May 17, 2020
25 mins read

“ውሸት ሲደጋገም እውነት ይሆናል።” መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

“If you tell a big enough lie and tell it frequently enough, it will be believed.”
adolf hitler
ሂትለር ቢልም
The truth is rarely pure and never simple.” ይለዋል
Oscar wild

የዓለም ሶሾ ፖለቲካል ኢኮኖሚ፣ ሁኔታ፣በአፍሪካ እና በአውሮፓ፣በአውሮፓ፣በአሜሪካ፣በሩሲያ እና በአጎራባቾቿ፣በቻይና እና አጓራባቾቿ፤በእግር ኳስ ጥበበኝነት በሚታወቁት በላቲን አሜሪካ ሀገሮች፤ እንዲሁም በመካከለኛው ምሥራቅ፣በሩቅ ምሥራቅ(በኮራያ ና ጃፓን) ፍፁም የተለየ ነው። የዛሬው ዓለምን ኢኮኖሚ ተቆጣጣሪዎቹ ቻይና እና አሜሪካም በየሀገራቸው ያለው ሶሾ ፖለቲካል ኢኮኖሚ የተለየ ነው።
በቻይና ያለ የፖለቲካ ና የኢኮኖሚ መንገድ በአሜሪካ የለም።የእንግሊዝ ና የኢራን ፖለቲካና ኢኮኖሚ አካሄድ ለየቅል ነው። በእንግሊዝ ና በአሜሪካ የዴሞክራሲ መብት፣የኢኮኖሚ መብት እና የፖለቲካ ተሳትፎ መብት ከግለሰብ ይጀምራል።
በአሜሪካ ና በአብዛኛዎቹ የአውሮፓ ሀገሮች፣ አንድ ግለሰብ ፣የአሜሪካንን ገፅታ ታበላሻለህ ተብሎ ፣ ከቀየው አይነቀለም፣ከጎዳና ላይ ወደ እሥር ቤት አይጋዝም ።በኃይማኖት ሰበብ አይቀሰፍም።ሌላውን ግለሰብ ሳያውክ ፣እንደነፍሥና ሥገው ምኞት መኖር ይችላል።…
የነፍሥና ሥጋ መሻቱን እንደአቅሙ እንዲያገኝ መንግሥታቱ ያመቻቹሉታል።ምክንያቱም መንግሥታቸው በተጠያቂነት ላይ የተመሠሰተ፣በህዝብ ይሁንታ ያለው ከመሆኑም በላይ ፣ህግ አሥፈፃሚዎቹ የነቁ፣የበቁና ህግን በተገቢው ያወቁ ናቸው።መንግሥትን በምርጫ ያቋቋመው ህዝብም መብትና ግዴታውን በሚገባ ያውቃል።አፍሪካ ግን ዛሬም የቀድሞ ቅኝ ገዢዎቿ ፣መቶ ፐሮሰንት ለህዝብ ጥቅም የቆመ መንግሥት እንዲኖር አይፈልጉም።
ያለመፈለጋቸውንም ዛሬም ፣በአፍሪካ ከምእራቡ ና ከሩቅ መሥራቁ፣በተለይም ከቻይና እና አሜሪካ ጥገኝነት የልተላቀቀ ሶሾ ፖለቲካል ኢኮኖሚ መኖሩ ይመሠክርልናል።
አሜሪካ እና ቻይና በግንባር ቀደምትነት ሌሎች የአውሮፓ ሀገራት በተከታይነት ፣ ዛሬም በወዳጅነት ሰበብ የብዝበዛ ግንኙነታቸውን ቀጥለዋል። ባላቸው የኢኮኖሚ ና የፖለቲካ አቅም በመጠቀም የአፍሪካ መንግሥታትን እና ህዝቡን እያሥፈራሩ ፣ ምንጊዜም ከእነሱ ጥገኝነት ሥር እንዳይወጣ እያደረጉት ነው።ምንም እንኳን ቻይና እና ሩሲያ በርእዮተ ዓለማቸው ከአውሮፓና አሜሪካ ቢለዩም ከጥቅም አንፃር የሚያራምዱት ፓሊሲ ተመሳሳይ ነው። ይህንንም እውነት ከልመና አዙሪት የማያላቅቀን፣በድርና እርዳታቸው ያሣብቅባቸዋል። …
እርግጥ ነው፣ሁሉም ባለፀጋ ሀገሮች “ዘላቂ ወዳጅነት እንጂ ዘላቂ ጥቅም አንፈልግም።” ብለው በውጪ ፓሊሲያቸው ውስጥ አላሰፈሩም። እናም ቅድሚያ የሚሰጡት ላልተቋረጠ ብዝበዛቸው ነው።
ለበለጠ ተጠቃሚነት ወይም ለተፈቀደ ብዝበዛ ፣ እጅግ የሚጥሩት ከበርቴዎቹ መንግሥታት ” አውሮፖና ታላቋ አሜሪካ” ይህንን ፖሊሲ የሚከተሉት በሚመሯቸው ሀብታሞች አሥገዳጅነት ነው።
እንደሚታወቀው፣ የአውሮፖ፣የቻይና እና የአሜሪካ ሀገራት ሀብታሞች የዓለምን ገብያ ተቆጣጣሪዎች ናቸው።በግዙፍ ባንካቸው አማካኝነት።በጥሬ ገንዘብም ሆነ፣ በኤሌክትሮኒክ መክፈያ ተጠቀመው የእያንዳንዳችንን ገንዘብ የሚቆጣጠሩት እነዚህ በአሜሪካ፣ በቻይና ፣በእንግሊዝ፣በጀርመን፣በሩሲያ፣በሲውዘርላንድ፣በፈረንሣይ ያሉ ባንኮች ናቸው። አብዛኛውን የዓለም ብር የሚቆጣጠረው ደግሞ የአሜሪካው የዓለም በንክ ነው።
የህ ባንክ ” ከድህነት ነፃ የሆነች ዓለም እመሠርታለሁ።” የሚል መሪ ቃል አንግቦ የተቋቋመ ባንክ ነው።ባንኩ በመጪው ሐምሌ 76 ዓመት ይሞላዋል። ይህ ባንክ በሚያበድረው ወለድ የገዘፈ እና ከተነሳበት ዋና ዓላማ ያፈነገጠ ነበር። ደሃ አገሮችን ከድህነት እንዳይወጡ አንቆ የያዛቸው በዋነኝነት ይህ ባንክ ነው።
ብድር አመቻማቹ አይ ኤም ኤፍም ሆነ የዓለም ባንክ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ ናቸው።ሁለቱም የዓለምን ገንዘብ ተቆጣጣሪዎች ከመሆናቸውም በላይ የአፍሪካን ፖለቲካ ወደ ፈለጉት አቅጣጫ እንዲሾር የሚያሥገድድ የኢኮኖሚ ኃይል እንዳላቸው ይታወቃል።
( የዓለም ባንክ ሠራተኞች በደርግ ውድቀት የራሳቸው ሚና ነበራቸው።የደርግ ውድቀትን ከውድቀቱ በፊት ያውቁ ነበር።ይህንን ለማወቅ ኢንጂነር ካሣ ገብሬ የሸገር ኤፍ ኤም 102 የጫወታ እንግዳ ሆነው በክፍል 3 ከክብርት ማአዛ ጋር ያደረጉትን ጭውውት አዳምጥ።በነገራችን ላይ ኢንጂነር ካሣ ገብሬ ከማአዛ ጋር ያደረጉት ጭውውት አሥተማሪ ጭውውት ነው።ሥለ ሃውዜን የነገሩንም የወያኔን እና የደርግን ሆዳሞች ተንኳል ያሣየ ነው።እርግጥ ኢንጂነርን ዓይነት ጠንካራ፣ቅን፣ሠራተኛ፣አዋቂ እና አሥተዋይ ባለሥልጣናት በደርግም ሆነ በወያኔ ኢህአዴግ ውሥጥ እንደነበሩ ሁሉ ዛሬም መሠል ሰዎች በብልፅግና ውሥጥ የሉም ማለት ከቶም አይቻልም። )
የዓለም ባንክም ሆነ ብድር አመቻማቹ የባንኩ ባልደረባ ድርጅት (World Bank and International monitor Fund) በወለድ ክፍያ ብዛት እያበጡ የሄዱ እና የአፍሪካ ሀገሮችን መቀመቅ ያወረዱ የአሜሪካ ቱጃሮች ንብረቶች ናቸው።ሥለ ታሪካዊ አመጣጣቸው በራሳቸው ቋንቋ የተፃፈውን ማንበብ ትችላላችሁ።
Motto : Working for a World Free of Poverty
Formation July 1944; 75 years ago
Not to be confused with World Bank Group .
The World Bank is an international financial institution that provides loans and grants to the governments of poorer countries for the purpose of pursuing capital projects. It comprises two institutions: the International Bank for Reconstruction and Development (IBRD), and the International Development Association (IDA). The World Bank is a component of the World Bank Group .

The World Bank was created at the 1944
Bretton Woods Conference , along with the
International Monetary Fund (IMF). The president of the World Bank is, traditionally, an American. The World Bank and the IMF are both based in Washington, D.C.
የዓለም ባንክ እንደሥሙ ዓለምን በሙሉ አለበለፀገም ።አሜሪካንን ከሁሉም በላይ፣ በመጀመሪያ ያበደራትን ፈረንሳይን ቀጥሎ ያበደራትን ቺሊን ግን አበልፅጓል።ይህንን እውነት ከፎርብስ መፅሔት መረዳት ይቻላል።
እንግሊዝን አሥቀድሞ ጀርመንን ፣ጣሊያንን አሥከትሎ ፣ድፍን አውሮፖን ማበልፀጉን የሀብት ደረጃቸው ፎርብሥ ይመሠክራል።ሌላ መሥካሪ የሚያሻው አይመሥለኝም።
ይህ በሥሙ ፣የሚያማልለን “የዓለም ባንክ” ባለፉት ዓመታት ባበደረው ብር አፍሪካን ከድህነት አላወጣትም።እናም የዓለም ባንክ ሳይሆን “የአሜሪካን ቱጃሮች ባንክ ” እንጂ የዓለም ባንክ መባል አይገባውም ነበር። ይሁን እንጂ ከእውነት ይልቅ ታላላቆቹ ሀገራት የሚነዙት ፕሮፖጋንዳ ይታመናል ና ይሄ ባንክ አፍሪካውያንን አቆርቋዡ ባንክ ሆኖ ሣለ የዓለም ባንክ እየተባለ መጠራቱ ያሥገርማል።
በአፍሪካ፣ ከደቡብ አፍሪካ እና ከግብፅ በሥተቀር ማነው በዓለም ባንክ እርዳታ የበለፀገው?
እርግጥ ነው፣በሌሎች የአፍሪካ ሀገሮችም ሆነ በናይጄሪያ፣በግብፅም ሆነ በደቡብ አፍሪካ የበለጠ የበለፀጉት ህሊና ቢሥ መሪዎቻቸው ና ግብረ አበር ቱጃሮች ናቸው።ዜጎች እና ዜጋ ያልሆኑ።ጥቂት ለሀገር እና ለህዝብ እድገት ደንታ የሌላቸው በልፅገውበታል። መበልፀግ ያለበት አርብቶ አደር ገበሬ ና ላብ አደር ግን ዛሬም በከፋ ድህነት ውሥጥ ነው።
በመላው አፍሪካ የእነዚህ ሚሊዮኖች ህይወት እጅግ አሣዛኝ ነው።ንፁህ የመጠጥ ውሃ እና መብራት ሊኖራቸው ይቅርና በቂ ምግብ፣ልብሥና መጠሊያ የላቸውም።እነዚህ ምንዱባኖች ከዚህ የሥቃይ ኑሮ እንዲላቀቁ ደግሞ በጥበብ መጥቀናል ፤በዕውቀት ተመንድገናል ፤ በቴክኖሎጂ ተራቀናል ፤ የሚሉ ሥልጡን ነን ባዮች በቅንነት አንዳችም እርዳታ ሲያደርጉላቸው አልታዩም።
በችጋር ና በችግር ሲያልቁ አምሳያቸው ሰው እንደሞተ እንኳን አይገነዘቡም።ከዚህ አንፃር እነሱ ጥበበኛ ነን ቢሉም ለእኔ ደንቆሮዎች ናቸው።በነሱ ተባባሪነት፣ የፓለቲካ ሥልጣንን በበለፀጉት ሀገራት እገዛ ( በምእራቡ ና በምሥራቁ እገዛ) በጉልበትና በሤራ የሥልጣንን መሪ በመጨበጥ ነፃ፣ገለልተኛ ፣ግልፅ፣ ተአማኒና ዴሞክራሲያዊ ባልሆነ ምርጫ እርካቡን ተቆናጦ መንበሩን በመያዝ፣ እሥከ ዘር ማንዘራቸው ከዓለም ባንክ ብድር ተጠቃሚ ከመሆናቸውም በላይ ሀብቱንም ወደ በለፀጉት ሀገራት በማሽሽ የበለፀጉት ሀገራት ባንኳች እንዲጠቀሙበት አድርገዋል። እያደረጉም ነው።የዚህ ፍቺ ደግሞ በተዘዋዋሪ የዓለም ባንክ እያሠረቀ የአፍሪካን ህዝብ እንዲደኸይ አድርጓል ማለት ነው። (ወዳጄ የቻይና ባንኮችም ፃድቃኖች ናቸው አልልህም።)
የዓለም ባንክ ሥርዓት የተፈጠረው በብድር ወለድ ለመበልፀግ ነው።ባንክ ያለብድር ምንም ነው።ባንክ ማለት በድር እና ወለድ ነው። ያደገውና ባለጡንቻ የሆነው በሚያባራ የወለድ ትርፍ ነው።
አፍሪካ የዓለም ባንክ እና የቻይና ባንክ ባበደሯት ብር የወለድ ክፍያ ብዛት ከወገቧ ቀና ማለት ያቃታት አሳዛኝ ሀገር የሆነችውም በዚህ ከፍተኛ ወለድ ምክንያት ነው።
የዓለም ቱጃሮች እድገት በየጊዜው የሚያገኙት ወለድ ከፍታ ከሚከፍሉት ብድር መብለጥ ነው ምሥጢሩ።ገንዘብን በየቀኑ በሚሊዮን ቤት እያተረፍክበት በባንክ ካሥገባኸው ብቻ ነው ቱጃር የምትሆነው።ያለማቋረጥ ታተርፋለህ ገንዘብህ ወለዱ እየጨመረ ብድርህ ዜሮ እየሆነ እንዲሄድ ሥም ካለው ባንክ ጋር ትተሳሰራለህ።አክሲዮንም ይኖርሃል።እናም በዓለም የታወቀ ቱጃር ትሆናለህ።መንገዱ ከተመቻቸለህ።
የዚህን እውነት ተጨባጭነት ደግሞ የዓለምን ቱጃሮች ሀብት እና ሥም በየዓመቱ የሚያሳውቀን “ፎርብስ” የተባለው ተቋም ይገልፅልናል።
2020
In the 34th annual Forbes list of the world’s billionaires, the list included 2,095 billionaires with a total net wealth of $8 trillion, down 58 members and $700 billion from 2018. The list was finalized as of 18 March, thus was already partially influenced by the coronavirus pandemic .
No. Name Net worth (USD ) Age Nationality
1 Jeff Bezos $113 billion 56 Uni States
2 Bill Gates $98 billion 64 Uni States
3 Bernard Arnault and family $76 billion 71 Fra
4 Warren Buffett $67.5 billion 89 Uni States
5 Larry Ellison $59 billion 75 Uni States
6 Amancio Ortega $55.1 billion 84 Spa
7 Mark Zuckerberg $54.7 billion 35 Uni States
8 Jim Walton $54.6 billion 71 Uni States
9 Alice Walton $54.4 billion 70 Uni States
10 S. Robson Walton $54.1 billion 77 Uni States
ከዝርዝሩ እንደምንገነዘበው፣ከ 3ኛው እና ከ6 ኛው ውጪ 8 ቱ አሜሪካኖች ናቸው።
በዓለም ላይ 2095 ቢሊየነሮች ሲኖሩ ድምር ብራቸው 8 ትሪሊዮን ነው።በቢሊየነሮች ብዛት አንደኛ አሜሪካ ናት።585 ቢሊዮነሮች አሏት ።ቻይና ሀለተኛ ሥትሆን የ476 ቢሊዮነሮች ባለቤት ናት።ህንድ 131፣ጀርመን 114 ወዘተ።
ከአፍሪካ ናይጄራያ ፣ግብፅ ና ደቡብ አፍሪካ በአለም የታወቁ ቢሊዮነሮች አሏቸው።በእርግጥ በግለሰብ ደረጃ የናይጄሪያው አሊኮ ዳንጎቴ አንደኛ ነው።የግብፁ ናሲፍ ሳዊሪሥ ደግሞ ሁለተኛ።
በከበርቴ ግለሰቦች ቁጥር አፍሪካዊ ከበርቴዎች ኢምንት ናቸው። የዓለም ባንክ ለአፍሪካ ዕድገት ያደረገው አሥተዋፆም ኢምንት ነው።ይህንንም እውነት ለማረጋገጥ ፣ከናይጄሪያ፣ከግብፅ፣ከደቡብ አፍሪካ፣ከማሊ፣ከዚምባብዌ በሥተቀር የበዙ ቱጃሮች በሌላው የአፍሪካ ሀገር ያለመኖራቸው ምሥክር ነው።በነዚህም ሀገሮች ኢኮኖሚውን በእጅ አዙር የሚዘውሩት ምእራባውያን ናቸው።እንደ እኛ አይነት ሀገሮች በተለይም የዓለም አቀፉ የንግድ ድርጅት ዓባል ያልሆኑ እና መላ ገብያውን ለከበርቴዎች ያላሥረከቡ ከዓለም ባንክ ብድር አያገኙም።
የእኛ አላሙዲን እንኳን በሀብት ላይ ሀብት የተጎናፀፉት በእጅ አዙር የወርቅ ንግዳቸውን ከኃያላኑ ሀገራት ጋራ በማሥተሳሰራቸው ነው።ዛሬበኢትዮጵያ ወርቅን ጨምሮ የመዓድን ማውጣት ሥራው ችግር ገጥሟታል።በየክልሉ የህግ የበላይነት እሥከሚሰፍንም ሥራ ያቆሙ የማዕድን አውጪዎች አሉ።አንዳንድ ፋብሪካዎችም በምርት ግብአት እጥረት ምርት ማምረት አቁመዋል።ወይም በሌለ የውጪ ምንዛሬ ጥሬ ዕቃ ከውጪ ሀገር እየገዙ ነው።…
ይህ ሁሉ ጦስ የመጣው ግን፣ ከህግ በላይ በመሆን ፣ ጥቂት የህወሓት አመራሮች ባለፀጋ በሆኑበት ባለፈው ዘመን ብዝበዛ ሰበብ መሆኑ አይዘነጋም። ሼህ መሐመድ ዓላሙዲንንም ከለቡት የከበርቴነት ማማ ላይ ቁልቁል ተምዘግዝገው እንዲወርዱ ያደረጋቸው ይሄ ለትውልድ ደንታ የሌለው” የእንብላ እና እንሙት” ሥርዓት ነው። ይሁን እንጂ እሳቸውም በዓለም ባንክ መዳፍ ውሥጥ ሥለሆኑ ለጠቅላላ ሀገሩ ብልፅግናን የሚያጎናፅፍ፣ ለገበሬውና ለላብ አደሩ የሚጠቅም፣ኢትዮጵያን ከሥንዴ ልመና ያወጣ የጎላ የልማት ሥራ በዚች ሀገር እንዳልሰሩ ይታወቃል።
የዓለም ባንክ ዋና ባለሥልጣናትም ዓላማ ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ አቅም እንዳይኖራት ማድረግ ነው። ኢትዮጵያ እንድትበለፅግ እንደማይፈልጉ የተገነዘብነው ለታላቁ የህዳሴ የኤሌትሪክ ማመንጫ ግድብ ዜሮ አምሥት ሣንቲም ያለማበደራቸውን በማስተዋል ነው።
በተቃራኒው፣ለብዝበዛ ተባባሪያቸው ለሲዊስ ካናል ባለቤት ለግብፅ ግን የተለየ የብድር ድጋፍ በመሥጠት ታላላቅ ፕሮጀክቶችን እንድትገነባ በማድረግ አበልፅጎታል።እኛ ወደብ አልባ ሥለሆንን ብልፅግናችንን አይፈልግም። የማይፈልገውም ያለታረሰው መሬታችንን እና ሰው ያረገጠውን ድንግል መሬታችንን በመቆመጥ ነው።ይህንን ህዝብ እንደ ሩዋንዳ አጨራርሼ መሬቷን የእኔ አደርጋለሁ በማለት ረጅም እቅድ አቅዷል።ከተባባሪዎቹ ጋር።ይህንን እቅዱን የሚያሳኩለት በሰሜን እና በመሐል ሀገር ዘረኛ እና ሆዳም ግለሰቦችን ፈጥሯል።ዛሬ እውነት እና የሰው ደም በቀኑ እንዳጋለጠው የሩዋንዳው ሂትለር “ፊሊሲን ካቡጋ” አይነቶችን እዛና እዚህ በእቅድ ተንኳል እንዲሸርቡ እያደረገ ነው።ከበሥተጀርባው ደግሞ የእነ ትራምፕ እጅ አለ።በውሸት እና በቅጽበት ዓለምን ለማሸበር የማይሳነው።ይሁን እንጂ እውነት የፈጣሪ ናትና ያሰቡት እንዳይሳካ ማንነታቸውን በየወቅቱ በማጋለጥ በህዝብ እንዲጠሉ ታደርጋለች።
በዓለም ላይ ውሸት በፕሮፖጋንዳ ገና እውነት ኮስምና ብትታይም አንድ ቀን የገነነውን ውሸት ፣ አይረቤ ፣የማይጠቅም ውዳቂ መሆኑን በዓለም ህዝቧች አማካኝነት ለወዳጆቿ በማሣየት ማሥደሰቷ አይቀሬ ነው።በዛን ጊዜም፣ በእውሸት ሲመፃደቁ የኖሩት መሬት ተከፍታ እንድትው ጣቸው ይመኛሉ።
የእውነትን ኃያልነት ለ26 ዓመት ራሱን ከህግ ሰውሮ ፣በኬኒያ መሽጓል ተብሏ ሲታመን ከነበረው፣”ፊሊሲን ካቡጋ” (Felicien Kabuga) በፈረንሳይ ሀገር በፓሪስ አቅራቢያ በሐሰተኛ ሥም እየኖረ መሆኑ ተደርሶበት ግንቦት 8/2012 እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በቁጥጥር ሥር መዋሉ መገንዘብ ይቻላል።
ይህ ሰው ከሁቱ ዘር የተወለደ ሩዋንዳዊ ከበርቴ ነው። የሁቱን ፋሺሥታዊና ዘረኛ እንቅሥቃሴ በፋይናሥ የሚደግፍ ከመሆኑም በላይ ፣ዘረኛና ፋሺሥታዊ ቅሥቀሳ በማድረግ የ800, 000 ሩዋንዳዊያን ብዙዎቹ “ቱትሲዎች” ናቸው ህይወት እንዲጠፋ ትልቅ ሚና የተጫወተውን RTLM የተባለ የቴሌቪዢን እና የሬዲዮ ጣቢያ ያቋቋመ ከሂትለር የማይተናነስ ግፈኛ ሰው ነበር።
እናም ይህ ግለሰብ በሰው ደም የተጨማለቀ ዶላሩን ይዞ ፈረንሳይ ሀገር ለ26 ዓመት እንዴት ኖረ?ማን ነው ፣መኖሪያውን የመቻቸለት ? ማነው የሐሰት መታወቂያ የሰጠው ?የኃያላኑ ሀገራት ቱጃሮች እጅ አልነበረበትም ወይ? ዛሬ በ84 ዓመቱ የኮሮና የቤት ለቤት ምርመራ ባያጋልጠው ኖሮ ሊያዝስ ይችል ነበር ወይ? ኃያላኑ በኮሮና ሰበብ የተደበቁ ወንጀለኞችን ከጎሬያቸው ለማውጣት የተቀናጀ ሥራ ባይሰሩ ኖሮ ሰውየው ይያዝ ነበር ወይ?…እነዚህ ጥያቄዎች መልሥ ይሻሉ።
ያም ሆነ ይህ የእውነት ቀን ደርሳ ግለሰቡ ተያዘ።ፕሮፖጋንዳው ግን እውነትን ያላካተተ እና የኃያላኑን ውንብድና የሚያሳብቅ ነው።እባካችሁ በፕሮፖጋንዳ አትፎግሩን ፣እሥራኤል ምንም የመጠቀ ቴክኖሎጂ ባልነበረበት ሰዓት የናዚን ወንጀለኞች እንዴት አድርጋ ፣ ከተደበቁበት እያነቀች ለፍርድ እንዳቀረበች፣አንዳንዶቹንም በአሠቃቂ ሁኔታ እንደተበቀለች አንዘነጋም።
በዛሬ ጊዜ ግን ውሸት በዝቷል።ውሸት ገዝፏል። ከዓለም ባንክ ጀምሮ እሥከ የዓለም ኃያላን መሪዎች ድረሥ የተዘረጋው የውሸት ድር ህሊና ላለው ያሳምማል።ከነዚህ ሰዎች እየተደጋገመ የምንሰማው ውሸት እንደ እውነት ተቆጥሯል። ሂትለር እንዳለው:-

“ዘዴ የተቀነባበረ ፣የበሬ ወለደ ውሸት ዋሽተህ ከደጋገምከው ተአማኒነት መግኘቱ አይቀርም።”

If you tell a big enough lie and tell it frequently enough, it will be believed.”
adolf hitler

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop