ህወሀት ያደለበችው አለሌ ይህ አድግ፤ ለበኩር ልጇ የሰጠችው ሥም ደሞ ብአዴን ነው፡፡

አረሩ፣ ይህ አድግም ሆነ ብአዴን ካለ እናቶቻቸው ፈቃድ ሥማቸውን መቀየር ክህደት ነው፡፡ አረሩ ሺ ጊዜ ሥም ቢቀይር እናቱም ሺ ጊዜ እማማ ሐብትሽ ናት፡፡ ብልጽግና የተባለው ይህ አድግም ሺ ጊዜ አስቀያሚ መልኩን በስም ሊደግፍ ቢሞክር ፈጣሪው ጭራቁ ህወሀት ነው፡፡ ብአዴንም ሺ ጊዜ ሥም ቢቀይር እናቱ ሰይጣኗ ህወሀት ናት፡፡ በአፈጣጠራቸው አፍረው አረሩ፣ ይህ አድግም ሆነ ብአዴን ሥማቸውን ቢቀይሩም እናታቸው፣ መልካቸው፣ ግብራቸውንና ታሪካቸው ዘላለማዊ ናቸው፡፡

ስለዚህ መልካቸውን፣ ግብራቸውንና ታሪካቸውን በሚገልጡትና እናቶቻቸው ባወጡላቸው ሥሞች አረሩ፣ ብአዴንና ይህ አድግ ተብለው ቢጠሩ መልካም ነው፡፡ ጋሰለ አረሩ፣ አዴፓ ብአዴን፣ ብልጽግናም ይህ አድግ ነው፡፡

 

ታህሳስ ሁለት ሺ አስራ ሁለት ዓ.ም.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop