ከሚገድለኝ ሰይጣን ይልቅ የሚሰድበኝ ባለስልጣን ይሻለኛል! – ስዩም ተሾመ

አቶ  ሽመልስ_አብዲሳ “በትላንትናው እለት የተናገረው ነው” ተብሎ የተሰራጨው መረጃ #ከሰባት_ወር በፊት #የብልፅግና_ፓርቲ ገና በምስረታ ሂደት ላይ እያለ የተናገረው መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። በወቅቱ የድርጅቱን አባላትና አመራሮች በኦቦ ለማ መገርሳ፣ ወ/ሮ ጠይባ እና በዶ/ር ሚልኬሳ ከሚመራው ብሔርተኛ ቡድን ለመነጠልና በድርጅቱ ውስጥ ተፈጥሮ በነበረው የሃይል ሹኩቻ አሸናፊ ሆኖ ለመውጣት በሚደረግ ጥረት የተናገረው እንደሆነ ተረጋግጧል።
አቶ ሽመልስ የተናገረበት ግዜና ቦታ ምን ያህል የተለያየ ቢሆንም አዲስ አበባን አስመልክቶ የተናገረው ነገር መቼም፥ እንዴትም ትክክል አይሆንም። ይሁን እንጂ በወቅቱ ድርጅቱ ውስጥ የጃዋር መሃመድ ጉዳይ አስፈፃሚ የነበሩት ከላይ የተጠቀሱት የኦዴፓ አመራሮች ከኮዬ ፈቼ ኮኖደሚኒዬም ጋር በተያያዘ ሲያራምዱት የነበረው አቋምና ጉዳዩ በብሔርተኞቹ ዘንድ የነበረው ድጋፍ ሲታሰብ እነ ሽመልስ የነበሩትን አጣብቂኝ በግልጽ ያሳያል። ያ ባይሆን ኖሮ ተቀናቃኙ ቡድን አሸናፊ ቢሆን ኖሮ አሁን ላይ ጃዋር መሃመድ መገኛው እስር ቤት ሳይሆን ቤተመንግሥት ይሆን ነበር። ስለዚህ አቶ ሽመልስ የተናገረውን ነገር ከዚህ አንፃር ማየት ተገቢ ነው።
ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ከሰባት ወር በፊት የተደረገውን ንግግር ልክ ትላንት እንደተደረገ ተደርጎ የወጣው የጃዋር ጉዳይ አስፈፃሚዎች ለግምገማ ሲቀርቡ እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል። ስለዚህ የመንግስት ስልጣንና ሃላፊነት ይዘው በአክቲቪስት የሚመሩ፤ ለምሳሌ ጥቅምት 12/2012 ማታ አቶ ጃዋር መሃመድ ባስነሳው ሁከትና ብጥብጥ በንፁሃን ዜጎች ላይ ጥቃትና ጉዳት እንዳይደርስ ከመከላከል ይልቅ የጃዋር ጠባቂ ለመሆን በውድቅት ሌሊት መኖሪያ ቤቱ ድረስ የሄዱት ለማና ጠይባ፣ ልክ በድርጅቱ ግምገማ ሲደረግባቸው ከሰባት ወር በፊት የተቀዳን ንግግር #ለፅንፈኛ_የአማራ አክቲቪስቶች Leak አደረጉ። ህዝቤ እየተነሳ እሪሪሪሪ አለ።
ነገር ግን ይሄን መረጃ አሾልኮ ያወጣው ቡድን ቀንደኛ የጃዋር ጉዳይ አስፈፃሚዎች፣ ይህንንም ያደረጉት ጃዋርንና ግብረ-አበሮቹን ለማስፈታትና እንደ ለመደው እናታችን ላይ እንዲፈነጭ ለማድረግ ነው። ስለዚህ ይህን ሴራና ተንኮል የጠነሰሱት በግምገማ ከአባልነት ሊሰረዙ እንደሆነ ሲያውቁ ነው። ነገር ግን የእነሱ ቡድን አሸናፊ ሆኖ ቢወጣ ኖሮ ሽመልስ የተናገረውን እነሱ በተግባር የሚያደርጉትን እና ያደረጉትን ነው። የኮዬ ፍቼ ኮንደሚኒየም ለነዋሪዎች ሊተላለፍ በኦሮሚያና አዲስ አበባ መካከል ያለው የድንበር ጉዳይ መፍትሔ ስላላገኘ ብለው የፃፉት ደብዳቤ ለዚህ ማሳያ ነው። በአጠቃላይ አቶ ሽመልስ ከሰባት ወር በፊት የተናገረው ከዚህ ፅንፈኛ ቡድን ጋር በነበረው የሃይል ሽኩቻ አሸናፊ ሆኖ ለመውጣት ነው።
“ዋሽቱ ማስታረቅ” እንደሚባለው አቶ ሽመልስ የተናገረውን ተናግሮ ድርጅቱና የክልሉ መንግስትን ከእንዲህ ያለ ፅንፈኛ ቡድን መታደግ በመቻሉ ሊያስመሰግነው ይገባል። ከሰባት ወር በፊት ሆነ ትላንት በተለይ በአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ የተንፀባረቀውን አቋም  ፋሽታዊ ነው በማለት አውግዤያለሁ። ነገር ግን ሽመልስ ሆነ ሌላ ሰው ይሄን የተናገረው በእውን የተረጋገጠ ፋሽታዊ አቋምና አመለካከት ያላቸው አመራሮች በክልሉም ሆነ በሀገር ደረጃ አሸናፊ ሆነው እንዳይወጡ ለማድረግ በሚል ስለሆነ “እሰይ… አበጀህ” ብዬዋለሁ።
ምክንያቱም ያ ቡድን ባይገታ ኖሮ ምን ሊከሰት እንደሚችል በዚህ አመት ጥቅምት 12 እና ሰኔ 22 በተግባር አይተንዋል።
ሽመልስ የተናገረው በወቅቱ ትክክል ነው
ስዩም ተሾመ
ተጨማሪ ያንብቡ:  በዝቋላ ገዳም አራት መነኮሳት መገደላቸውንየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክስርቲያን አስታወቀች

21 Comments

  1. ጀግናው ስዩም ዘወትር ሀቅን ከመጋፈጥ ፍንክች አትልም:: የሺመልስን ንግግር ሰርግና ምላሽ አድርገው የሚዝናኑበት በይበልጥ የህውሀት አጨብጫቢዎች ናቸው:: ቀኝም ነፈሰ ግራ ሺመልስ የተናገረው ለፖለቲካ ኳኳታ ሊጠቅም ይችል ይሆናል መሬት ላይ ሊወርድ ግን አይችልም:: የዐቢይ ብልፅግና የጃዋርን ክንፍ ከድርጅቱ ማፅዳት መጀመሩ ለኢትዮጵያ ሀገር ግንባታ አስፈላጊ ነው::

    • ሃቅን ሳይሆን ጫቱን ይዞ ይክለፈለፋል የሆዳም ምስክር ሆዳም ! ስዩም የሚባል የጫት ሱሰኛ በብልፅግና ዳረጎት በየቀኑ ጫት መግዣ ካልተሰጠው እራሱን አንቆ ይገላል
      Lost soul, sold his soul to the devil

  2. ምን አይነት አሳፋሪና ለሆድህ ያደርክ የብልጽግና ካድሬ ነህ? ቢቻልህ መቃብር የበቀል ጫት እየሸመጠጥክ ልክ እራስህን እንደ ትልቅ ፖለቲካ ተንታኝ አድርገህ ባትቀባጥር መልካም ነው ሰው ይታዘብሀል።
    ሽመልስን ከመከላከል ይልቅ ጁዋርን መከላከል ይቀላል።
    ምን ጠብቀህ ነው ብልጽግና ውስጥ እንዲህ ቁም ስቅልህን የምታየው? ቃለ መጠይቅህን ቀድተህ ትሰማዋለህ ለመሆኑ? እስክንድርና ኢንጅነር ይልቃልን አፍህን ስትጠርግባቸው ትውላለህ ሽመልስ ግን ላንተ presice than egg ነው። አይ ጋዜጠኝነት እነ በአሉ ግርማ አረ ተዋረድን ንጉሴ አክሊሉ አረ አንድ በላቸው።
    ከአምበሳው ታምራት ነገራ ትንሽ ሞራል አትወስድም? ነውረኛ ነህ ከምር ይሄ ሁሉ ዜጋ ሲታጨድ የጌቶችህን ፊት እያይህ ትዘባርቃለህ ከተናግሮ አናጋሪ አውለኝ አለ።

  3. Dear Seyoum , are you alright ? What kind of nonsensical defense are you talking about? You may have a good friendship with Mr Shemekes and that is fine . You may not like individuals who got and released the audio ,and that is ok too. But trying to defend the indefensible is totally disgraceful even to your own political personality !

    • The weyanne T.Goshu,
      As the TPLF supporter and Tigray ethno-nationalist , you do not have any ground moral or otherwise to insult the courageous young activist Seyoum Teshome. Seoum Teshome is a hero who has struggled against the TPLF fascists and is popular among the youth.

  4. አቶ ስዩም ማንም ሰው የአቶ ሽመልስን ንግግር ትናንትና የቀረበ ነው ያለ የለም ። ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳነው እንደሚባለው አቶ ሺመልስ የተናገሩበትን ምክንያትም ሆነ ማስተባበያ ሳያቀርቡ አነተ ተጣድፈህ ይህን ማወናበጃ ምክንያት ለማቅረብ የፈለከው የቤት ሥራ ተሰጥቶህ መሆኑን የማንገነዘብ መስሎህ ከሆነ የምታታልለው ራስህን እንጂ እኛን አይደለም ። ሌላው የቻይልድ ሳይኮሎጂ በመጠቀም አዲስ አበባን አስመልክቶ የተናገረውን የተቃወምክ በማስመሰል ያቀረብከውን ማወናበጃ ተአማኒ ለማድረግ የሞከርከው ደግሞ ምን ያክል “ብስል” መሆንክን አመላካች ነው ። የአፍ ወለምታ በቅቤ ስለማይታሽ ራስህን እንደ ብቅል ፀሀይ ላይ ባታሰጣው ይበጅ ነበር ።

  5. Siyum Teshome
    Why don’t you just go to hell.
    Do you think we are born yesterday? We know what we heard and do not want any interpreter especially a vagabond like you. What happened to Amara people and orthodox Christians is executed as planned by Shimelis and abiy’s party. Church burning , done as he said he did. What does Protestant is more democratic than orthodox mean? This shows state and party mixed with religion. demographic change On Addis Ababa done as he said he did. People like you show up to defend the undefinable. Who is closer to abiy and his administration? The Lebanese incident or the Amara genocide? He is sorry for the lebanese while People’s throat are cut in shashemene and Arsi by Galla fanatics. May I go on? Now you come here to tell us Shimelis speech was a few months ago. It doesn’t make any difference if his speech is yesterday or yesteryear. What matters what we saw on the ground. Shimelis and abiy’s led opdo planned and excuted as planned. So, please do not put a salt on the victims wound. Simply go away and don’t Come back to tell us anything. We don’t want unsolicited information from your kind. if anything keep it to yourself, after all we know for whom you are working.

    • To Mesfin,
      From my point of view you are from under-graved TPLF. It is all of us demand for justice who lost their lives by betrayal of the people and their country killing people brutally without having humanity, they are dull-minded vagabond. However your way of expressing your idea has no any value for those innocent people rather creating hatred feeling among people.

      • Mr Ethiopia first,

        To me, Ethiopia without her people is just a barren land. Unlike you I am not looking for a barren empty land. I will say to you the same thing I said to siyum Teshome, that is you can not defend the undefandale. I caught him defending the killers who kill pregnant women and children who happen to be amahara and orthodox Christians. As for you if you want to be in the same camp as siyum Teshome then go to hell. I have no mercy for these kind of charlatans. Calling me tplf is your kind of charlatan politics we used to hear. So save your breath and stay on your side of the street. Our patience reached it’s limit, no more apology.

  6. ሥዩም ተሾመ የብልግና ፓርቲ ተከፋዮች ውሥጥ እንደሚካተት ሰምቸለሁ፤ ተግባሩም በግልጽ የሚናገረው ይህንኑ እውነታ ነው። አሁን ምን አድርግ ነው የምትሉት? ኅሊናውን ለገንዘብ የሸጠ ሰው በበላበት አይጩህ ነው የምትሉት? ዝም ካለማ ማን ለምን ብሎ ይከፍለዋል? ሥለዚህ ሥራውን ይሥራበት፤ አትነጂሱት።

    • ይነጋል ማልቀስ ነው የሚገባን ኢትዮጵያ ውስጥ እሱን የመስለና ተስፋዬ ገአብ። የተባሉት ጋዜጠኞች ሲባሉ። ሽመልስ አብዲሳ አፍሮ ቁጭ ብሏል ይሄ ሆዳም መቃብር የበቀለ ጫት እየበላ ይዘባርቃል። እንደሰው እንግዳ ጋብዞ ሰው አያናግርም ካልቃመ አይኑን አይከፍትም። ሰው ጠፋ ወይስ እነዚህ ጎን አልቆምም ብሎ ነው ሰው ጥጉን ይዞ የተሰወረው? በሰው ሁሉ ተስፋ እንዳትቆርጥ ታምራት ነገራ ተመስግ0ን ደሳለኝ የሚባሉ አምበሶች አሉ ግራ ገባን እኮ።

  7. አቶ ስዩም ተሾመ በጣም አክባሪህና አድናቂህ ነኝ። በቅርቡ በምትሰጣቸው አስተያየቶችህ ሙሉ በሙሉ አለመስማማቴ እንደተጠበቀ ሆኖ የዛሬው ደግሞ ትንሽ ወልገድገድ አለብኝ።በመጀመሪያ መረጃው ከሰባት ወር በፊት ገደማ በእጃቸው እንደገባና ባቀረቧቸው የተለያዩ ምክንያቶች እንዳዘገዩት ለእንደኔ አይነቱ ተራ አንባቢ ግልጽ ሆኖ ተቀምጦ እያለ እንዴት ልክ “ትላንት እንደተረገ ተደርጎ የወጣው መረጃ”
    ብለህ መረጃውን ለማጣጣል የሄድክበት መንገድ ላንተ ያለኝን ክብር እንዳይቀንስብኝ እሰጋለሁ። ሌላው መረጃው በድምፅ ቅጂ ተደግፎ የቀረበ ስለሆነ በመረጃው ላይ እንደወትሮህ ሰፋ ያለ ምርምሮችህን በማድረግ ጠለቅ ያለ ምሁራዊ ትንተናህን ታቀርብልናለህ ብዬ በጉጉት እጠብቃለሁ።
    አድናቂህ

  8. ስዩም ተሾመ

    ለምንድነው አንተ ለሽመልስ አብዲሳ ጠበቃ ሆነህ የምንትነግረን?
    ለምን ይህን የምትከዉን እራሱ ሽመልስ አብዲሳ ዘርዝሮ አይነግረንም፡፡ ከሁሉም የሚያስንቅ ነገር ቢኖር እንደ ውተት ዝንብ ጥልቅ ማከትህ ነው፡፡ ድንቄም የፖለቲካ ተንታኝ፡፡ አንዴ እነ እስክንድርን ታጥላላከህ፤ አከፍ ብከህ የአማራ ወኪሎች የሆኑትን አብንን ከወያኔ ጋር ትቅላቅላልህ የሚገርመው ይህንን ሁሉ የምትነግረን ደግሞ በኛው አማርኛ ቋንቋችን ነው፡፡ እነሽመልስን የምትከላከል ከሆነ እንዲሰሙህ በኦሮምኛ ብትነግራቸው አይሻልም? ደሞዝ እንዲጨምሩልህ ማለት ነው፡፡ እኛ የተበዳይ ወገኖች መሆናችን ትረሳዋለህ እንዴ? ምን አይነት አድር ባይ ብትሆን ነው ነፍሰጡር የሚገድልን ቡድን አድናቂ ሆነህ የመጣሃው? ትእግስታችን ከግራም ከቀኝም መፈታተን ዋጋ እንደሚያስክፍል የተረዳችሁ አይመስልም፡፡ ወገኖቻችን ታርደው ደማቸው ሳይደርቅ ልታሾፉብን ትመጣላችሁ፡፡ የማንም ሳይማር ወረቀት እየገዛ የሚኖር አድርባይ መሳለቂይ እንሁን እንዴ?

  9. ስዩም ተሾመ,ምን አለ ለሚያልፍ ግዜ ባትቀባጥር ?አንገት የት ፈጠረው ዞርብሎ ለማየት ነው ይባላል!እጅግ ፈጥነህ ለሆድህማደርያ በሚጥሉህ ፍርፋሪ ደንዝዘህ ለማያልፍ ትዝብትና ቅሌት መግባትህ ምን ያህል እየዘቀጥህ መሆንክ እንጅ ኢትዮጵያ ምጡቅ ሚልየን ልጆችዋ የዝንብ ጠንጋራ የሚለዩትን ሆድህ ሲጠግብ ረስተህ ስትቀባጥር ቢያንስ ለቤተስብህ ወይም ልጆችህ ማፈርያና መሽማቀቅያ ባትሆናቸው? መረጃው ያስደነገጠህና በቅጡ ያላዳመጥው መሆኑን አንተ ትላንት ሽመልስ እንደተናገረው ብለህ ስትፅፍ ለአሳዳሪዎችህ መከታና ጉርሻ ጣል እንድያደርጉልህ መውተርተርህ እውነትን አይቀይረውምና! ዛሬ በእነ እስክንድር በእነ እንጅነር ይልቃል ላይ ከአብይ አህመድ ጀምሮ የሚፈፀመው የሀስት ክስ ሆነምየመሰብስብያ ቦታ እስከመንፈግ ብሎም በእደባባይ ዶር አብይ ጦርነት ያስከፍተናል ያሉት ጉዳይ አቶ ሽመልስ የትናገሩትን ለማስፈፀም ነው;;
    አሁን በአዲስ አበባም ሆነ በኦሮምያ ክልል እየተክሄደ የአለው ጄኖሳይድ የኦሮሞ ውላጅ የሆነው ኦሮሞ ብልፅግና ፓርቲ እራሱ ኦሮሞ ኦሮሞን አይገድልም ብሂል እያስፈፀመው ነው!መቀሌ በመሽገው ህውሃት ማሳበብ ጅልነት የማሞ ቂሉ ትረት ነው!!ለጁሀር 56 ሚልየንብር በሀስተኛዋ አዳነች አቤቤ በዶር አብይ ትእዛዝ ነው የሀገሪቱ ብር ለሽብርተኛው የተስጠው ምክንያቱም እንደመጥቁ ዮሀንስ ለእነርሱ ወደፊት አፍርስው በኦሮሙማ ለሚፈጥሩዋት ኢትዮጵያ መንገድ ጠራጊያቸው ነውና!
    አቶ ተሾመ ስዩም ምድብህን ቦታ እንድናውቅ ስላደረከን እናመስግናለን!!ብዙ ልኢትዮጵያ የተደገስልን እልቂት ጄኖሳይድ ውንብድና ቁማር ወደፉት እንዳለ እናውቃለን!!ጅብ መጣብህ ማስፈራርያ ህውሀትን ተጠያቂ ማድረግ ያበቃበት ቁማር ነው!ምንግዜም እየተታለለ አንገቱ በገጀራ እየታረደ ሀብት ንብረቱ እየተቃጠለ አይኖርም!!እግዚአብሔርም በእርሱ አምሳል አክብሮየፈጠረው በፍፁም ጭካኔ እየታረዱ ሲቃጠሉ ክፉኛ ልቅሶ ማቅልብስው ሲያነቡ ዝም አይልም!አዎን እስራኤልን ከግብፅ ባርነት ከአርባ አመት በሁዋላ ሙሴን አስነስቶል!በእኛም በእርግጠኝነት ይሁናልም!ያ ዘመን በእናንተ አድርባይነት አይዞህ ባይነት አጫፋሪነት አይመለስም ይበልጥ እንድንጠንክር ወደ አምላካችን እያነባን ለዳዊት ሀይልን ጥበብን የስጠ አምላክ አይተወንምና በብርታት እየተማለድን ነው
    አንተም በቅጥፈትህ ይሉንኝታ በአጣው ብዕርህ ከመቀባጠር አትቦዝን!ስራህን የሚያይ የሚመዝን አለና!

  10. የኢትዮጵያ አምላክ አያሸልብም የሚባለው አለነገር አይደለም። ይህ የሺመልስ ቪዲዮ መውጣት ለብቻው ፣ ምንም ከሁዋላው ተጓዳኝ ባይኖረው በሀገር ክህደት የሚያስጠይቅ ነው። እጅግ አሳዛኝም ነው የዖሮማራን ጥምረት ለምናቀነቅን ዜጎች። ሆኖም ልክ ዛሬን ሰምቼው ቅስሜ ተስብሮ እየተከዝኩ የለማንና ጠይባን ብሎም ሚልኬሣን ሽኝት ሳዳምጥ አሃ! ለብዙ ጊዜ የከነከነኝን የለማን ዝምታ መልስ ስላገኘሁበት በበኩሌ ተረጋግቻለሁ። ብልፅግና ከውስጡ ያሉትን ቅራቅንቦዎች እንዲህ ያፅዳ እንጅ ። ይህን መልእክት አደራ ለዶር አቢይ አድርሱልኝ።

    ፩) የለማን ሽኝት እንደ ቀላል ሽኝት ሳይሆን ታሪኩን በዝርዝር ነገውኑ ጋዜጣዊ መግለጫ ይስጡበትና ሽኝቱን በአደባባይ ያጠናክሩለት። ሁላችሁም በኢትዮጵያ ፊት አናሳ ግለሰቦች ናችሁና። የኦቦ ለማ ያበቃልኝ በቪኦኤ አልተደመርኩም ያለን ቀን ነው። አለመታደሉ ነው እንጅ የኢትዮጵያ ቡልኮ ከጎጠኛ ጥብቆ እጅጉን ያምር ነበር። ምን ያደርጋል ታድያ? ያሳዝናል።
    ፪) ከሀጫሉ ህልፈት በሁዋላ ስለሆነው ወገኖቻችን እልቂት ጥልቅ የሆነ ለየት ያለ ለህዝባችን ይቅርታ ይጠይቁበት ሰኞ ጠዋት በትኩሱ። ቢያንስ መአት የብልፅግና አክራሪ ሹመኞች ስለተሳተፉበት በግልፅ ይሁን ተዘዋዋሪ ህዝቡን ይማለዱበት። ተቀፍድዶ ያላለቀውንም ሹመኛ ያጠናክሩበት። ብሪፊንግ ይፈልጋል ህዝቡ።
    ፫) አቶ ሽመልስ ለፖለቲካም ፍጆታ ይሁን ለምን የሚያለያይ ስለተናገረ በአቶ ታዬ ደንደአ ይተኩት። ይህው ነው። አምና ያንን ስህተት እንደሰራ በታዬ ይቀየር ብዬም ነበር ይህ ልጅ።
    ፬) አንድ ወንድም የቀድሞ ወታደሮችን ይሰብስቡ ያለውን እኔም አምና ስማለድ ነበር። ህግ ያስከብራሉ ቢያንስ። አደራ ያስቡበት። ብ/ጄ ካሣዬ ጨመዳን አስተባባሪ ያርጓቸው በኢትዮጵያ ይሁንቦት ዶር አቢይ።

    ፈጣሪ ይርዳን !!!!
    ህውሀቶችና አክራሪዎች ብዙም አትጨፍሩ። የኢትዮጵያ ትንሳኤ እውን ይሆናል። ለማየት ያብቃችሁ። አገር ወዳዶች ወደ ቀልባችሁ ተመለሱ። አትዘናጉም።

    • አባዊርቱ እግዜር አብዝቶ ይባርክህ! እጅግ በጣም ግሩም ሃሣብ ነው ያሰፈርከው። እንዲያውም ትንሽ አዳብረውና ራሱን የቻለ መጣጥፍ አድርገው። ይህን መሠል የኦሮማራ አቀንቃኝ ነው ያጣነው፤ አክራሪ በዛና ሊያፋጁን ነው። ያልኩህን አደራ!

  11. Thanks much, Sir.
    It is a very reasonable assessment and very much in line with what I am thinking. I tried to see what has been said by Ato Shimeles and I couldn’t find any single fact that can be considered as destructive or against the will of Ethiopians. People seems to forget that he is the president of Oromia and what he may present should, in one way or another, reflect the interest of the region and the Oromo people (unfortunately, this is how our political system is set up at the moment). I am sure, same will be said if the regional presidents of all other regions are discussing such matters with their cabinet or parliament members or their people in general. Even his points regarding Addis; what is wrong with the fact that creating other economic capitals in the country? May be the language he used is not as attractive or appealing as it should be, but the way I understood it, it is an interesting idea and will eventually address the chronic problem of ownership revolving around Addis. Imagine, Bahirdar, or Dessie, or Mekelle, or Hawassa, or Dire Dawa, or you name it…….. cities grow and have all the economic and political power like the
    at of Addis. Trust me it will be a dream come true and will definitely stabilize the current tensions revolving around Addis. Finfine…

  12. ሰላም ስዩም
    ስዩም ተሾመ እድግመዋለሁ ኢትዮጵያዊ ጀግና ነህ:: ነፍስህን አስይዘህ ከወያኔ ጋር ፊትለፊት የተጋፈጥክ ሀቀኛ ወገን:ነህ:: የወያኔን እባብነት አፍረጥርጠህ የማወቅ ችሎታህን አደንቃለሁ::
    አንዳንድ ደናቁርቶች አንተ ለጥቅም ያደርክ አድርገው ሲስሉህ ለእነሱ ህሊና አዘንኩላቸው:: ስዩም ተሾመ እስካሁን ካንተ አቋም ያልተዋጠልኝ ስለ አብን ነው:: የብሄር ድርጅትነቱ ሊዋጥልህ ባይችል እረዳሀለሁ:: ሆኖም ብልፅግናና ዶክተር ዐቢይ የብሄር ድርጅት አቀንቃኝ ናቸው:: ይህን እንዴት ታስታርቃለህ? ብልፅግናን አድንቀህ አብንን ያለመቀበል ሚዛናዊ አይደለም:: ከሁሉም በላይ ግራ ያጋባው ስለድርጅቱ መሪ በለጠ ሞላ ትውልድ ነው:: በለጠ በአባትና እናት አማራ ነኝ እያለ አንተ ከባለቤቱ የበለጠ አይደለም ብለህ የምትከራከረው ተቀባይነት እንዴት ይኖረዋል:: እኔ በእናቱ ኦሮሞም እንኳ ቢሆን ሸጋ የአማራ ድርጅት መሪ ይሆናል ብዬ አምናለሁ:: አብን እስካሁን ካየሁት የብሄር ድርጅት መነሻና መድረሻው ኢትዮጵያ የሆነ ድርጅት ነው:: አብን በአማራ ላይ የ45 አመታት ዘመቻ የፈጠረው የመከላከያ ሀይል ነው:: አብን የአማራ እሳት አደጋ መከላከያ ነው ማለት ይቻላል:: ስዩም ፀረ ኢትዮጵያዊውን ኦነግን በምትጠራበት አንደበት
    አብንን አትጥራ! እግዚአብሄር አይወደውም!

  13. ኦሮማራ ምን እንደሆነ ሽሜ ነገረን። በቃ ቁማሩ ተበልቷል።አቤት ስንት ሆድ አደር ታዘብን።

  14. “ከሚገድለኝ ሰይጣን ይልቅ የሚሰድበኝ ባለስልጣን ይሻለኛል! ሽመልስ የተናገረው በወቅቱ ትክክል ነው‼️”
    ስዩም ተሾመ
    ቼ በለው!
    ** ይህ ተርቦም፡ ተጠምቶም፡ ታርዞም፡ ተቃጥሎም ፡ተቆራርጦም፡ተፈናቅሎም፡ተገሎም የሚጨፍር ቆራጥ የፈረደበት ቦርቃቃ ሕዝብ ከሰይጣንና ከባለሥልጣን ውግረት ሌላ ምን ምርጫ አለው! ወደሽ ነው ገጣቢት ንጉስ ትመርቂ…
    “አቶ ሽመልስ አብዲሳ “በትላንትናው እለት የተናገረው ነው” ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ፒፒፒ (የፒኮክ ብልጥ’ገና ፓርቲን )ከብሔርተኛ ቡድን ለመነጠልና በድርጅቱ ውስጥ ተፈጥሮ በነበረው የኃይል ሹኩቻ አሸናፊ ሆኖ ለመውጣት በሚደረግ ጥረት የተናገረው እንደሆነ ተረጋግጧል።”…( ችግሩ መቼና ለማን አወራው ሳይሆን ጭብጡ ምንድነው? )
    **ይህ የሽመልስ አብዲሳ የመጀመሪያውም ይሁን የሁለተኛው ንግግር የዓብይ አህመድን ጨምሮ ስለተፎካካሪ ቡድን ስለለዘብተኛ አክራሪና ፅንፈኛ ጎራ መለየት አያወራም! በትክክል የሸፍጥ(ሴራ፡ሰሬ) ፓለቲካ የህወሓት ትምህርቶችን ብልጥገና እንዴት በፈጠነና በተቀናጀ መልኩ ኢዴፓን አጃጅለን…(አግባብተንም ግራ አጋብተንም) ኢትዮጵያን በልካችን አፍርሰን ሠርተን፤ በገዳ ሥርዓት በአፍሪካ ቀንድ የበላይነትን ተቀዳጅተን በሕዝብ ቁጥር ለሚቀጥሉት ሶስት ሺህ ዓመት በኦሮሙማ የሚመረጥና በኦሮሞ የሚመራ ብልጥገና እንዴት እንደሚቀጥል የተነደፈ ሐሳብ የተንፀባረቀበት ንግግር ቀደሞ፡ ሽመልስ አብዲሳም ይሁን ዓብይ አህመድ ሰበርናቸው አበረርናቸው ተመልሰው ያለእኛ ፍቃድ እዚህ አይደርሱም ዘመንና ሥልጣን በእጃችን ነው ” ሲሉ አባራሪና ተባራሪ፡ ባለቤትና መጤ ፡ባለግዜና ባለብዙ የሰው ኅይል አንደኛና ሁለተኛ ዜጋ ብልጥግና መሥርቷል! ስለዚህ ከሰይጣንና ከሥድብ ማማረጥ ቅንጦት ነው።
    እንዳለች እንደወረድች መዋጥ ሕገመንግስታዊ ግዴታ መሆኑን መረዳት ያሻል…አንዳንዴ ሲተነተን መበተን አለ!!
    “… ተቀናቃኙ ቡድን አሸናፊ ቢሆን ኖሮ አሁን ላይ ጃዋር_መሃመድ መገኛው እስር ቤት ሳይሆን ቤተመንግሥት ይሆን ነበር። ስለዚህ አቶ ሽመልስ የተናገረውን ነገር ከዚህ አንፃር ማየት ተገቢ ነው።”
    **ጀዋር ኮዬ ፈጬ ላይ ሰው ሊፈጭ ሜንጫና ሚስማር ይዞ ሲወጣ ሁለተኛው መንግስት ሆኖ ታምኖበት እንጂ የሕንጻው መሐንዲስ ወይም ቁጠባ ያደረገ ቡድን አዛዥ ሆኖ አልነበረም። ማነህ? ወዴት ነህ? ያለው የለም! ያም የሚነግረን “አንተ በዚያ ቅደም እኛ በሩቁ እንጠብቅሃለን የፈራ ይሸሻል ትወርሳላችሁ” ተብሎ ነው።የቦታ ባለቤት ለመሆን ሜንጫ ገጀራ ሚስማር የተጠቀጠቀበት አጠና ተሸክሞ፡ የማንንም ቤት ከፍቶ መሥፈር አጣና ዘርግቶ ባለመሬት መሆን በኦሮምኛ ኬኛ ማለት በቻ በቂ ነው። የቡራዩን የዘር ማፅዳት የተመከረበት የተቀናጀ ሥራ ታዝበናል፡ በጦፈው የኮረና የዓለም ሥጋት ወረርሽኝ በሽታ ዘመን ከቤት አትውጡ በተባለበት ወቅት መንገድ የተጣሉ ዜጎችን አይተናል፡ ሥራውም በደንብ የተቀናጀ በሥልጣን ተዋረድ በመመሪያ የተደገፈ ነው ሽመልስ አሁን የተናገረውም በቋንቋና በኢኮኖሚ ውህድ ማንነት ያለውን ጥሩ የአዲስ አበቤን ሕዝብ ኑሮ ማተራመስ፡ መስበርና ማፍረስ! አጠና ገጀራ ይዞ ከማስፈራራት የሰለጠነና ጥሩ ቁማር ነው። ህወሓት ኦነግን ሸወደ … ኦዴፓ አዴፓን ሸወደ!? ይለናል።
    “ጥቅምት 12/2012 ማታ አቶ ጃዋር መሃመድ ባስነሳው ሁከትና ብጥብጥ በንፁሃን ዜጎች ላይ ጥቃትና ጉዳት እንዳይደርስ ከመከላከል ይልቅ የጃዋር ጠባቂ ለመሆን በውድቅት ሌሊት መኖሪያ ቤቱ ድረስ የሄዱት ለማና ጠይባ፣ ልክ በድርጅቱ ግምገማ ሲደረግባቸው ከሰባት ወር በፊት የተቀዳን ንግግር ለፅንፈኛ የአማራ አክቲቪስቶች Leak አደረጉ።”
    *** ሽመልስ አብዲሳ ይሁን ዓብይ አህመድ “ጀውር አባ ሜንጫ ወንድማችን አጋራችን፤ መካሪችን ዋ! ተተኪያችን በእሱና በዓይን ቀልድ የለም” ሲሉ ነበር እንጂ ስለወደመ ንብረትም ይሁን ስለተጨፈጨፈው ህዝብና ተዘቅዝቆ ለተገደለው ዜጋ ትንፍሽ አላሉም… እንዲያውም የሀገሪቱ ጠ/ሚ መሆኑ የሠራዊቱ አዛዥ መሆኑን ዘንግቶ ወረዳና ቀበሌ አላስተዳድርም እራስህን ጠብቅ ይልሃል!? ጥቃት ከመፈፀሙ ቀድመው ራስመጠበቂያ መሳሪያህን ያስፈቱሃል…መጓጓዣ መኪና ክብሪትና ጋዝ ለፅንፈኛው ያቀርባሉ.. ፖሊስና ጸጥታ አስከባሪው የመከላከል ትዕዛዝ አልደረሰንም ሲሉ ቆመው በድሃ ዕንባና ደም ይዝናናሉ! ሲበረታም መሳሪያቸውን ለወንበዴ ያውሳሉ… በዚያው ሹፈት የተበረታታ መንጋ መዝረፍ፡መድፈር፡ ማረድ፡ ማቃጠል፡ የዘርማፅዳቱን ዘመቻ ቀጥሎበታል። በወረርሽኝ አመካኝቶ ከአዲስ አበባ ባሕር ዳር በአውቶቡስ ጭኖ ወስዶ አልበተናቸውም? አዲስ አበቤው የሥራ ማግኘት፣ መሰብሰብ መዘዋወር መብቱ አልተገታም? በአራቱም የአዲስ አበባ በሮች የመዝጋትና በእቅርቦት እጥረት እንዲሸበር አይደረግም? የሥራ ማስታወቂያ ለዖሮምኛ ተናጋሪ ቅድሚያ እየተባለ አደለም? የተናገረው እውነታና የብልጥገናን ገሃድ ነው።
    “ዋሽቶ ማስታረቅ” እንደሚባለው አቶ ሽመልስ የተናገረውን ተናግሮ ድርጅቱና የክልሉ መንግሥትን ከእንዲህ ያለ ፅንፈኛ ቡድን መታደግ በመቻሉ ሊያስመሰግነው ይገባል።በክልሉም ሆነ በሀገር ደረጃ አሸናፊ ሆነው እንዳይወጡ ለማድረግ በሚል ስለሆነ “እሰይ አበጀህ” ብዬዋለሁ”
    ** “ዋሽቶ ነፍስ ማዳን” ሲባል ተሰምቷል! አስታራቂው ውሸታም ከሆነ ምኑን አስታረቀው!? አዋለቀው እንጂ… ዓይኔን ግንባር ያርገው ካልሆነ አሁን ብልፅግና ብልግና ሆኖ ሕዝብ ንብረትና ሀገር ሲፈርስ ፅንፈኛው ቡድን የሚሰራውን እየሰራ ያለውን እና ሊሰራ ያቀደውን ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ የአፓርታይድ ወይም አክራሪ ወራሪ የካድሬ ሥልጠና ላይ የተነገረን እውነት እንጂ ከማንም ጋር የሚነካካ አደለም። ለማስተባበል የተሄደበት መንገድ በራሱ ፅንፈኛና ሽመልስ እንዳለው ” የገባውን አሳምነሀ ያልገባውን አወዛግበህ ትልምህን ማሳካት!” ለምን ተምታታበት (ተወዛገበ) ብለህ አትጠይቅ!።” ኦሮማራ በራሱ ወሮ ማራ ነው … ለጥፋት ቅንጃ መፍጠር ልክ እንደዚህ ፅሑፍ ግለሰቡ የፖለቲካ ተንታኝ ነውና ያመነውን አሳምን ያልገባውን ግራ አጋባው ትወና ማለት ነው። ከሚያጠፉት ሰዎች ይልቅ ጥፋትን የሚያጣፉት ሰዎች አጭቤ እጅግ አደገኞች ናቸው። አራት ነጥብ። ሰዩመ ብልጥ’ገና !

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share