ምኞትና ቅዠት 000 – ጌቱ ለማ ሸዋንግዛው (ከአርባ ምንጭ)

ግንቦት 8/2012 በሪፖርተር የአማርኛው ጋዜጣ ላይ አቶ ልደቱ ሻሞ 274 በሚል ርዕስ የጻፉትን ምኞትና ቅዠት መሰል የ6ኛውን ምርጫ የህዝብ ተወካዮች ወንበር አሸናፊና ተሸናፊ ትንበያ አነበብኩት፡፡  ቀደም ሲል ስለሽግግር መንግስት አስፈላጊነት የጻፉትንም አንብቤያለሁ፡፡ ከነችግሩም በምክንያት የተደገፈ ነበር፡፡ ከዚህ በፊትም በተለያዩ መድረኮች የሚሰጧቸውን መከራከሪዎች ለኔ ይደንቁኛል፡፡ ዛሬ ግን እንዘጭ አሉብኝ፡፡ ግን በሰላም ነው፣ በጥቂት ቀናት ውስጥ አጀንዳ ለመወርወር በሚል የጻፉት ይመስለኛል፡፡ የሌላው ክፉ መንፈስ ተጋባብዎ እንዴ፣ ሌሎች ነበሩ ላለፉት 2 አመታት አጀንዳ ህዝቡንና ሚዲያውን ሲጭኑት የነበሩት፡፡ ሁሉም ፓርቲ ላይ ጉድፍ ቢኖርም አቶ ልደቱ በሚያሳብቅ መልኩ በተለይ ለብልጽግና እና ለኢዜማ ያለዎትን የመረረ ጥላቻ ፍንትው አድርገው አሳይተውበታል፡፡ ትንበያ ለማቅረብ ፓርቲን ማጥላላት ቦታው ነው ብለው ስላመኑበት ሳይሆን መደበቅ ስላልቻሉ ያመለጥዎ መልዕክት ስለመሆኑ ትዝብት ላይ መውደቅዎ አይቀሬ መሆኑ ይሰማኛል፡፡ በሌላው ጎን ተቃዋሚውን ጎራ ደግሞ ዲሞክራት (የትንበያዎ መነሻ ምርጫው ዲሞክራሲያዊ ከሆነ ስለሚል) ቢሰባሰብ የሚግባባና ለሽግግር መንግስት መስራችነት የሚመጥን የአርቆ አሳቢዎች ስብስብ፣ ከራስ ይልቅ ህዝብን፣ ከብሶትና የበደል ታሪክ ትርክት ይልቅ አይዲዮሎጂን መሰረት ያደረጉ አይነት አድርጎ መሳል ምነው ጋሽ ልደቱ ምን ነካቸው ያስብላል፡፡

ቀጥሎ በጽሁፍዎ ላይ ያለኝን አስተያየት/ነቀፌታ አቀርባለሁ

  1. አሁን ላይ ያሉት የተቀዋሚ ፓርቲዎች እንኳን ከበድ ባለ ቀርቶ ቀለል ባሉ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ስርዓት ባለው መንገድ መወያየት የሚያስችል ተሞክሮ እንደሌላቸው ፓርቲዎቹም፣ ህዝቡም እርስዎም ጭምር ያውቁታል፡፡ ታዲያ ሽግግር መንግስት የተባለው ውስጥ አዳራሽ ውስጥ ታጉራችሁ ስትራኮቱ እንጂ ተቻችላችሁ ለአገር ስንቅ ታበጃላችሁ ብለን ለማመን ቢከብደን ቅር ይልዎት ይሆን፡፡ ትርምሱ በኢትዮጵያዊነቱ ከማያምነው አገር አፍራሽ ጀምሮ እስከ ጠባብ ብሄረተኛው በተከማቸበት ስብስብ ሰላም፣ አንድነት፣ መግባባት ይፈጠራል ብሎ ማመን ይከብዳል፡፡ ምፍተሄው ምንድነው ካሉኝ ሁኔታችሁን ሲያዩት የሚያውቀው ፈጣሪ ብቻ ይመስለኛል፡፡
  2. ጥናት ነው ብለውናል፡፡ ጥናት ደግሞ ነጻ መሆን አለበት፡፡ እርስዎ ግን የግል አቋምዎ ብቻ ሳይሆን ምኞትዎ ጫማ ስር ወድቀው ነው ሰነዱን የጻፉት፡፡ ቁጥሮችን ትተን ድምዳሜዎችዎ በሙሉ ፍራቻ፣ ጥላቻና ምኞት ናቸው፡፡ ይህ ደግሞ ጥናት ሳይሆን ድርሰት ነው፡፡
  3. ሙሉ ዶክምንቱ ብልጽግና እና ኢዜማን ማጥላላት እና ስለእነሱ ውድቀት የሚያልም ነው፡፡ ከስያሜው ጀምረው አቋም አልባ ይሉታል፡፡ የፓርቲው ህገ ደንብ ደግሞ ህብረ-ብሄራዊ ነኝ ይላ፡፡ እስቲ መጀመሪያዎንና መጨረሻዎን ይመልከቱት፡፡ አቋም የለሽ፣ ማህበራዊ መሰረት የሌለው ይሉታል፡፡ አያስነቃም
  4. በአገራዊ ፓርቲ ስም የተደራጁትን የትኛውም ክልል እንደሚወዳደር ተዘንግቷል፡፡ የእርሰዎን ጭምር፡፡ ለምሳሌ ትግራይ ክልል ፓርቲዎ አይወዳደርምን፣ ወይንስ አንዳንዴ የክልል ሰዎች እንደሚሉን–በክልላችን ከሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ጋር ተወያይተን—፡፡ ህብረብሄራዊ የሆኑ ፓርቲዎች ክልላቸው የት ነው
  5. ብዙ ጊዜ ሳይንሳዊ መንገዶችን ተጠቅመው የምርጫ ውጤት ትንበያ የሚሰሩ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ ሰፊ ግዛት፣ ብዙ ህዝብና ውጥንቅጡ የወጣ ፖለቲካ ባለበት አገር ላይ በግለሰብ ደረጃ መስራት ከባድ ከመሆኑም በተጨማሪ ለጥናቱም ዳጎስ ያለ አቅም፣ ሃብትና ጊዜ ይጠይቃል፡፡ ታዲየ እንዴት ቻሉት፡፡ ደካማና ኮራጅ ተማሪዎች ገልብጠው ያመጡት የመመረቂያ ወረቀት ነው የሚመስለው፡፡
  6. ሌላው እርግጠኛ የሚመስል ቁጥሮች አሸናፊ በማለት ደርድረዋል፡፡ ምን የተባለውን ፎርሙላ ተጠቅመው ነው እንደዚህ ቁርጥ ያሉ ውጤቶችን ያገኙት፡፡ እከሌ ያሸንፋል ቢን ግምት እንላለን ግን ያለቁ እርግጠኛ ቁጥሮችን ማንም ጤነኛ የተማረ ሰው ሲያነበው ከየት አመጡት መባልዎ አይቀርምና መድረሻ መንገድዎ ባለመኖሩ ፉርሽ ትንበያ አስመስሎታል
  7. ሌላው ይህን ትንበያ በማየት ባንድ በኩል ተስፋ ለማስቆረጥ በሌላ በኩል ደግሞ ያሉት ካልሰመረ አመጽ ለማነሳሳት ያለመ ማመሻ ነው ብልዎ ቅር አይልዎም ብዬ ተስፋ ባደርግስ፡፡ በሌላ በኩል ብሄረተኞችን ጮቤ በማስረገጥ ወዳጅ ማፍሪያም ይመስላል፡፡
  8. የሚገርመው ምርጫው ዲሞክራሲያዊ ከሆነ አክራሪ ብሄረተኞች እንደሚያሸንፉ የተነበዩበት መንገድ አክራሪ ብሄረተኞችን ዲሞክራት በተቃራኒው ሌላውን ኢ-ዲሞክራት በማስመሰል የሄዱበት መንገድ ስምዎ እንጂ አቶ ልደቱ መሆንዎን ብጠረጥርስ

ሰላም እንሁን

2 Comments

  1. ይህ ልደቱ የሚባል ደላላ ደግፌ የተከራከርኩለት ቀን ይፀፅተኛል:: የሚያወራ በቀቀን እንጂ ከአሁን በሗላ የማይደመጥ ግለሰብ መሆኑን ያረጋገጠልኝ ከመስከረም 30 በሗላ ኢትዮጵያ መንግስት የላትም ብሎ አደገኛ ፕሮፓጋንዳ ያስተላለፈ እለት ነው:: እንዴት አንድ ለኢትዮጵያ ቀና ያስባል ተብሎ ከሚጠበቅ ግለሰብ ይህ አይነት የተዝረከረከ የወያኔ ምኞት ይስተጋባል:: በእሱ ቤት ጮሌ ዘመናዊ ፖለቲከኛ መሆኑ ነው የኢትዮጵያውያን ትዝብት ባረዳ አፉን በአባባይ አይከፍትም:: ለዚያው የኢዮጵያ አንድነት ከሚሸረሽሩት ጃዋር ጋር ሆኖ:: የአማራ ህዝብ ማፈሪያ!

  2. Whoever said Ethiopia got no government after መስከረም 30 must be modest giving the benefit of the doubt to PP because in all measurements Ethiopia currently has just a “Go” without the “vernment” .

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.